የተወደዳችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰቦች

የትምህርት አመቱ ሊያጠናቅቅ ስንቃረብ፣ በዚህ አመት የተማርኩትን የትምህርት ሥርዓታችን በሙሉ አቅም እና በከፍተኛ ደረጃ ምርጥ አገልግልት መስጠት የሚችልበትን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ተማሪዎቻችንን፣ሰራተኞቻችንን፣ቤተሰቦችን እና ማህበረሰቡን እንዴት በተሻለ ሁኔታ መደገፍ እንዳለብን እያሰላሰልኩ ቆይቻለሁ።

ይህ ጊዜ ውጤታማና ፍሬያማ ነበር። በትምህርት ቤት ስርዓታችን እና በመላው ማህበረሰባችን ውስጥ ካሉ አጋሮች ጋር በመተባበር ጥንካሬያችንን፣ ፍላጎቶቻችንን እና የአፈጻጸም ደረጃዎችን እየገመገምኩ ቆይቻለሁ። በመጨረሻም ጥሩ እየሰራ ያለውን ማስቀጠል እና የት ጋ ማሻሻል እንደምንችል መገምገም በጊዜያዊ ሱፐር ኢንተንደንትነት ሚናዬ ማከናወን ያለብኝ ቁርጠኝነት ሲሆን ይህም በኃላፊነት ዘመኔ ሁሉ የሚቀጥል ነው።

ከወላጆች እና ተማሪዎች ጋር ያደረግናቸው ግልጽ እና ጠንካራ ውይይቶች አስደስተውኛል። በሙያው ውስጥ ካሉ ምርጥ ሰዎች ለመማር ከመላው ሀገሪቱ ከተውጣጡ ስኬታማ የትምህርት ቤት መሪዎችም ጋር ተከታታይ ውይይቶችን አድርጌያለሁ። አዳምጫለሁ–በእርግጥ አዳምጫለሁ– ወደ ስኬታማነት የሚያደርሱ የአሠራር ስርዓቶችን እና አወቃቀሮችን እንዴት መገንባት እንደምንችል የመረዳት ቁርጠኝነቴ አካል በመሆኑ

Student Member of the Board of Education
Newsletter

እነዚህ ውይይቶች የት/ቤት ስርዓታችንን ማደራጀት እንዳለብን ይበልጥ እርግጠኛ አድርጎኛል፣ እምነትን ለመፍጠር ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የተማሪዎችን ጤንነት እና ደህንነት ማረጋገጥ፣ እና ፍትሃዊ በሆነ መማር ማስተማር ላይ ማተኮር ትኩረታችንን በሦስቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ እንድናደርግ አስገንዝቦኛል።

Student Member of the Board of Education
Newsletter

ከተካሄዱት ውይይቶች በተማርኩት ለብዙዎቻችሁ ምስጋና ይግባውና - አሁን ባለው የአመራር መዋቅር ላይ አንዳንድ ስልታዊ ማሻሻያዎችን እየተመለከትን ነው። ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር ለማስማማት፣ ወደምንፈልግበት ቦታ ጠለቅ ብለን እንድንገባ እና እንድናዳብር፣ የተማሪ የአእምሮ ጤንነት መጠበቅን የመሣሰሉ ከፍተኛ ፍላጎት ላላቸው ነፃ ሪሶርሶችን ለማቅረብ በቅልጥፍና መሥራት እንዳለብን ተገንዝቤአለሁ።

https://ww2.montgomeryschoolsmd.org/departments/publicinfo/community/school-year-2021-2022/Community-Update-20220502.html

በ MCPS የበጀት ዓመት FY2023 ስልታዊ ድርጅታዊ አመራር መዋቅር ላይ አንዳንድ ጠቃሚ ለውጦች ተዘርዝረዋል። በፍትሃዊ የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ያለንን ትኩረት ለማሻሻል ምክትል ሱፐር ኢንቴንደንት እና ዋና የአካዳሚክ ኦፊሰር እንጨምራለን። አዲሱ የኮሚዩኒኬሽን ረዳት ዋና ኃላፊ እና ከፍተኛ የማህበረሰብ አማካሪዎች መተማመንን እንደገና በመገንባት እና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ላይ ያተኩራሉ። የልዩ ትምህርት አገልግሎት ከሚያገኙ ተማሪዎች ወላጆች ጋር ባደረግነው ውይይት መሠረት ከቤተሰቦች ጋር በንቃት ለመገናኘት እና ት/ቤቶች የልዩ ትምህርት ግብዓቶችን ለማግኘት የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎች ለማስወገድ የልዩ ትምህርት አገናኝ ይቀጠራል። ዋና የኦፕሬቲንግ ኦፊሰራችን፣ በፋይናንስ ጉዳይ ላይ እውቀት ያለው፣ ትምህርት ቤቶቻችን፣ ተማሪዎቻችን እና ሰራተኞቻችን የሚያስፈልጋቸውን ነገር እንዲያገኙ ፍትሃዊ የሪሶርስ ክፍፍልን ይቆጣጠራል/ትቆጣጠራለች። በመጨረሻም፣ ባለፈው የፎል ወቅት አወዳድረን ያገኘነው እና በቅርቡ የቀጠርነው የጤና መኮንን ለተማሪዎች ጤንነት እና ደህንነት ባለን ቁርጠኝነት ላይ ሙያዊ እውቀትን ይተገብራል።

በእነዚህ አዳዲስ የስራ መደቦች አማካይነት የተለያዩ እና ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች ቀድሞ ያገለግሉ በነበሩት ጠንካራ ቡድኖች ላይ ይጨመራሉ፣ የወደፊት እድሎችን ለመጠቀም የእድገት ቦታዎችን ይፈጥራሉ፣ እና መጪዎቹን ተግዳሮቶችም ይቋቋማሉ። ለውጦቹ ለተማሪዎቻችን እና ለዲስትሪክታችን ያለንን ታላቅ ሀላፊነት የሚደግፉ ሲሆን ከእናንተ/ከማህበረሰቡ ለሰማሁት ነገር ቀጥተኛ ምላሽ ናቸው። በጥንቃቄ፣ ጥረት እና ጥንቃቄ በተሞላበት የበጀት አስተዳደር እነዚህ ሪሶርሶች ትምህርት ቤቶቻችንን ያሻሽላሉ።

በፍኖተ ካርታችን መሠረት በመጪዎቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ማመልከቻዎችን ለመቀበል፣ ለመቅጠር እና ልምድ ያላቸውን መሪዎች በሥራ ላይ ለመመደብ ጥሩ አቋም ላይ እንገኛለን። ምክትል ሱፐርኢንቴንደንት፣ ዋና የኦፕሬሽን ኦፊሰር እና ዋና የአካዳሚክ ኦፊሰር ለማግኘት ገለልተኛ፣ ሀገር አቀፍ ፍለጋ ጀምረናል። በመሪዎቻችን ውስጥ የሚፈልጓቸውን ባህሪያት ግንዛቤ በማዳበር እና በተመረጡ የስራ መደቦች ላይ በቃለ መጠይቅ ፓነሎች ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በመጋበዝ ባለድርሻ አካሎቻችንን በምርጫ ሂደቱ እናሳትፋለን።

እስከዚያው ድረስ፣ ነባር መሪዎቻችን እና ሰራተኞቻችን ለተማሪዎቻችን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን እቅዶች እና አተገባበር ለመቀጠል ዝግጁ ናቸው። በኮቪድ-19 ምክንያት የሚከሰቱትን የመማር እና የጤንነት መስተጓጎሎችን ለመቀነስ በምናደርገው ጥረት በግንዛቤ ማስጨበጥ ረገድ ተማሪዎቻችን እና ባለድርሻ አካላት የሚገባቸውን የላቀ ደረጃ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል በዲስትሪክቱ ውስጥ በእያንዳንዱ ደረጃ ተሳትፎን በማሻሻል የምንጠብቀውን የተሻለ የግንዛቤ አቅም ገንብተናል።

ስለ ትምህርት ቤቶቻችን ጠንካራ ጎኖች፣ ማሳደግ ያሉብንን ዘርፎች እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ከእርስዎ ጋር ለመወያየት መሰባሰባችንን እንቀጥላለን። ዲስትርክታችንን ወደፊት ለማራመድ በምንሰራበት ወቅት በቀጣይነት ለሚያበረክቱት አጋርነት ትልቅ አድናቆት አለኝ።

ከአክብሮት ጋር

Monifa B. McKnight, Ed.D.
Interim Superintendent of Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools