ሐሙስ፣ ጁን 2 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ ጁን 2 አምስት ጉዳዮችን እነሆ!
የተማሪዎች ምረቃ በዓላት፣ ስለ ኮቪድ-19 ማሳሰቢያ፣ ነፃ የክትባት ክሊኒኮች እና ሌሎችንም ያካትታሉ።

 1. graduationየተማሪዎች ምረቃ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ነው
  ትናንት ጁን 1 በጀመረውና እስከ ጁን 14 ድረስ በሚካሄደው የተማሪዎች ምረቃ ከ11,000 በላይ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎች ዲፕሎማ መቀበል ጀምረዋል።
  የበለጠ ለማወቅ
  የእንግሊዝኛ ቪዲዮ እዚህ ይመልከቱ (ቪዲዮ በስፓኒሽኛ)
  የፎተግራፎች ክምችት ይመልከቱ
 2. አሁንም የኮቪድ-19 ክትባት ይፈልጋሉ? ቡስተር ይፈልጋሉ? ክትባት በነፃ ይሰጣል!
  የኮቪድ-19 ክትባት እና ቡስተር መውሰድ በቫይረሱ እንዳይታመሙ በጣም አስተማማኝ እና የተሻለ አማራጭ ነው። MCPS ከጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት ጋር በመተባበር ጎልማሶች ወይም ልጆች ክትባቱን እንዲወስዱ እና/ወይም ወቅታዊ መረጃ ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ ብዙ እድሎችን ለመስጠት እየሰራ ነው። ይህ ጥረት እርስዎን እና በዙሪያዎ ያሉትን ሰዎች ሁሉ ደህንነት ለመጠበቅ ይረዳል!
  እዚህ ክሊኒክ ይፈልጉ እና ክትባት ይውሰዱ።
 3. በሞንትጎመሪ ካውንቲ የኮቪድ-19 ፖዚቲቭ ሁኔታዎች አሁንም ከፍተኛ ናቸው።
  የ 2021-2022 የትምህርት ዓመት ወደ ማጠናቀቂያው እየተቃረብን ቢሆንም በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ ፖዚቲቭ የኮቪድ-19 ሁኔታዎች ከፍተኛ ናቸው። በሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና ጥበቃ እና ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት የመረጃ ሠሌዳ/ዳሽቦርድ ላይ ያሉትን ቁጥሮች ማየት ይችላሉ።
  ማህበረሰባችን በ"መካከለኛ" የአደጋ ምልክት ምድብ ውስጥ ይገኛል። የጤና ጥበቃ እና ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት ጭምብል እንዲጠቀሙ፣ የበሽታ ምልክቶች ሲታዩዎት እንዲመረመሩ፣ የእጅ ጀርም ማጽጃ እንዲጠቀሙ/እጅዎን መታጠብ እና በተቻለ መጠን አካላዊ ርቀትን እንዲጠብቁ በጥብቅ ያበረታታል።
  1. በኮቪድ-19 መያዝዎን ካረጋገጡ፣ እባክዎን በ Google ሪፖርት ማድረጊያ ቅጽ ለትምህርት ስርዓቱ ሪፖርት ያድርጉ።
  2. ራስን የማግለለ መመሪያዎችን ወዲያውኑ ተግባራዊ ያድርጉ።
   ራስን የማግለል መመሪያዎችን እዚህ ይመልከቱ፡-
 1. MCPS ስለ ትምህርት ቤቶች ደህንነት ያለውን ጠንካራ ቁርጠኝነት ይቀጥላል
  ጊዜያዊ ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒት ሰኞ፣ ሜይ 30 ለህብረተሰቡ የሚከተለውን መልእክት አስተላልፈዋል። መልእክቱ ስለ ት/ቤቶች ደህንነት ዲስትሪክቱ (MCPS) ያለውን ቁርጠኝነት፣ ከካውንቲ ፖሊስ ጋር ያለውን ጠቃሚ ትብብር እና ለሰራተኞች ስልጠናን ጭምር ይገልጻል።
  መልእክቱ እዚህ ይገኛል
  ቪዲዮ፡ ስለ ትምህርት ቤቶች ደህንነት የተደረገ ውይይት ይመልከቱ
 2. የአእምሮ ጤንነት እና ደህንነት መርጃዎችን በኦንላይን ያግኙ
  MCPS ከ160,000 ለሚበልጡ ተማሪዎቹ እና 24,000 ሰራተኞቹ አካላዊ፣ ማህበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ደህንነት ቁርጠኛ ነው። በ MCPS ዋናው ደረገጽ ላይ ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች እና ለቤተሰቦች ጠቃሚ የዲስትሪክት አቀፍ መረጃ እና የማህበረሰብ ሪሶርሶችን ማግኘት ይችላሉ።
  ብሔራዊ የአእምሮ ጤና ተቋም እነዚህን ቀላል ምክሮች ይሰጣል።
  1. MCPS ዋናው የበይነመረብ ገጽ
  2. MCPS በትምህርት ቤቶች የሚገኙ የአእምሮ ጤንነት እና ደህንነት መርጃ ሪሶርሶች

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools