የኮቪድ-19 ማህበረሰብ ዝመና

September 16, 2022

ኮቪድ-19 የማህበረሰብ አደጋ ተጋላጭነት ደረጃ ለውጥ  ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች

ሶስተኛውን ሳምንት የትምህርት ቤት ቆይታ ስናጠናቅቅ በኮቪድ-19 ላይ ያለ ማሻሻያ አለ። ምንም እንኳን የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (ሲዲሲ/CDC) የኮቪድ-19 የማህበረሰብ ስጋት ደረጃ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ “ዝቅተኛ” ቢሆንም፣ በአዎንታዊ የኮቪድ-19 ጉዳዮች ላይ መጠነኛ ዕድገት እያየን ነው። ከክለምት ጉዞ እና ወደ ትምህርት ቤት መመመለስ በኋላ ለMCPS ሪፖርት ተደርጓል። እስካሁን ከፍተኛው የአዎንታዊ ምርመራዎች ቁጥር ባለፈው ሳምንት የሰራተኞች ቀን ቅዳሜና እሁድ በኋላ ሪፖርት ተደርጓል። እንደ እድል ሆኖ፣ በዚህ ሳምንት ጥቂት አዎንታዊ ውጢቶች ሪፖርት እየተደረገ ነው።

ሰራተኞቻችን እና ቤተሰቦቻችን ምልክቶች ሲታዩ ወይም ከተጋላጭነት በኋላ መመርመራቸሁን ስለቀጠላችሁ፣ የኦንላይን መመርመሪያ መሳሪያ ን ስለተጠቀሙ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤቶችን ስለተከተላችሁ እና የሲዲሲ ማግለል መመሪያዎችን  ስለተከተላችሁእናመሰግናለን። በህመም ወቅት ቤት እንደመቆየት ያሉ ዋና ዋና የጤና ስልቶች እና ጥሩ የእጅ መታጠብ የኢንፌክሽን ስርጭትን ለመገደብ ጠቃሚ ናቸው። መርሃ ግብሮቻችን ስራ እየበዛ ሲሄዱ፣ መሰረታዊ ነገሮችን አስታውሱ - እረፍት፣ ጥሩ አመጋገብ እና ንቁ መሆን ሁሉም ተማሪዎች ጤናማ እና ለመማር ዝግጁ እንዲሆኑ ይረዳሉ።

እባክዎ ያስታውሱ የፊት ጭምብል ማድረግ የግል መርጫ  ቢሆንም፣ በአንዳንድ ሁኔታዎች የፊት  ጭምብል ለጊዜው ያስፈልጋል፡

  • ሊሆኑ የሚችሉ የኮቪድ-19 ምልክቶችን ለመገምገም ወደ ጤና ክፍል የሚያቀርቡ ተማሪዎች።
  • በትምህርት ቤት ወይም በሥራ ቦታ በኮቪድ-19 እንዳለባቸው የታወቀ ሰራተኞች ወይም ተማሪዎች።
  • በኮቪድ-19 የተያዙ ሰራተኞች ወይም ተማሪዎች፣ ለአምስት ቀናትን መገለልን ከጨረሱ በኋላ፣ ወደ ትምህርት ቤት ወይም ወደ ስራ ለመመለስ ጥሩ ስሜት የሚሰማቸው (እስከ 10ኛው ቀን ድረስ  የፊት ጭምብሉ ይለብሳሉ)።
  • በወረርሽኝ ወቅት የተጋለጡ ግለሰቦች እንደ አማራጭ ለ10 ቀን ለይቶ ማቆየት። ። የተጋለጡ ሰራተኞች እና ተማሪዎች የበሽታ  መልክት እንዳሳዩ እስካልተረጋገጠ ድረስ መገለል አያስፈልጋቸውም እና ከተጋለጡ በኋላ ለ 10 ቀናት ጭምብል ማድረግ ይችላሉ።

በጤና ጉዳዮች፣ በወጣትነት ዕድሜ ወይም በሌሎች ምክንያቶች የፊት ጭምብልን በአግባቡ ማድረግ የማይችሉ ልጆች በወረርሽኝ ጊዜ ሌሎች የመከላከያ ዘዴዎችን ሊፈልጉ ይችላሉ። በማንኛውም የአደጋ ደረጃ፣ አንድ ግለሰብ በራሱ  ምክንያቶች የፊት ጭምብል ለመልበስ ወይም ሌላውን ሰው ለመጠበቅ የሚያደርገውን ውሳኔ እናከብራለን።

ክትባቱ አሁንም በኮቪድ-19 ምክንያት ከባድ ችግሮችን ወይም ሞትን ለመከላከል በጣም ውጤታማ መሳሪያችን ነው፣ እና በበሽታው የመያዝ ስጋትን ሊቀንስ ይችላል። ከአዲሶቹ የOmicron ንዑስ ተለዋጮች ጥበቃን የሚያካትቱ አዲሱ የኮቪድ-19 ማበረታቻዎች አሁን በትምህርት ቤት ላይ የተመሰረቱ የክትባት ክሊኒኮችን ጨምሮ ካውንቲ ስፖንሰር የተደረጉ ክሊኒኮችወይም በችርቻሮ ፋርማሲዎች ወይም ሌሎች አካባቢዎች

በአስተማማኝ፣ በአካል ለመማር ያለንን ቁርጠኝነት ለመደገፍ ንቃት፣ ዝግጅት እና መከላከል አስፈላጊ ናቸው። ከሕዝብ ጤና አጋሮቻችን ጋር በካውንቲ እና በት/ቤት ደረጃ ያሉ የመረጃ አዝማሚያዎችን በቅርበት መከታተል እንቀጥላለን እና ሁሉም ሰው የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመገደብ የመከላከያ እርምጃዎችን እንዲወስድ እናበረታታለን።

የMCPS ማህበረሰባችንን ጤናማ ለማድረግ ስላደረጉት እገዛ እና ቁርጠኝነት በድጋሚ እናመሰግናለን። መልካም ቅዳሜና እሁድ ይሁንልዎ!
ከልብ

ፓትሪሺያ ካፑናን/Patricia Kapunan፡ M.D., MPH
MCPS Medical Officer



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools