ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ዛሬ ይህንን ስጽፍ በኡቫልዴ ቴክሳስ በሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተፈፀመው አሰቃቂ የትምህርት ቤት ተኩስ እያዘንኩ ነው። ሁላችንም የሚወቸውን ዘመዶቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች እና የዚህ አሰቃቂ ክስተት ሃዘንተኛ ሆነው ለሚቀጥሉት ማህበረሰብ ጥልቅ የሆነ ርህራሄ ማሰማታችንን እንቀጥላለን።

ታጣቂው እንዴት ወደ ትምህርት ቤት እንደገባ እና የፖሊስ ምላሽን በተመለከተ እየወጡ ያሉት ዝርዝሮች በመላ ሀገሪቱ ስለትምህርት ቤት ደህንነት ጥያቄዎችን አስነስተዋል። በዚህ ጊዜ ሁሉም እውነታዎች አይታወቁም ነገር ግን ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ከእንደነዚህ እይነት ጥቃቶች ለመዘጋጀት በMCPS ውስጥ የምናደርገውን ላካፍላችሁ እፈልጋለሁ። ዝግጁነታችን በአራት ቁልፍ ቦታዎች ላይ የተመሰረተ ነው።

  1. ከክልሉ ፖሊስ እና የደንብ አስከባሪ  ጋር ያለን ትብብር
  2. የፖሊስ እና የMCPS ሰራተኞች ስልጠና
  3. የትምህርት ቤትአካላዊ  ደህንነት
  4. የማህበረሰብ  የደህንነት ቁርጠኝነት

ከክልሉ ፖሊስ ጋር ያለን ትብብር
ሰራተኞችን እና ተማሪዎችን ለሚያስፈራ ማንኛውም ክስተት ምላሽ ለመስጠት የድንገተኛ ተኳሽን ጨምሮ ዝግጁ ለመሆን ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት እና በካውንቲው ውስጥ ካሉ ሁሉም የፖሊስ ኤጀንሲዎች ጋር በቀጣይነት እንተባበራለን። ለትምህርት ቤታችን የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰሮች አዲሱ ስምምነት ለዚህ ጠንካራ አጋርነት ጥሩ ምሳሌ ነው።

በአሁኑ ጊዜ በቴክሳስ ትምህርት ቤት ተኩስ ላይ በነበረበት ወቅት ፖሊስ ስለሰጠው ምላሽ እና በተለይም ወደ ክፍል ውስጥ ለመግባት ወስዷል የተባለውን ጊዜ አስመልክቶ እየተጠየቁ ያሉት ጥያቄዎች ከፖሊስ አጋሮቻችን ጋር እንድንነጋገር አስገድዶናል። ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ጋር የድንገተኛ ተኩስ ከፋች አደጋ ፖሊሲያቸው እና ስልጠናቸው የመጀመሪያው ምላሽ ሰጪ መኮንን(ዎች) ህይወትን ለመጠበቅ ወዲያው እንደሚንቀሳቀሱ አረጋግጠናል። ይህ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ በማንኛውም ትምህርት ቤት ውስጥም ሆነ ውጭ በማንኛውም ተማሪ ወይም ሰራተኛ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት የሚያሳዩ ተጠርጣሪዎችን በንቃት በማሳተፍ ነው።

የፖሊስ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ስራተኞች ስልጠና
ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት ጋር ባለን ትብብር ትምህርት ቤቶች ውስጥ በድንገት ለሚከሰቱ የጅምላ ተኩስ የሚያዘጋጁ ስልጠና/ ልምምዶችን መስራታችንን እንቀጥላለን። የት/ቤታችን ካምፓሶች እንደ የአትሌቲክስ ስታዲየም እና ወደ ሌላ ቦታ መዛወር የሚችሉ ክፍሎች እንዳሉት በመረዳት አሁን በየተኛውም የትም/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ለድንገተኛ አደጋ ለመዘጋጀት የስልጠና ልምዶቻችንን እያሳደግን ነው።

ለMCPS የደህንነት ሰራተኞች እንደ ድንገተኛ ተኳሽ ለመሳሰሉት የአደጋ ጊዜ ሁኔታዎች ምላሽ መስጠት ላይ የሚያተኩር ተጨማሪ ስልጠና በዚህ ክረምት እንሰጣለን። ይህ ስልጠና በየካቲት 10 በወጣው የተማሪዎች ጤንነት እና ድህንነት ዘገባ ላይ ተካትዋል ሁሉም የሰራተኞች ስልጠና በችግር ጊዜ ምላሽ መሰጠትን ብቻ ሳይሆን አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት ለማስወገድ የግንዛቤ ማስጨበጫ እርምጃዎችን ይሸፍናል።

እካላዊ ደህንነት
ግልጽ ልሁን; በሞንቶጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቤቶች የሚጠበቀው ነገር ሁሉም የውጪ በሮች ሁል ጊዜ መቆለፍ አለባቸው። አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶቻችን የትኛውም ጎብኚ ወደ ህንጻው መግባት ያለበት የጥበቃ ቬስቲቡል እንዳላቸው መረዳት ያስፈልጋል። ጎብኚዎች አንድ ቁልፍ ተጭነው በደህንነት ካሜራ ላይ መታየት አለባቸው እናም ሰራተኛ ወደ ትምህርት ቤቱ የመጡበትን አላማ እስኪጠይቃቸው ድረስ መግባት አይችሉም። ከገቡ በኋላ በትምህርት ቤቱ ዋና ቢሮ በኩል ሄደው የመግባት ሂደቱን በጎብኚዎች አስተዳደር ስርዓታችን/መመዝገቢያ ማጠናቀቅ አለባቸው።

እጅግ በጣም ትንሽ ለሆኑት የደህንነት መፈተሻዎች ላልተጫኑላቸው ትምህርት ቤቶች አሁንም የሚቆለፍ የውጪ በር እና በጎብኚ አስተዳደር/መመዝገቢያ ስርዓት የመግባት መስፈርት አለ። በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ወይም ብዙ ቁጥር ያላቸው መዛወር የሚችሉ የመማሪያ ክፍሎች ባሉበት ትምህርት ቤት የተሻሻለ የደህንነት ፍተሻ እንዲኖረን ሂደቶቻችንን እያስተካከልን ነው።

ለደህንነት የማህበረሰብ ቁርጠኝነት
ደህንነቱ የተጠበቀ ትምህርት ቤት አካባቢ MCPS ሁልጊዜም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።  በአካል እና በስሜታዊነት ተማሪዎች እና ሰራተኞች በከፍተኛ ደረጃ ማስተማር እና መማር እንዲችሉ ደህንነት እና እንክብካቤ ሊሰማቸው ይገባል። የመቆለፍ፣ የመጠለያ ቦታ እና የመልቀቂያ ሂደታችንን በመለማመድ በትምህርት ዓመቱ ለአደጋ ሰአት ዝግጁነት እናሠለጥናለን። በMCPS ህንፃ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው በሮችን መቆለፍ፣ መጋረጃዎችን መዝጋት፣ ጸጥ ማለት እና የአስተዳዳሪዎችን መመሪያ መከተል ያውቃል። በችግር ጊዜ ሁላችንም ለመከላከል እና ለማስወገድ ያለንን ሚና ማወቅ አስፈላጊ ነው። ይህ ማለት ስልጠና እና ዝግጁ መሆ: የደህንነት ሂደቶችን መከተል ድንገተኛ ወይም በአደጋ ጊዜ የሁላችንም ደህንነትን ለመጠበቅ ይረዳል።

“የሆነ ነገር ካየህ የሆነ ነገር ተናገር” የሚለውን ሀረግ በመከተል ቀውሶችን እናስወግዳለን። ይህ ማለት ለታመነ አዋቂ መንገር፣ አጠራጣሪ ነገር ካዩ ወይም በአካልም ሆነ በድህረመረብ ላይ ስጋት እንዳለ ካወቁ ለአስተዳዳሪዎች ወይም ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ማለት ነው። የፖሊስ አጋሮቻችን እነዚህን የተጠረጠሩ ስጋቶች ለመመርመር እና እውነት መሆናቸውን ለመወሰን ክህሎት እና ስልጠና አላቸው። በዚህ ውስጥ፣ እርስ በርሳችን ደህንነታችንን እንጠብቃለን ፡እናም ትምህርት ቤቶቻችንን በኡቫልዴ ቴክሳስ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ካሳደረው ጥቃት አይነት ነፃ እናደርጋለን።

ዛሬ ባለው ህብረተሰብ ውስጥ ብጥብጥ/ነውጥ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ጭምር ይበልጥ እየተደጋገመ የመጣ ክስተት ሲሆን   ነገር ግን እኔ እና በMCPS ውስጥ ላሉ ሰዎች ሁሉ ደህንነት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንደምናስብ እንድትረዱልኝ እፈልጋለሁ። ለቀጣይ ዝግጁነት እና ደህንነትን ለመጠበቅ የምናደርገውን ሁሉ ለመገምገም ቃል ገብተናል። ከእርስዎ አጋርነት ጋር፣ የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ እንሆናለን።

ከአክብሮት ጋር

ሞኒፋ ቢ. ማክነይት ዶ/ር
ተጠባባቂ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት

 

 



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools