MCPS በቴክሳስ ትምህርት ቤት በደረሰው የህይወት መጥፋት አዝኗል

በትምህርት ቤቶቻችን አስተማማኝ አካባቢን ለመፍጠር ቃል ገብቷል

May 25, 2022

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

በኡቫልዴ፣ ቴክሳስ ውስጥ በደረሰው አሰቃቂ አደጋ እኛ በMCPS እና መላው የሞንትጎመሪ ካውንቲ ማህበረሰብ ልባችን ተሰብሮአል። ሁላችንም በጋራ ለሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቤተሰቦች እና ማህበረሰብ ጥልቅ ሀዘናችንን እንገልፃለን። ወደ ስራ እና ትምህርት ቤት ስንጓዝ እና የእለት ተእለት ህይወታችንን ስንመራ ስለራሳችን ደህንነት እና የምንወዳቸው ዘመዶቻችን ደህንነት ጥያቄዎችን እና ስጋቶችን በሚያመነጨው በዚህ ሁከት ሁላችንም ተከፍተናል። እውነታው ግን ሁላችንም ነቅተን መጠበቅ እና ተማሪዎቻችንን እና ሰራተኞቻችንን ለመጠበቅ የተቻለንን ሁሉ ለማድረግ በጋራ መስራት አለብን። አስተማማኝ ጤንነት/ደህንነት ለእኛ የቅድሚያ ትኩረታችን ነው።

አካላዊ ደህንነት
በየቀኑ፣ ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ ለማመቻቸት በMCPS የት/ቤት ደህንነት እና ድንገተኛ አስተዳደር መምሪያ እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት ከአጋሮቻችን ጋር እንሰራለን። በደንብ የሰለጠኑ የትምህርት ቤት ሰራተኞች እና የደህንነት አባላት፣ የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰሮች እና የፖሊስ አጋሮች፣ የትምህርት ቤታችን አካባቢ ለመማር እና ማስተማር ምቹ እና ጤናማ ቦታ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ሁሉም ሰው የሚከተለውን እንዲያደርግ እናሳስባለን:

  • ተማሪዎች ስለዚህ አደጋ ሊሰማቸው የሚችለውን ፍርሃት፣ ቁጣ እና ግራ መጋባት ስሜትን መቀበል
  • ከእርስዎ ወይም በትምህርት ቤቱ ውስጥ ካሉ ሌሎች ታማኝ አዋቂዎች እርዳታ እንዲጠይቁ ማበረታታት; እና
  • ማንኛውንም አጠራጣሪ ባህሪ ወይም እንቅስቃሴ ለትምህርት ቤት ወይም ለፖሊስ ያሳውቁ

MCPS ከአካባቢው አጋሮች ጋር ከማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰሮች ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር የታደሰ ስምምነት አለው ይህም የትምህርት ቤታችንን ህንፃዎች አካላዊ ደህንነትን ለማረጋገጥ ትልቅ እርምጃ ነው።
የአእምሮ ጤና እና ደህንነት ደህንነት
አንዳችን ሌላውን ለመጠበቅ የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ በጋራ ስንሰራ ጥንካሬ እና እንክብካቤ ማሳየት አለብን። ከልጅዎ ጋር ስለ አመጽ/ረብሻ ለመነጋገር ጠቃሚ ምክሮችን የሚሰጡ በርካታ ምንጮች ከዚህ በታች አሉ። MCPS ተማሪዎች የሚያምኑትን  ትልቅ ሰው  እርዳታ እንዲጠይቁ ያበረታታል። እነዚህ በትምህርት ቤት ላይ የተመሰረቱ የአእምሮ ጤና እና የምክር አገልግሎቶች ለተማሪዎች ሁልጊዜ ይገኛሉ።

ጠቃሚ መረጃዎች

MCPS

ድጋፍ ለመጠየቅ ጠቃሚ የስልክ መስመሮች

  • የሞንቶጎመሪይ ካውንቲ የችግር ጊዜ አስቸኳይ መስመር —240-777-4000
  • የሜሪላንድ ደህንነት ትምህርት ቤቶች ጠቃሚ ምክር መስመር—833-MD-B-SaFE
  • የሞንቶጎመሪይ ካውንቲ የችግር ጊዜ ቁጥር —240-777-4000

 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools 



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools