ሐሙስ፣ ኦገስት 18 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ለሐሙስ ኦገስት 18 ስድስት ጉዳዮችን እነሆ፡ ስለ MCPS ት/ቤቶች መክፈት መመሪያ፣ 2022-2023 ወደ ትምህርት ቤት መመለሻ ትርኢት፣ የት/ቤቶች አውቶቡስ መስመር መረጃ እና ስለ ፀረ ዘረኝነት ኦዲት ዘገባ መረጃን ያካትታል። 

 1. MCPS 2022-2023 የትምህርት ዓመት ዳግም መክፈቻ መመሪያ

  ዛሬ ቀደም ብሎ፣ MCPS ስለመጪው የትምህርት ዘመን የመልሶ መክፈቻ መመሪያ አሠራጭተናል። ኮቪድ-19 በሚመለከት የቅርብ ጊዜውን መመሪያ አካተናል፥ ስለ ስርአተ ትምህርት እና ትምህርት አሰጣጥ፣ ውጤት አሰጣጥ፣ የተማሪዎች፣ የሰራተኞች እና የቤተሰቦች ድጋፎች እና ሌላም ምን እንደሚጠበቅ ይዘረዝራል። ሙሉውን መመሪያ እዚህ ያንብቡ ወይም የመመሪያ ድረ ገጽ ይጎብኙ።

 2. MCPS Back to School Faitአዝናኝ፣ የመረጃ ልውውጥ እና ነፃ ክትባቶች እና የኮቪድ-19 ክትባት ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርኢት፣ ቅዳሜ፣ ነሐሴ 27 ይካሄዳል።

  በ 2022-2023 የትምህርት ዓመት ከ 10 a.m. እስከ 1 p.m. ባለው ጊዜ ውስጥ MCPS ሰራተኞችን እና የማህበረሰብ አጋሮችን ይቀላቀሉ ። ቅዳሜ ነሐሴ 27 በዌስትፊልድ ዊተን የገበያ አዳራሽ። የበለጠ ለማወቅ እና ስለክትባቶች ወይም የክትባት ቀጠሮ ለመያዝ Back-to-school Fair ድረገጽ ይጎብኙ።

 3. 2022–2023 MCPS የት/ቤት አውቶቡስ አገልግሎት መርሃ ግብሮች በኦንላይን አርብ ኦገስት 19 ያገኛሉ።

  2022-2023 የትምህርት ዓመት የአውቶቡስ አገልግሎት መርሃ ግብሮች ዓርብ ኦገስት 19 በኦንላይን ይለጠፋል። አንዳንድ የአውቶቡስ መስመሮች ሊለወጡ ይችላሉ። የትራንስፖርት መምሪያ ሰራተኞች የሁሉም መስመር አገልግሎት የተሸፈነ እና ቀልጣፋ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በትጋት እየሰሩ ነው። ሆኖም አንዳንድ መስመሮች በሠራተኞች ብዛት እና በበርካታ ጥድፊያ ፍላጎት ምክንያት የአገልግሎት መዘግየት ሊያጋጥማቸው ይችላል። የሚዘገዩ እና ያልተሸፈኑ መስመሮችን የሚመለከቱ መረጃዎችን በየእለቱ በት/ቤቶች ይነገራሉ፣ MCPSድረ-ገጽ ላይ ይገኛሉ።

  MCPS እንደሚከተለው ቁርጠኝነቱን ይቀጥላል፦

  1. የልዩ ትምህርት ተማሪዎችን መጓጓዣ ቅድሚያ መስጠት፣
  2. አውቶቡሶችን ለመንዳት ብቃት ያላቸውን የአስተዳደር እና የጥገና ሰራተኞችን ጨምሮ ሁሉንም ያሉትን ሰራተኞች መጠቀም፣
  3. የሰው ሃይል አቅርቦትን ለመጨመር መመልመል፣ ማሰልጠን እና የመቅጠር ጥረታችን ይቀጥላል።
 4. የፀረ-ዘረኝነት ኦዲት ሪፖርት በዚህ ፎል ይደርሳል፣
  የሚታቀዱ የተሳትፎ ክፍለ ጊዜዎች፦

  MCPS የፀረ-ዘረኝነት ስርዓት አቀፍ ኦዲት የመጨረሻ ሪፖርት- ከአትላንቲክ ኤኩቲ ኮንሰርቲየም በዚህ ፎል ይቀበላል። የመጨረሻው ሪፖርት ኦክቶበር 11 ላይ ለህዝብ ይፋ ስለሚሆን ለእያንዳንዱ ስድስት የትኩረት አቅጣጫዎች የጥናት ግኝቶችን ያካትታል። ሁሉም ባለድርሻ አካላት የዳሰሳ ጥናት ግኝቶቹን ለመገምገም እና በዲስትሪክት የድርጊት መርሃ ግብር ላይ ግብአት ለመስጠት እድል እንዲኖራቸው ለማድረግ MCPS ከማህበረሰብ አጋሮች፣ የተማሪ ድርጅቶች እና የሰራተኛ ማህበራት ጋር ይተባበራል። የማህበረሰብ ተሳትፎ ክፍለ ጊዜዎች መርኃ ግብር በሴፕቴምበር ውስጥ ይገለጻል። የዲስትሪክቱ አመራር የመጨረሻ የድርጊት መርሃ ግብር እስከ ጃንዋሪ 31፣ 2023 ይጠናቀቃል።

 5. የተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል አማካሪ የካቢኔ አባላትን ይፈልጋል

  አርቪን ኪም፣ 45ኛው የተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል (SMOB)፣ ለተማሪዎች አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ምክረ ሃሳብ ለመለዋወጥ የተማሪ ካቢኔን እያዘጋጀ ነው። የካቢኔ አባላት SMOB የተማሪዎችን ስጋቶች እና ሀሳቦችን እንዲመረምር፣ እምቅ የመመሪያ ግቦችን እንዲወስኑ እና MCPS እና ማህበረሰቡ እንዲገናኙ ያግዛሉ። እዚህ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ እና ያመልክቱ

 6. በነጻ እና በቅናሽ ዋጋ የምግብ ጥቅሞችን ለማግኘት በኦንላይን አሁን ያመልክቱ

  ለነጻ ወይም ለዋጋ ቅናሽ ብቁ የሆኑ የተማሪ ቤተሰቦች አሁን ለትምህርት ቤት የምግብ እርዳታ ማመልከት ይችላሉ። ብቁነት በቤተሰብ ብዛት እና በጠቅላላ የገቢ መጠን ላይ የተመሰረተ ነው። በሜሪላንድ ውስጥ ለቅናሽ ምግብ ብቁ የሆኑ ተማሪዎች ነጻ የቁርስ እና የምሳ ምግብ ያገኛሉ።

  እዚህ ያመልክቱ።
  ስለ ፕሮግራሙ የበለጠ ይወቁ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public SchoolsEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools