ሐሙስ፣ ኦገስት 8 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ለሀሙስ፣ ሴፕቴምበር 8 መታወቅ ያለባቸው ሥምንት ነገሮች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል። የሚያካትቱትም ስለ ኮቪድ-19 መረጃ፣ ስለ ባስ/አውቶብስ መስመሮች መረጃ፣ ነፃ የት/ቤት ምግቦች መገኘት፣ የመገኛ አድራሻዎትን እንዲያድሱ ጥያቄ፣ በስቴት-የታዘዘ የጤና ትምህርት ስርዓት፣ የቤተሰብ አካዳሚ የሚሄድ / Parent Academy TO GO እና ስለ MCPS ተመራቂዎች መልካም ዜናዎችን ነው።

 

 1. አዲሱን ኮቪድ-19 ያለባቸው የመነጠል/ብቻ የመሆን መመሪያዎች ተገንዘቡ
  ሰራተኞች እና ቤተሰቦች አሁንም የኮቪድ-19 ያለባቸውን ሪፓርት ማድረግ መቀጠላቸው አስፈላጊ ነው፣ ይሄንን የሚያደርጉትም በዚህ ኦንላይን ቅፅ ነው። የተሻሻለ የመነጠል መለኪያ የተቆራኘ/ሊንክ የተደረገው ወደ ስራ ወይም ት/ቤት መቼ ብትመለሱ ተገቢ እንደሚሆን መረዳት እንድትችሉ ነው።
 1. ስለተሻሻሉ የኮቪድ-19 ቡስተሮች (Boosters) እወቁ
  ባሳለፍነው ሀሙስ፣ CDC ከተሻሻለ የኮቪድ-19 ቡስተሮች (Boosters) ክትባቶች እውቅና ሰጥቷል። ክትባቶቹ ባይቫለንት/ “bivalent” ናቸው፣ ይሄም ማለት የሚሰጡት ጥበቃ ለሁለቱ ለመጀመሪያው ኮቪድ-19 ለሚያስከስተው SARS-CoV-2 ቫይረስ፣ እና አሁን ላይ እየተስፋፋ ለአለው ሌላ መገለጫው የሆነው Omicron ተለዋጭ (BA-4 እና BA-5) ነው። ማንኛውም እድሜው ከ12 አመት በላይ የሆነ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰደ ሰው ቡስተሩን (booster) መከተብ ይችላል/ትችላለች። የ Pfizer ክትባት 12 አመት እና ከዛ በላይ ለሆናቸው የተፈቀደ ነው። የ Moderna ክትባት 18 አመት እና ከዛ በላይ ለሆናቸው የተፈቀደ ነው። ሁለቱም ቡስተር (booster) ክትባቶች መሰጠት ያለባቸው ከቀዳሚ ተከታታይ ክትባቶች በኋላ ነው፣ እናም የመጨረሻው ክትባት ወይም ቡስተር (booster) ከተወሰደበት ቀን አንስቶ ከ8 ሳምንታት በኋላ ሊሰጥ ይችላል።
  እነዚህን ክትባቶች የት ማግኘት ይችላሉ፦
  የሞንትጎመሪ ካውንቲ ጤና እና የሰው አገልግሎቶች ክፍል አሁን ላይ የተሻሻለውን ባይቫለንት / bivalent የኮቪድ-19 COVID-19 ቡስተር (booster) ክትባት እየሰጠ ነው ። ይሄም አሁን ላይ 12+ እድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙት በካውንቲ-ስፖንሰር የተደረጉ ክሊኒኮች (ት/ቤት-መሰረት ያደረጉ ክሊኒኮችን ጨምሮ) ውስጥ የሚገኘው ብቸኛ ቡስተር (booster) ነው። ቀጠሮዎች አሁን ላይ ማስያዝ ይመከራል። የሜሪላንድ ክትባት ፈላጊዎች / Maryland's Vaccine Locator የቡስተር (booster) ቀጠሮዎችን እየሰጡ የሚገኙ ፋርማሲዎችን እና ሌላ ቦታዎችን በተመለከተ እና ይሄንን ቡስተር (booster) በሚመለከት አጋዥ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች / FAQ ላይ መረጃ ይሰጣሉ።
 1. አዲሱ ኦንላይን የሚያካትተው ስለ ባስ መስመሮች መዘግየት ሪፖርቶችን ነው
  በጨመረ የትራፊክ መጨናነቅ፣ በተማሪዎች ተሳፋሪነት ማሻሻያዎች ወይም  መስመሮቹን ለመጨረስ ሁለት ጊዜ ወይም ከዛ በላይ መመላለስ አስፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ በትምህርት አመት መጀመሪያ ላይ የባስ መዘግየቶች ሊከሰቱ ይችላሉ። ቤተሰቦች አዲሱን የኦንላይን መተግበሪያ/መሳሪያ በመጠቀም የልጃቸው ባስ መስመር በሰአቱ መድረሱን ወይም መዘግየቱን ማረጋገጥ ይችላሉ። መዘግየቶች በዚህ ድህረገፅ/ድር ጣቢያ ላይ ይለጠፋሉ።
  Connect-Ed ስልክ ጥሪዎች በእያንዳንዱ ምሽት ላይ በሚቀጥለው ቀን ላይ የተማሪያቸው የባስ መስመር ይሸፈን እንደሆነ ለቤተሰቦች ለማሳወቅ ይደወላሉ።
 1. የት/ቤት ምግቦች ለልጅዎ በነፃ የሚቀርቡ መሆኑን አረጋግጡ
  ለነጻ ወይም ለዋጋ ቅናሽ ብቁ የሆኑ የተማሪ ቤተሰቦች አሁን ለትምህርት ቤት የምግብ እርዳታ ማመልከት ይችላሉ። ብቁነት በቤተሰብ ብዛት እና በጠቅላላ የገቢ መጠን ላይ የተመሰረተ ነው። በሜሪላንድ ውስጥ ለቅናሽ ምግብ ብቁ የሆኑ ተማሪዎች ነጻ የቁርስ እና የምሳ ምግብ ያገኛሉ።
  ጠቃሚ ማስታወሻ፦ በት/ቤት ስርዓት ፖሊስ መሰረት፣ ማንም ልጅ በ MCPS ት/ቤት ውስጥ ምግብ አይከለከልም እና ማንኛውም መክፈል አለመቻል አማራጭ ምግብ እንዲቀርብ አያደርግም።
  እዚህ ያመልክቱ።
  ስለ ፕሮግራሙ የበለጠ ይወቁ
 1. የመገኛ አድራሻዎን በ ቤተሰብ / ParentVUE ውስጥ አድሱ/አስተካክሉ ይሄም ይሄም ከ MCPS እና ከልጅዎ ት/ቤት መረጃ ለመቀበል ያስችልዎታል
  ሁሉም የ MCPS ቤተሰቦች ለ ቤተሰብ አድራሻ/ParentVUE account ለማግኘት እንዲመዘገቡ ይበረታታሉ እና የአድራሻችሁ መረጃ አሁን ላይ ያለውን የሚያሳይ መሆኑን አረጋግጡ። ቤተሰብ / ParentVUE፣ ኦንላይን የቤተሰብ ገፅ/ portal፣ ት/ቤቶች ውጤቶችን፣ መገኘትን፣ የቀን ቀጠሮ ለማስያዝ፣ የኔMCPS ክፍል / myMCPS Classroom ለማግኘት እና ሌሎችም ነገሮችን በሚመለከት መረጃ ለማጋራት በተቀዳሚነት የሚጠቀሙት ነው። ParentVUE(ፓረንት ቪው) እንዲሁም የዲጂታል ትምህርት መድረክ የሆነውን Canvas/MyMCPSClassroomን(ካንቫስ ማይ ኢምሲፒአኢስ ክላስሩም)ን ይፈቅዳል። ወላጆች እና አሳዳጊዎች የማስተማሪያ መረጃን እና ግብዓቶችን ማየት እና ስለ ምደባዎች እና ውጤቶች ማንቂያዎችን/መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።
 1. በስቴት-የታዘዘ የጤና ስርዓተ-ትምህርት ማሻሻያ
  የሜሪላንድ ስቴት ትምህርት ክፍል አሁን ላይ የ2025 እና ከዛ ጊዜ በኋላ የሚመጡ ተመራቂ ተማሪዎች 1.0 በጤና ትምህርት አይነት ይዘው መጨረሳቸውን ለምርቃት መስፈርት አድርጓል። የጤና ትምህርት ይዘት የሚያካትተው የተለያዩ ማህበረሰቦችን መረጃ እና ግብዓቶች ነው፣ ይሄም የ LGBTQ+ ማህበረሰብ አባላትን ያካትታል።  ቤተሰቦች ከቤተሰብ ህይወት እና የሰው ተፈጥሯዊ ፆታ ትምህርት ክፍል መውጣት ይችላሉ፣ በስቴት ህጉን በመከተል። እዚህ የበለጠ ይወቁ፦ MSDE ጤና ትምህርት ስርዓተ-ትምህርት ማዕቀፍ
 1. የፎል/መኸር የቤተሰብ አካዳሚ / Parent Academy ለቤተሰቦች ጠቃሚ መረጃዎችን ይዟል
  የቤተሰብ አካዳሚ / Parent Academy የሚሄድ / TO GO በመጠቀም ቤተሰቦች እና ተማሪዎች አመቱን ሙሉ ተሳታፊ ሆነው መቆየት ይችላሉ፣ ይሄም ቤተሰቦች በቤታቸው ሊያዩ የሚችሉት ተከታታይ የድህረገፅ ሴሚናሮች (webinars) ነው። የድህረገፅ ሴሚናሮች (webinars) በቤተሰብ አካዳሚ ድህረገፅ/ድርጣቢያ ላይ ይገኛሉ። ለመመዝገብ እዚህ ይክፈቱ።
 1. መልካም ዜና፦ ዋልተር ጆንሰን (Walter Johnson) ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2022 ተመራቂ ሙሉ በሙሉ የተሸፈነ ስኮላርሺፕ/የትምህርት እድል በ ስፔልማን (Spelman) ኮሌጅ ማግኘት
  ሜሪ አንድሬ (ጆይስ) ኦናን ምፌጅ / Marie Andre (Joyce) Onana Mfege በዚህ መኸር (fall) በ ስፔልማን (Spelman) ኮሌጅ ትምህርቷትን ትከታተላለች እና እንደ የ ዶቬይ ጆንሰን ራውንድትሪ ስኮላር / Dovey Johnson Roundtree Scholar በመሆን እውቃና ተሰጥቷታል። እንደ የስኮላርሺፕ/የትምህርት እድል ተቀባይ፣ ጆይስ (Joyce) ከሀያዎቹ አንዷ የ ዶቬይ ጆንሰን ራውንድትሪ ስኮላር / Dovey Johnson Roundtree Scholar አሸናፊ/ተቀባይ ሆናለች፣ ይሄም የሚያካትተው ለሚቀጥሉት አራት አመታት የትምህርት፣ የክፍያዎች፣ የክፍል፣ እና የመኖሪያ ወጪን ያካትታል።
  እንኳን ደስ አለሽ ጆይስ (Joyce)!
  የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ  Montgomery County Public Schools Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools