ስለ ቨርቹዋል ትምህርት እና የቀለም ኮድ መግለጫ ደብዳቤ

ጥር 2023

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች እና ሰራተኞች

አሁን በክረምቱ የአየር ሁኔታ ወቅት መሀል ላይ ስለገባን፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በከባድ/አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ወቅት የአሠራር ሁኔታን ለውጥ ማድረግ ሲያስፈልግ እና ት/ቤት መዝጋት እና ወደ ቨርቹዋል ማስተማር መሸጋገርን በሚያረጋግጥ ጊዜ ለማህበረሰቡ የማሳወቅ አሠራር ሂደቱን እያሻሻለ ነው። ሁኔታዎች ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች ደህንነት አመቺ እንዳልሆኑ ሲታወቅ፣ ስድስት የክወና ሁኔታዎች አማራጮች አሉን፣ይህም አሁን በቀላሉ ለመረዳት በሚቻል፣
በቀለም በተቀመጠላቸው መልእክቶች ሪፖርት ይደረጋል። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፦

color codes
(View full-sized image)

የተማሪዎች እና የሰራተኞች ደህንነት ተቀዳሚ ትኩረታችን ሆኖ ይቆያል፣ MCPS እነዚህ ሁኔታዎች ለቤተሰቦች እና ለሰራተኞች ሊያስከትሉ የሚችሉትን ችግር ይገነዘባል። በድንገተኛ የአየር ሁኔታዎች ምክንያት የአሠራር ለውጦችን ማድረግ አስፈላጊ የሚሆነው በጥንቃቄ ከተገመገመ በኋላ ብቻ ነው።

ውሳኔ በሚሰጥበት ጊዜ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አመራር ከሀገር አቀፍ እና ከአካባቢ የአየር ሁኔታ ባለሙያዎች፣ ከአካባቢው የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር ባለስልጣናት፣ እና ሌሎች የመንግስት እና የአጎራባች ትምህርት ቤቶች ዲስትሪክቶችን የስራ ሁኔታ ይገመግማል። በተጨማሪም አመራሩ ከስቴት ሀይዌይ አስተዳዳሪዎች መረጃን ይሰበስባል፣ የመንገዶችን፣ የእግረኛ መንገዶችን፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን እና የት/ቤት አውቶቡስ መጓጓዣ መስመሮችን ሁኔታ በሠራተኞቹ አማካይነት በመመርመር አስፈላጊነቱ ሲረጋገጥ ብቻ ውሳኔ ይሰጣል።

ቨርቹወል ትምህርት-Virtual Learning
ወደ ቨርቹዋል ትምህርት መሸጋገሩን የሚያመለክተው ሐምራዊ ኮድ በከባድ የአየር ሁኔታ ጊዜ መማር እና ማስተማር እንደሚቀጥል ያረጋግጣል። የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት ይህንን እድል ለአካባቢው ትምህርት ቤቶች ያቀረበ ከመሆኑም በላይ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ጃንዋሪ 12 በተካሄደው ቨርቹዋል የስራ ስብሰባ ላይ እቅዱን አጽድቋል። ያለው ቴክኖሎጂ እና የቀድሞው ቨርቹዋል የመማር ማስተማር ልምድ MCPS በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ እና በድንገተኛ ጊዜም ቢሆን ከተማሪዎች ጋር መስራቱን እንዲቀጥል ያስችለዋል። ሰራተኞች እና ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ዝግጁ እንዲሆኑ አስፈላጊ መመሪያዎች አሉ። እነዚህ መመሪያዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ተጽዕኖ የሚያሳድረውን ክስተት መተንበይ ይቻላል?
  • ተጽዕኖ የሚያሳድረው ክስተት (እንደ አውሎ ንፋስ የመሣሰለ) የበርካታ ቀናት ሁኔታ አካል ነው? ወይስ የአንድ ቀን ክስተት ብቻ ነው?
  • ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እና ከቤተሰቦች፣ተማሪዎች እና ሰራተኞች ጋር መገናኘት ይቻላል?
    ግንኙነት
    ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ቤተሰቦች በቀላሉ መሸጋገር እንዲችሉ ግንኙነት ወሳኝ ነው። ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች እና ሰራተኞች እንዲያውቁ MCPS እነዚህን ደረጃዎች ይከተላል፦
  • "ተዘጋጁ" ማስታወቂያ (ከባድ የአየር ሁኔታ ይከሰታል ማለት ነው) በዲስትሪክቱ ዙሪያ ይደረጋል።
  • ከማንኛውም የአየር ሁኔታ አንድ ቀን በፊት እኩለ ቀን ላይ ቨርቹዋል ትምህርት ስለማቅረብ ውሳኔ ይደረጋል።
  • ስለ ቨርቹዋል ትምህርት ስለሚጀመርበት ጊዜ ለማስታወስ የተማሪ ደህንነት ቡድኖች የተለዩ ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን ያነጋግራሉ።
  • ትምህርት ቤቶች የሚያስፈልግ የትምህርት ቀን መሆኑን እና ወደ ክፍል እንዴት እንደሚገቡ እንዲያስታውሷቸው ለቤተሰቦች መልእክት ይልካሉ።

የአየሩ ሁኔታ አሳሳቢ በሚሆንበት ጊዜ፣ MCPS በጊዜው እና በትክክለኛ መረጃ ወቅታዊ መረጃዎችን ማግኘትዎን ለማረጋገጥ ጥረት ያደርጋል። እባክዎ ከአየር ሁኔታ ጋር የተገናኙ የት/ቤቶች ዘግይቶ መከፈት፣ የት/ቤቶች መዘጋት እና ተማሪዎችን ቀደም ብሎ ማሰናበት የመሳሰሉትን መከታተል እና የተማሪዎቻችንን እና የሰራተኞቻችንን ደህንነት ለማረጋገጥ በምንሰራበት ጊዜ ከትምህርት ቤት ሰራተኞች ጋር መተባበርዎን ያረጋግጡ።

ParentVUE አካውንትዎን አዘውትረው ይመልከቱ፥ እና አስፈላጊ ከሆነ እርስዎ የሚገኙበትን መረጃዎን ያዘምኑ። ይህ ሁሉንም አስፈላጊ የትምህርት ቤት የስራ ሁኔታ ወቅታዊ መረጃዎችን እንደሚያገኙ ያረጋግጣል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools 

ስለ ቨርቹዋልትምህርት ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል
ስለ ቀለም ኮዶች ተጨማሪ መረጃ እዚህይገኛል



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools