መልእክት፦ መታወቅ ያለባቸው አምስት ነገሮች / የካቲት 25

ለአርብ ፌብሩዋሪ 25 ልታውቋቸው የሚገቡ አምስት ነገሮች የሚከተሉት ናቸው። እነርሱም ስለ ጭንብል መመሪያ፣ ኳራንቲን ማግለል እና መመሪያዎች፣ የኮቪድ-19 መመርመሪያ ኪት መመሪያ፣ መጥፎ የአየር ሁኔታን የማካካስ ቀናት እና ሌሎችንም ጉዳዮች ያካትታሉ።

  1. በ MCPS ትምህርት ቤቶች የማስክ አጠቃቀም መመሪያ አሁንም ይቀጥላል።

የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት (MSDE) ፌብሩዋሪ 22 የአደጋ ጊዜ ጭንብል አጠቃቀምን መመሪያ ለመሻር ድምጽ ተሰጥቷል። የጋራ የህግ አውጪው ኮሚቴ ውሳኔውን ማጽደቅ እና ስልጣኑ በስቴት አቀፍ ደረጃ የሚነሳበትን ቀን መወሰን አለበት። ኮሚቴው የ MSDE ን ውሳኔ ካፀደቀ፣ የአከባቢ ትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች ስለ ጭንብል ግዴታዎች የራሳቸውን ገለልተኛ ውሳኔ የማድረግ ሥልጣን ይኖራቸዋል።
ፌብሩወሪ 24 በተካሄደው የትምህርት ቦርድ ስብሰባ አገናኝ/LINK ጊዜያዊሱፐር ኢንተንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ማክነይት (Interim Superintendent Dr. Monifa McKnight) ማስክ መጠቀም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን የመከላከል ስትራቴጂ መሆኑን ገልጸዋል። MCPS በአካባቢው የቫይረስ ስርጭት ሁኔታ መረጃዎችን በመመርመር በሚቀጥሉት ሳምንታት የጭምብል አጠቃቀምን በተመለከተ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል።

ለአትሌቲክስ
ለ MCPS አትሌቲክስየቅርብ ጊዜ ግንኙነቶች፣ ከተሻሻለው ጋር ወደ R.A.I.S.E. የመመለስ እቅድ ጋር፣ በኮቪድ-19 የአትሌቲክስ መረጃ ድረ-ገጽ ላይ ይገኛሉ።

  1. የኳራንቲን እና ራስን የማግለል መመሪያዎች ተሻሽለዋል

ከማርች 1 ጀምሮ፣ አንዳንድ የጤና ሁኔታዎች ከተሟሉ MCPS ለተማሪዎች ከ10-ቀን መገለል እና ኳራንቲን ማቆያ ጊዜ ወደ አምስት ቀን ኳራንቲን መቆየት ይሸጋገራል። ይህ ለሰራተኞች ክተሰጡት መስፈርቶች እና ከ CDC የተሰጡ መስፈርቶች ጋር፣ የሜሪላንድ የጤና መምሪያ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ (DHHS) መመሪያዎች ጋር ይጣጣማል።
እዚህ የበለጠ ግንዛቤ ማግኘት ይችላሉ

  1. የኮቪድ-19 መመርመሪያ ዕቃዎች በሚቀጥለው ሳምንት ይሠራጫሉ።

የ MCPS ተማሪዎች እና ሰራተኞች የኮቪድ-19 ፈጣን የቤት ውስጥ የአፍንጫ መመርመሪያ ኪቶችን ማግኘት ይቀጥላሉ። ከፌብሩወሪ 28 እስከ ማርች 21 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቅርብ ጊዜ የሚመጡ መመርመሪያዎች እንደሚሰራጩ ይጠበቃል። በእያንዳንዱ እሽግ ውስጥ ሁለት መመርመርያዎች ይኖራሉ። ምርመራዎቹ በዚህ ድህረ ገጽ ላይ ባለው መረጃ መሰረት ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው፣ ተዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች (FAQs) እና የሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ አገናኝ/ሊንክ እነሆ። እባክዎን ፈጣን የመመርመሪያ እቃዎች በ 32F እና 86F ዲግሪዎች መካከል ባለው ደረቅ ቦታ መቀመጥ አለባቸው።

  1. በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት የተስተጓጎሉ የትምህርት ቀኖችን የማካካሻ እቅድ ተዘጋጅቷል።

በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ስርአት አቀፍ የት/ቤቶች መዘጋት እና ኖቬምበር 24፣2021 አንድ የትምህርት ቀን በእቅድ የተዘጋበትን ቀን ለማካካስ፣ MCPS ለዚህ የትምህርት አመት የሜሪላንድ ስቴት መስፈርቶችን ለማሟላት ሶስት የትምህርት ቀናትን ማካካስ አለበት። የ 2021–2022 የትምህርት ዓመት አቆጣጠርን የሚያብራራ መልእክት ፌብሩዋሪ 24 ወደ ማህበረሰቡ ኢሜል ተልኳል እዚህ ያንብቡት።

  1. የፀረ-ዘረኝነት ኦዲት ዳሰሳ በሚቀጥለው ሳምንት ይጀመራል

ከ 4ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በሙሉ በማርች ውስጥ ከዕድሜአቸው ጋር የሚስማማ ማንነታቸው በማይገለጽ ሁኔታ የዳሰሳ ጥናት ላይ ይሳተፋሉ። መርጠው ለመተው ከፈለጉ ጊዜው (opt-out period) እስከ አርብ ፌብሩዋሪ 25 ቀን 11:59 p.m. ድረስ ተራዝሟል።

    1. እነዚህ ሪሶርሶች ስለ ዳሰሳ ጥናቱ ያብራራሉ-
        1. ሁሉም ተማሪዎች የዳሰሳ ጥናቱ ላይ ከመሳተፋቸው በፊት ማየት ያለባቸው vቪዲዮ
        2. ስለ ፀረ ዘረኝነት ኦዲት የተሰጠ አጭር መግለጫ (español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ)
        3. የዳሰሳ ጥናቱ ምን እንደሚመስል ማብራሪያ

በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች (español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ)



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools