ሐሙስ፣ ኦገስት 25 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ለሐሙስ ነሐሴ/ኦገስት 25 ማወቅ ያለብዎ ዘጠኝ ነገሮች እዚህ አሉ፡ ስለ MCPS 2022-2023 ወደ ትምህርት ቤት መመለስ መክኒያት የሚደረግ ትርዒት፡ የነጻ እና የዋጋ ቅናሽ ማመልከቻዎች፣ አስፈላጊ የትምህርት ቤት ስርዓት መሳሪያዎች ለቤተሰቦች፣ የአውቶቡስ መስመር መረጃ እና የትምህርት መጀመሪያ ቀን ፎቶዎች ጥያቄውች ያካትታሉ።

  1. እንኳን ወደ 2022-2023 የትምህርት ዘመን በደህና መጡ!

MCPS Back to School Faitሰኞ፣ ነሐሴ/ኦገስት 29፣ MCPS ወደ 160,000 ለሚጠጉ ተማሪዎች በሩን ይከፍታል። ለመምህራን፣ ለሰራተኞች እና ለአስተዳዳሪዎች፣ ይህ ቀን ለወራት ስንጠብቀው እና በጋውን በሙሉ ስንዘጋጅበት የነበረ ቀን ነው። የMCPS ሱፐርኢንቴንደንት ሞኒፋ ማክናይት(Monifa McKnight ) እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ፕሬዘዳንት ብሬንዳ ዎልፍ(Brenda Wolff ) ተማሪዎችን፣ ቤተሰቦችን እና ሰራተኞችን ዲስትሪክቱ አዲሱን የትምህርት አመት መጀመሩን አስመልክቶ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።
ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ
የ2022-2023 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ እዚህ ይገኛል።

  1. ትርኢቱ ቅዳሜ ነው! ወደ ትምህርት ቤት መመለን ለማክበር ይቀላቀሉን።

MCPS Back to School Faitበ 2022-2023 የትምህርት ዓመት ከ 10 a.m. እስከ 1 p.m. ባለው ጊዜ ውስጥ MCPS ሰራተኞችን እና የማህበረሰብ አጋሮችን ይቀላቀሉ ። ቅዳሜ ነሐሴ 27 በዌስትፊልድ ዊተን የገበያ አዳራሽ። ለክትባቶች ወይም መከላከያዎች ቀጠሮ ለመያዝ የትምህርት ቤት ዳግም መከፈት ማሳያ ትርዒት ድር ጣቢያውን ይጎብኙ

  1. በነጻ እና በቅናሽ ዋጋ የምግብ ጥቅሞችን ለማግኘት በኦንላይን አሁን ያመልክቱ

ለነጻ ወይም ለዋጋ ቅናሽ ብቁ የሆኑ የተማሪ ቤተሰቦች አሁን ለትምህርት ቤት የምግብ እርዳታ ማመልከት ይችላሉ። ብቁነት በቤተሰብ ብዛት እና በጠቅላላ የገቢ መጠን ላይ የተመሰረተ ነው። በሜሪላንድ ውስጥ ለቅናሽ ምግብ ብቁ የሆኑ ተማሪዎች ነጻ የቁርስ እና የምሳ ምግብ ያገኛሉ።
እዚህ ያመልክቱ።
ስለ ፕሮግራሙ የበለጠ ይወቁ

  1. ከትምህርት ቤትዎ ጋር ለመገናኘት ለ ParentVUE(ፓረንት ቪው)ይመዝገቡ

ለMCPS አዲስ የሆኑ ቤተሰቦች በትምህርት አመቱ መጀመሪያ ላይ ለParentVUE(ፓረንት ቪው) መለያ እንዲመዘገቡ ይበረታታሉ። ParentVUE(ፓረንት ቪው)  ስለ ክፍሎች፣ የተማሪ መገኘት መከታተያ፣ የጊዜ ሰሌዳ አወጣጥ፣ የmyMCPS ክፍል መክፈቻ እና ሌሎችንም በተመለከተ መረጃን ለመለዋወጥ ለት/ቤቶች እንደ ዋና የመገናኛ መዘዋወርያ ሆኖ የሚያገለግል የአኦንላይን  የወላጅ ፖርታል ነው።
ParentVUE(ፓረንት ቪው) ከትምህርት ቤት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና የተማሪዎችን መረጃ የሚመለከቱበትን መንገድ ያቀርባል። ለአትሌቲክስ፣ ለልዩ ፕሮግራሞች ይመዝገቡ፣ ከመምህራን ጋር ይገናኙ እና የተማሪዎን መረጃ በየአመቱ ያረጋግጡ።
ParentVUE(ፓረንት ቪው) እንዲሁም የዲጂታል ትምህርት መድረክ የሆነውን Canvas/MyMCPSClassroomን(ካንቫስ ማይ ኢምሲፒአኢስ ክላስሩም)ን ይፈቅዳል። ወላጆች እና አሳዳጊዎች የማስተማሪያ መረጃን እና ግብዓቶችን ማየት እና ስለ ምደባዎች እና ውጤቶች ማንቂያዎችን/መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።

  1. ይመዝገቡለ Alert MCPS

ማንቂያ MCPS ስለ ትምህርት ቤት መዘጋት ወይም ድንገተኛ አደጋዎች የድንገተኛ ጊዜ መረጃ በጽሁፍ ወይም በኢሜይል ለሚመዘግቡ መሳሪያዎች ያቀርባል። እዚህ ይመዝገቡ።

  1. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቤተሰቦች፡ ለናቪያንስ(Naviance) ይመዝገቡ

Naviance(ናቪያንስ) ፡ Tይህ ፕሮግራም ተማሪዎች የኮሌጅ እና የስራ እቅድ ሂደትን ቀላል ለማድረግ ይረዳቸዋል። ናቪያንስ(Naviance)የኮሌጅ እና የስራ ቢሮ  የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቤተሰቦችን ኢሜይል ለመላክ የሚጠቀምበት መድረክ ነው። ለበለጠ መረጃ የተማሪዎን ትምህርት ቤት አማካሪ ያነጋግሩ።

  1. እነዚህን አስፈላጊ የመረጃ አሰራሮችን  እወቅ
  • GoFanይህ የኦንላይን  ዲጂታል ትኬት መመዝገቢያ መድረክ  ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዝግጅቶች ፈጣን እና ቀላል አሰራርን ያቀርባል፣ እናም ደጋፊዎች በፍጥነት እና ደሀንነታቸው ተጠብቆ ወደ ጨዋታዎች እንዲገቡ ያስችላቸዋል። ትኬት ለሚያስፈልጋቸው ስፖርቶች ትኬቶች ከአሁን በኋላ በሩ ላይ አይሸጡም እናም በአኦንላይን መገዛት አለባቸው።
  • SchoolCash Online፡ https://www.schoolcashonline.com MCPS  ለሁሉም ከትምህርት ቤት ጋር የተያያዙ ክፍያዎች እንደ ተመራጭ የመክፈያ ዘዴ ወደዚህ የመስመር/አኦንላይን የክፍያ ስርዓት ተሸጋግሯል። ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች አሁን ለገንዘብ ማሰባሰብያ፣ የመስክ ጉዞዎች፣ የኮርስ ክፍያዎች እና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች SchoolCash Onlineን ይጠቀማሉ። ይህ አዲሱ የክፍያ ስርዓት ከትምህርት ቤት የመመገቢያ ቦታ መለያዎች ጋር የተገናኘ አይደለም።
  • MySchoolBucks(ማይ ስኮል በክስ)፡የትምህርት ቤት ምግብ መግዣ ገንዘብ ወደ ልጅዎ መለያ ለመጨመር MySchoolBucksን ይጠቀሙ። ይሄ አሠራር ልጅዎ በየቀኑ ወደ ት/ቤት ገንዘብ ይዞ/ይዛ መምጣትን ያስወግዳል። በዚህ አመት፣ ምግቦች (ምሳ እና ቁርስ) በአገራቀፍ ደረጃ ነፃ አይሆኑም። ተማሪዎ በትምህርት ቤት ምሳ መግዛት ከፈለገ፣የMySchoolBucks መለያ ያስፈልጋቸዋል። ለነጻ እና  ቅናሽ ዋጋ ላለው የምግብ አቅርቦት ብቁ ነን ብለው የሚያምኑ ቤተሰቦች እዚህ ማመልከት ይችላሉ።

8. ትምህርት ቤት የተከፈተበት የመጀመሪያ ቀን ክስተቶች/እይታዎች በMCPS ድህረ ገጽ ላይ ይተአያሉ/ይወጣሉ
MCPS ወላጆች የወደዱዋቸውን  የመጀመሪያ ቅን -ይትምህርት ቤት ፎቶዎችን ሰኞ፣ ኦገስት 29፣ 2022 እንዲያቀቡ/እንዲያካፍሉ ይጋብዛል። ከሰኞ ጥዋት ጀምሮ በርካታ ፎቶግራፎች በ ዲስትሪክቱ ድርጣብያና ማህበራዊ ሚድያ ይጋራሉ። ፎቶ በማስገባት፣ ወላጆች በMCPS ድህረ-ገጽ ወይም የማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎች ላይ ለህትመት እንዲውል ተስማምተዋል። ጥያቄ ካለዎት  Department of Public Information and Web Services በስልክ ቁጥር ፡-240-740-2837 ተገናኙ። ወይም በpio@mcpsmd.org ኢ-ሜይል አድርጉልን።

9. ማመልከቻ ለ SMOB አማካሪ ካቢኔ አባላት ክፍት ነው።
አርቪን ኪም፣ 45ኛው የተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል (SMOB)፣ ለተማሪዎች አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ምክረ ሃሳብ ለመለዋወጥ የተማሪ ካቢኔን እያዘጋጀ ነው። የካቢኔ አባላት SMOB የተማሪዎችን ስጋቶች እና ሀሳቦችን እንዲመረምር፣ እምቅ የመመሪያ ግቦችን እንዲወስኑ እና MCPS እና ማህበረሰቡ እንዲገናኙ ያግዛሉ። እዚህ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ እና ያመልክቱ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ  Montgomery County Public Schools 

 




Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools