እንኳን ደህና መጣችሁ፣ እና መልካም አዲስ ዓመት!

ጃኑዋሪ 2, 2023

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

እርስዎ እና ቤተሰቦችዎ በዚህ ሞቃታማ እና ፀሐያማ አዲስ አመት እየተደሰታችሁ እንደሆነ እና በክረምቱ የዕረፍት ጊዜ ዘና ለማለት እና ለማሰላሰል እድል እንዳገኛችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። 2023 የእኔ የግል ፅናትና ውሳኔ ለተማሪዎቻችን እና የወደፊት ማህበረሰባችን በማገልገል አብረን የምንሰራውን ስራ አስፈላጊነት በቀጣይነት ማከናወን ነው።

ከክረምት ዕረፍት በፊት በተላከው መልእክት፣ የመተንፈሻ አካላት በሽታ (ኢንፍሉዌንዛ፣ RSV እና ኮቪድ-19) በህብረተሰባችን ውስጥ ሲሰራጭ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅእኖ በንቃት እንዲከታተሉ እና እንዲያውቁ አሳስበናል። እነዚህ በሽታዎች ከበዓል ሰሞን በኋላ በመላው ክልላችን ለአካባቢያችን የጤና አጠባበቅ አገልግሎት መስጫዎቻችን ላይ ከፍተኛ ጫና ሊፈጥሩ ይችላሉ። ከክረምት ዕረፍት በኋላ ባሉት የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት በት/ቤት ስራዎች ላይ ያለውን ጫና እና የሚያስከትለውን ተጽእኖ ለመቀነስ የሁሉንም ሰው እርዳታ እንፈልጋለን። ያስታውሱ፣ የመከላከያ እርምጃዎች አሁንም ይተገበራሉ - እነዚህም ክትባቶችን መከታተል፣ የበሽታ ስርጭትን ለመከላከል ጤናማ የተላላፊ በሽታ መከላከል እርምጃዎችን መውሰድ እና ከታመሙ ቤት ውስጥ መቆየት ያስፈልጋል።

ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ እና ማክሰኞ ጃንዋሪ 3 ትምህርት ለመቀጠል ጉጉት ቢኖረንም፣ ይህንን ማድረግ የምንችለው እራሳችንን እና የሌሎችንም ጤንነት ጭምር ስንከባከብ ብቻ ነው።

ከዋና ኦፕሬቲንግ ኦፊሰራችን በተላለፈው መልዕክት ላይ እንደተገለጸው፣ በህመም ምክንያት ሥራ ለመገኘት እንደማይችሉ ለመግለጽ ከሰራተኞች የሚደርሱን ጥሪዎች የሚያስከትሉት ተጽእኖዎች በት/ቤት አውቶቡስ የመጓጓዣ መስመሮች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ፥ ወይም አንዳንድ የትምህርት ክፍሎችን በተተኪ አስተማሪዎች መሸፈን ይኖርብናል ማለት ነው። ወቅታዊ መረጃዎችን ማስተላለፋችንን እና ማናቸውንም ለውጦችን በተመለከተ መግለጻችንን እንቀጥላለን፤ እንደአስፈላጊነቱ ConnectED፣ በማህበራዊ ሚዲያ እና MCPS በይነመረብ ላይ እናቀርባለን። እንዲሁም የት/ቤት አውቶቡስ አገልግሎት ዳሽቦርድ (የመረጃ ቋት) በማናቸውም መዘግየት ወይም ስረዛ ከተደረገ በየቀኑ ጥዋት እና ቀኑን ሙሉ ወቅታዊ መረጃ ይሰጣል።

አሁንም፥ ወደ ፊታችን ስንመለከት የትምህርት አመታችንን በጀመርንበት መነቃቃት እንቀጥላለን፥ ማለትም “አሁን ሁላችን በአንድ ላይ" ተግዳሮቶቻችንን ተቋቁመን እንደማህበረሰብ በጥልቅ ትብብር እና አብሮነት እናድጋለን። ይህንኑ መሠረተሃሳብ እንደምትጋሩ እተማመናለሁ።

ዓመቱን ሙሉ፣ በሁሉም የትምህርት ቤት ጉብኝቶቼ ብሩህ ተስፋን፣ አልበገሬነት እና ጽናትን ተመልክቻለሁ። ሰራተኞች እና ተማሪዎች ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ ጓጉተዋል፣ እና በጥሩ ሁኔታ ወደዛ በመመለስ ላይ ነን። አዲስ ደስታ እና መነቃቃት ስላለ ይህን በማየቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ለምትኖሩ ሁሉ ለእያንዳንዳችሁ "መልካም አዲስ ዓመት" እና ለቀሪው የትምህርት ዓመት መልካም ምኞቴን ልገልጽላችሁ እወዳለሁ።

ከመልካም ወዳጅነት ጋር

Dr. Monifa B. McKnight
Superintendent of SchoolsEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools