buses covered in snow

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ በተቀረው 2021-2022 የትምህርት ዓመት በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች በሚዘጉባቸው ቀናት ወደ ቨርቹወል ትምህርት እንደሚሻገር ይገመታል። እነዚህ ቀናት ለሁሉም ደህንነት ሲባል የትምህርት ተቋማትን መዘጋት እንደሚያስፈልግ ስትሪክቱ የሚወስንባቸው ቀናት ናቸው። ይህ ውሳኔ የሚሰጠው እያንዳንዱን ሁኔታ በማጤን ነው።
መጥፎ የአየር ሁኔታ ሲተነበይ የ MCPS የመጓጓዣ እና የአመራር አካላት የአየር ሁኔታ ትንበያውን እየተከታተሉ ወደ ቨርቹወል ትምህርት የመሸጋገር ሁኔታ ካለ ለቤተሰቦች ያሳውቃሉ። ተማሪዎች ወደ ቤታቸው በሚመጡበት ጊዜ Chromebooks፣ቻርጀሮች እና ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶችን ይዘው መምጣታቸውን እንዲያረጋግጡ ይጠየቃሉ። ሰራተኞችም ቨርቹወል የማስተማሪያ ቁሳቁሶች እና ዝግጅት እንዲኖራቸው ይጠየቃሉ።
MCPS ከትምህርት ተቋማት ጋር ለመገናኘት እና ወደ ቨርቹወል ትምህርት ስለመሸጋገር ለማሳወቅ የሚቻልባቸውን በርካታ መንገዶችን ይጠቀማል።እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፡-

  • የ MCPS ድረገጽ
  • ConnectED ለትምህርት ሲስተም ኢሜይሎች እና አጫጭር የጽሑፍ መልዕክቶች ማስተላለፊያ
  • Alert MCPS/MCPS Alerta ለመላ ካውንቲው አስቸኳይ አጫጭር የጽሑፍ መልክት ማስተላለፊያ
  • በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ የማህበራዊ መገናኛ አውታሮች (Twitter, Facebook and Instagram)
  • የአካባቢ የዜና አውታሮች
  • MCPS–TV (Comcast 34, Verizon 36, RCN 89) እና
  • የተቀዳ ድምፅ ማስተላለፊያ የስልክ መስመር (301-279-3673)

ይህ ገጽ አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ሲከሰት በሚከናወን ቨርቹወል የትምህርት ወቅት ምን እንደሚጠበቅ ለማስገንዘብ እንዲረዳዎት እና የቴክኒካዊ ድጋፍ ግብአቶችን ለመስጠት የሚያግዝ መረጃ የያዘ ነው።
ጠቃሚ ማስገንዘቢያዎች፦

  • በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ቨርቹወል የመማሪያ ቀን ተማሪዎች እና ሰራተኞች ዝግጅታቸውን እንዲያመቻቹ፣log in አድርገው ሪሶርሶችን እንዲያገናኙ ጊዜ ለመስጠት ሁሉም ትምህርቶች ከትምህርት ቤቱ መደበኛ የደወል መርሃ ግብር ከሁለት ሰአት በኋላ ይጀምራሉ።
  • ከእርስዎ ትምህርት ቤት የእለቱን የትምህርት መርሃ ግብር መረጃ ወይም ሌላ የተለየ ነገር ካለ መረጃው በት/ቤቱ ርእሰመምህር አማካይነት ይተላለፋል።
  • ትምህርት ማግኘት ያልቻሉ ተማሪዎች በምክንያት እንደቀሩ ስለሚቆጠርላቸው ያመለጣቸውን የትምህርት ስራ እንዲያካክሱ እድል ይሰጣቸዋል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools