ሀሙስ ሜይ 12 ማወቅ ያለብዎት አምስት ጉዳዮችን እነሆ! ስለ ኮቪድ-19 ማሳሰቢያ፣ የኦንላይን ስለ አእምሮ ጤንነት እና ደህንነት መርጃዎች፣ ስለመጪው LGBTQ+ town hall እና ስለ ሠመር ፕሮግራም ምዝገባ መረጃዎችን ያካትታል።
ኮቪድ-19 አሁንም ስላለ ስለዚህ እንጠንቀቅ
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ፖዚቲቭ የኮቪድ-19 ህሙማን ቁጥር እየጨመረ ቢሆንም፣ በበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (CDC) መሥፈርት መሠረት በእኛ ማህበረሰብ ላይ ያለው ተጽእኖ “ዝቅተኛ” እንደሚሆን ይጠበቃል። ይሁን እንጂ ነቅቶ መጠበቅ እና የቫይረሱን ስርጭት የሚቀንሱ ጠቃሚ መከላከያዎችን መጠቀም አስፈላጊ ነው። ውጭ ከሰዎች ጋር በሚሆኑበት ጊዜ ማስክዎን መጠቀም ይኖርብዎታል፣ ከብዙ ሰው ጋር እንዳይሰበሰቡ፣ በሚችሉበት ጊዜ ሁሉ አካላዊ ርቀት ይጠብቁ፣ እጅዎን ደጋግመው ይታጠቡ እና ክትባት እና ቡስተሮችን ተከታትለው እንዲወስዱ በጥብቅ ይመከራል። እነዚህን ቀላል ነገሮች ማድረግ ጤናማ እንዲሆኑ ያግዛል እንዲሁም በትምህርት ቤቶቻችን የኮቪድ-19 ተፅእኖ ለመቀነስ ይረዳል።
ዝርዝሩን በሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት የመረጃ ሠሌዳ እና MCPS የመረጃ ሠሌዳ ላይ ማየት ይችላሉ።
ሶስት ወይም ከዚያ በላይ ፖዚቲቭ ኬዞች/በበሽታው የተያዙ ሰዎች ባሉባቸው ቦታዎች ጭምብል መጠቀም ጠቃሚ ነው።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት ምክሮች ጋር በሚስማማ መልኩ፣ MCPS በተወሰኑ ክፍሎች ወይም ትምህርት ቤቶች ላይ ያተኮረ አብዛኛውን ጊዜ በክፍሉ ውስጥ ሶስት ወይም ከዚያ በላይ የኮቪድ-19 ኬዞች ካሉ ጭንብል መጠቀምን ተግባራዊ አድርጓል።
ከቤተሰብ ጋር ለመነጋገር፣ ስለ ጭንብል አጠቃቀም ምክርን የሚያካትቱ ፖዚቲቭ ኬዞችን የሚመለከቱ ደብዳቤዎች እንደ አስፈላጊነቱ ወደ ቤት ይላካሉ። የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ጭምብል መጠቀም አስፈላጊ ነው። MCPS በተጨማሪ ወደ ቤት የሚወሰዱ ፈጣን መመርመሪያዎችን እና ጭንብል የኮቪድ ተጽእኖ ወዳለባቸው ትምህርት ቤቶች እያሠራጨ ነው። ከሜሪላንድ የጤና ጥበቃ ዲፓርትመንት እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት CDC በተሰጠው መመሪያ መሠረት ክትባት እና ቡስተር ተከታትለው ያልወሰዱ ተማሪዎች እና ሠራተኞች ራሳቸውን ማግለል ሊያስፈልጋቸው ይችላል።
ማሳሰቢያ፡ ማንኛውንም ፖዚቲቭ የኮቪድ-19 ሁኔታ በዚህ አገናኝ/ሊንክ ሪፖርት ያድርጉ።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org