magruder high school

የማግሩደር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት / ጃኑወሪ 25

ውድ የማግሩደር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቤተሰቦች፣

ያለፈው አርብ የተፈፀመውን አሳዛኝ ክስተት ተከትሎ ዛሬ ወደ ትምህርት ቤት የተመለስን የመጀመሪያ ቀናችንን አክብረናል። እያንዳንዱ ተማሪ፣ የሥራ ባልደረባ እና አስተዳዳሪ በጋራ ተሳስበን በአንድነት ተመልሰናል። የአርቡ ክስተት አሰቃቂ ነበር፣ ዛሬ ግን በፈውስ ጉዟችን ውስጥ የሆነው ሌላ አስፈላጊ እርምጃ ነበር። ከአእምሮ ጤና ባለሙያዎች፣ ከህግ አስከባሪ አካላት እና ከማህበረሰብ ሪሶርሶች ጋር በመሆን ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች የተሰማቸውን እንዲናገሩ እና እንዲገልጹ እድሎችን ሰጥተናል። አንዳንድ የማግሩደር ተማሪዎች እና ሰራተኞች ሀሳባቸውን እና ስሜታቸውን በግልፅ አስቀምጠዋል፣ ሌሎች ደግሞ እንደዚህ የተሰማቸውን ለመግለጽ ገና ዝግጁ አይደሉም፣ ወይም ይህን ለማድረግ የተለየ አካባቢን ይመርጣሉ። ምንም የተሳሳተ አካሄድ አልነበረም፥. ተማሪዎች እንዴት መሳተፍ እንደሚፈልጉ ምንም ይሁን ምን፣ አንዳችን ለሌላው ደጋፊ እንሆናለን።

outside magruderዛሬ በተማሪዎቻችን እና በሰራተኞቻችን ዙሪያ የተገኙት የመግሩደር አሳቢ ጓደኞቻችን የተለያዩ ሪሶርሶችን ስላቀረቡልን እድለኞች ነን። ከማህበረሰባችን የት/ቤታችን የፈውስ ሂደት እንዲጀምር ለመርዳት የወሰኑ ከ100 በላይ አጋሮችን ተቀብለናል። የ MCPS ካውንስለሮች እና ሳይኮሎጂስቶች ከ EverMind የአእምሮ ጤና ባለሙያዎች እና ከ Stread Outreach Network ስፔሻሊስቶች፣ የካውንቲው የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ፣ Identity, Inc.፣ አዎንታዊ የወጣቶች እድገት እና ከ MCPS የተማሪ እና የቤተሰብ ድጋፍ ጽ/ቤት ቡድን ጋር በመሆን ድጋፍ ሰጥተዋል። የአእምሮ ጤና ባለሙያዎች በሳምንቱ ውስጥ መገኘታቸውን ይቀጥላሉ።

ተማሪዎቻችን ቀኑን የጀመሩት ከፖሊስ አጋሮቻችን ድጋፍ በማየት ሲሆን ሁሉም ተማሪዎች ወደ ህንፃው ሲገቡ ሰላምታ እየተሰጣቸው ነበር። ብዙ ፖሊሶች ቀኑን ሙሉ አብረውን ቆይተዋል። የእኛ የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር Sgt. ጄሰን ኩፔታ፣ ከተማሪዎቻችን እና ሰራተኞቻችን ጋር የመሰረተውን ግንኙነት ለመቀጠል ከእኛ ጋር አብሮ ይቀጥላል።

ጊዜያዊ ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒት ተማሪዎችን እና ሰራተኞችን ለመገናኘት እና ድጋፋቸውን ለማሳየት ዛሬ ጥዋት ትምህርት ቤታችንን ጎበኝተዋል። የመማሪያ ክፍሎችን ጎበኝተዋል፣ተማሪዎችን አነጋግረዋል፣እና ካውንስለሮችን፣ሳይኮሎጂስቶችን እና የማህበረሰብ ድጋፍ አጋሮችን ላደረጉት ትብብር አመስግነዋል። የትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት ብሬንዳ ቮልፍ ከዶክተር ማክኒት ጋር አብረው በመሆን ሰራተኞቻችንን ለማየት እና ቃል የገባናቸው ድጋፎች እንዳሉ እና ተማሪዎቻችንን ለማገልገል ዝግጁ መሆናችንን ለማረጋገጥ ችለዋል።

ለተደረገልን ድጋፍ እጅግ በጣም እናመሰግናለን። ትምህርት ቤት በተለይም በጣም ፈታኝ በሆነ ጊዜ እርስ በርስ የሚደጋገፉ አባላት ያሉት ማህበረሰብ ነው። የተመለከትነው ምላሽ አንድ ማህበረሰብ በጥሩ ጊዜ እና በአስቸጋሪ ጊዜያት እንዴት መስራት እንዳለበት ያስገነዝበናል። ተማሪዎች በግቢያችን ውስጥ እጅግ ዋጋ እንዳላቸው እና ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ማወቅ አለባቸው። ሰራተኞቻችንም ለትምህርታዊ ተልእኳችን አስፈላጊ እና ወሳኝ መሆናቸውን ማወቅ አለባቸው።

ይህን የመሰለ ከፍተኛ መግባባት እና መተሳሰብ ያሳየ ማህበረሰብ ለመምራት በመቻሌ በጣም ኩራት ይሰማኛል። ከላይ ባለው ፎቶ ላይ እንደምትመለከቱት፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የፖሊስ መኮንን ተማሪዎቻችንን “እንወዳችኋለን” የሚል ምልክት ይዞ ነበር ያገኛቸው። በእርግጥ፣ ማህበረሰባችን ዛሬ እና በየቀኑ ይወደዳል።

እኛ ኮሎኔል ብርቱዎች ነን!

Leroy C. Evans, Ed.D.
Principal, Col. Zadok Magruder High School

ጠቃሚ ሪሶርሶች፦:

  • የአሜሪካ የሳይኮሎጂ ባለሙያዎች ማህበር = ስሜታዊ ቀውስ ሲያጋጥም እንዴት መርዳት እንደሚቻል (American Psychological Association: How to help in an emotional crisis)
    www.apa.org/helpcenter
  • የአሜሪካ የሳይኮሎጂ ባለሙያዎች ማህበር = የመሣርያ ተኩስ ፍርሃት ሲያጋጥም የልጅዎን ስጋት ለማስወገድ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ (American Psychological Association: Helping your child manage distress in the aftermath of a shooting)

https://www.apa.org/topics/gun-violence-crime/shooting-aftermath

  • ብሔራዊ የትምህርት ቤት ሳይኮሎጅስቶች = ስለ ትምህርት ቤት ደህንነት ደህንነት እና ቀውስ (National Association of School Psychologists: School Safety and Crisis)

https://www.nasponline.org/resources-and-publications/resources/school-safety-and-crisis

MCPS

እርዳታ ለመጠየቅ አስፈላጊ የስልክ መስመሮች፦

  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ በቀውስ ጊዜ ክፍት የስልክ መስመር = Montgomery County Crisis Hotline - 301-738-2255
  • ሜሪላንድ የት/ቤቶች ሠላምና ደህንነት የጥቆማ መስመር = Maryland Safe Schools Tip Line - 833-MD-B-SAFE
  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ የቀውስ ማዕከል የስልክ መስመር = Montgomery County Crisis Center - 240-777-4000
  • ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ሠራተኞች የድጋፍ ፕሮግራም የስልክ መስመር = Employee Assistance Program (EAP) for MCPS staff - 240-401-6498


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools