ሐሙስ፣ ኦገስት 11 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ ኦገስት 11 አራት ጉዳዮችን እነሆ!
እነርሱም ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአትሌቲክስ ክፍል የተገኘ መረጃ፣ የነጻ እና የቅናሽ ዋጋ ምግብ መረጃ፣ ስለ ነጻ ክትባቶች እና የበሽታ መከላከያ፣ ከእረፍት መልስ ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ አውደ ርእይ እና ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶችን ያካትታሉ።

 1. ስለ MCPS አትሌቲክስ R.A.I.S.E. ወቅታዊ ጋዜጣ

  ስለ ሁለተኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስፖርት ምዝገባ መረጃ እና የአትሌቲክስ አሰልጣኞች እጥረት እና MCPS ጉዳዩን እንዴት መፍትሔ እየፈለገለት እንዳለ የሚገልጸውን MCPS የአትሌቲክስ ክፍል ወቅታዊ ጋዜጣ ይመልከቱ።
  እዚህ ሙሉ ጋዜጣውን ማንበብ ይችላሉ።

 2. ነጻ የበሽታ መከላከያ ክትባቶች እና የኮቪድ-19 ክትባቶች ቅዳሜ፣ ኦገስት 27 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ አውደ ርእይ ላይ ይሰጣል።

  የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ቅዳሜ፣ ኦገስት 27 ከ10 a.m. እስከ 1 p.m. በዌስትፊልድ ዊተን የገበያ አዳራሽ (Westfield Wheaton mall) በሚደረገው ወደ ት/ቤት የመመለስ አውደ-ርእይ (Back-to-School Fair) ላይ ተገኝተው አዲሱን የትምህርት አመት እንዲያስጀምሩ ተጋብዘዋል።
  ስለ ዝግጅቱ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።
  ለክትባት ወይም ለበሽታ መከላከያ ክትባቶች ቀጠሮ ለመያዝ Back-to-school Fair ድረገጽ ይጎብኙ

 3. lunchበነጻ እና በቅናሽ ዋጋ የምግብ ተጠቃሚ ለመሆን በኦንላይን አሁን ያመልክቱ

  ወላጆች እና አሳዳጊዎች ማመልከቻውን ሞልተው ለትምህርት ቤት ምግብ እርዳታ እንዲያቀርቡ አሁን ክፍት ነው። ለነጻ ወይም ለቅናሽ ዋጋ ምግብ ብቁ የሆኑ የተማሪ ቤተሰቦች ለዚህ አገልግሎት ማመልከት ይችላሉ። ብቁነት በቤተሰብ ብዛት እና በጠቅላላ የገቢ መጠን ላይ የተመሰረተ ነው። በሜሪላንድ ውስጥ ለቅናሽ ዋጋ ምግብ ብቁ የሆኑ ተማሪዎች ከዚህ አመት ጀምሮ ለቁርስ ወይም ለምሳ ምግብ አይከፍሉም።እዚህ ያመልክቱ።
  ስለ ፕሮግራሙ የበለጠ ይወቁ

 4. በሮክቪል እና በጀርመንታወን ስለሚካሄዱት ሌሎች ሁለት ወደ ትምህርት ቤት መመለሻ ሁነቶች ይወቁ

  ኦገስት 20 በኖርዝዌስት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እንቅስቃሴዎችን፣ ጨዋታዎችን እና "spirit wear sales" ሽያጭ የሚካሄድበት ክላስተር አቀፍ ዝግጅት ይስተናገዳል።
   እዚህ የበለጠ ግንዛቤ ማግኘት ይችላሉ።

  ኦገስት 21 የሮክቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሮክቪል ቀንን እና ወደ ትምህርት ቤት መመለሻ እንቅስቃሴዎችን ከማህበረሰብ ድጋፍ ሰጪ አጋሮች  ጋር ያስተናግዳል።
  ስለዚህ ዝግጅት እዚህ የበለጠ ያንብቡ

 5. የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
  Montgomery County Public Schools Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools