ሐሙስ ጃንዋሪ 20 ማወቅ ያለብዎት አስራ አንድ ነገሮች

በዚህ ሳምንት ሊታወቁ የሚገባቸው አስራ አንድ ነገሮች፦
16 ትምህርት ቤቶች ለ10 ቀናት ወደ ቨርቹወል ትምህርት መሸጋገራቸውን፣ የትራንስፖርት መስተጓጎል መቀነስ፣ ስለ ተተኪ መምህራን ክፍያ መሻሻል፣ የታቀደ የተማሪ ጥሎ መውጣት፣ ወቅታዊ የኳራንቲን መመሪያዎችን ስለመጠበቅ እና ሌሎችንም ያካትታል።
1.16 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ለ10 የካለንደር ቀናት ወደ ቨርቹወል ትምህርት ተሸጋግረዋል።  በርካታ የአሠራር እና የጤና ሁኔታዎች ከተገመገሙ በኋላ፣ የሚከተሉት ትምህርት ቤቶች ከጃንዋሪ 20 እስከ ጃንዋሪ 29 ባለው ጊዜ ውስጥ በቨርቹወል ትምህርት እንዲቆዩ ተደርጓል። ይህ ውሳኔ የተደረገው ከት/ቤት መሪዎች እና የወላጅ ተወካዮች ቡድን በተሰጡ አስተያየቶች ነው። ትምህርት ቤቶቹ ሰኞ ጃንዋሪ 31 በአካል ወደ ት/ቤት ይመለሳሉ።

የትምህርት ቤቶ ዝርዝር፦ 

  • Beall Elementary School
  • Briggs Chaney Middle School
  • Brookhaven Elementary School
  • Clopper Mill Elementary School
  • Capt. James E. Daly Elementary School
  • Gaithersburg Elementary School
  • Glenallan Elementary School
  • Dr. Martin Luther King, Jr. Middle School
  • Lakelands Park Middle School
  • Neelsville Middle School
  • Paint Branch High School
  • RICA – John L. Gildner Regional Institute for Children and Adolescents
  • Sargent Shriver Elementary School
  • Twinbrook Elementary School
  • Watkins Mill Elementary School
  • Whetstone Elementary School

ወደፊት፣ ተጨማሪ ትምህርት ቤቶች ወደ ቨርቹወል ትምህርት የሚሸጋገሩ ከሆነ፣ MCPS በአርብ ቀናት ማስታወቂያዎችን ያስተላልፋል፣ ከዚያም ቨርቹወል ትምህርቱ ሰኞ ይጀምራል። በዚህ ሳምንት ምንም ተጨማሪ ትምህርት ቤቶች ወደ ቨርቹወል ትምህርት አይሸጋገሩም።

2. MCPS የቨርቹወል ማስተማር አቅርቦትን እያሰፋ ነው። MCPS በኳራንቲን ባቆዩም ነገር ግን በኮቪድ-19 ምክንያት ትምህርት ቤት ለመምጣት ስጋት ላላቸው ተማሪዎች እንደየሁኔታው ቨርቹወል ትምህርት ለመስጠት ቁርጠኝነት አለው። በዚህ አማራጭ ላይ ፍላጎት ያላቸው ቤተሰቦች የልጃቸውን ትምህርት ቤት ማነጋገር አለባቸው እና ከት/ቤት የቀሩበት ጊዜ በምክንያት እንደሆነ ይቆጠራል። ይህ አማራጭ እስከ ሰኞ ጃንዋሪ 31 ድረስ የሚገኝ ሲሆን ምናልባት ሊራዘምም ይችላል።

3. የትራንስፖርት አቅርቦት እክል ማሽቆልቆሉን ቀጥሏል። አገልግሎት መስጠት ያልተቻለ የትምህርት ቤት አውቶቡስ መጓጓዣ መስመሮች ከፍተኛ ከነበረው 8% ወደ ተሻሽሎ 0.5% ዝቅ ብሏል። ከጃንዋሪ 19 ጀምሮ፣ (ከ1200 በላይ የት/ቤት መጓጓዣ አገልግሎት ከሚሰጡ መስመሮች ውስት) 12 አገልግሎት መስጠት ያልቻሉ የአውቶቡስ መስመሮች ነበሩ። ወደ ሙሉ አገልግሎት ለመመለስ ጥረት ስናደርግ ስላሳዩን ትዕግስት እናመሰግናለን።

4. በሰው ሃይል እጥረት ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች ለመፍታት፣ MCPS ለተተኪ መምህራን ማካካሻ ከፍ ከማድረጉም በላይ ሌሎች ዋስትናዎችን ጭምር ፈቅዷል።  በአካል ትምህርት መማርን ለማስቀጠል በሚያስፈልገው ወሳኝ እርምጃ፣ MCPS ከዚህ ወር ጀምሮ ለተተኪ መምህራን የደመወዝ መጠን ጨምሯል። እነዚህን ጭማሪዎች በማድረግ፣ MCPS የተተኪ መምህራንን ክፍያ በአብዛኛዎቹ ምድቦች ሪጅኑን ይመራል። ተተኪ አስተማሪ ለመሆን ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች
እዚህ ማመልከት ይችላሉ።

5. ጊዜያዊ ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ማክኬነይት (Dr. Monifa McKnight) በዚህ ሳምንት የኮቪድ-19 አያያዝ ዕቅዶችን ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል ጋር ተወያይተዋል። ጃንዋሪ 18፣ ዶ/ር ማክኒት (Dr. McKnight) የትምህርት ሥርዓቱን እቅድ አጠቃላይ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ከካውንስል አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል። የተካሄደውን ክፍለ-ጊዜ እዚህ መመልከት ይችላሉ።
ጃንዋሪ 19፣ ዶ/ር ማክኒት (Dr. McKnight) እና የትምህርት ስርዓቱ አመራር ከካውንስል የትምህርት እና የባህል ኮሚቴ ጋር ያደረጉትን የጥያቄ እና መልስ ክፍለ ጊዜ እዚህ መመልከት ይችላሉ።
በክፍለ-ጊዜዎቹ የተካተቱት ርዕሰ ጉዳዮች የት/ቤቶችን ደህንነት ለመጠበቅ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎችን፣ MCPS ትምህርት ቤቶች ወደ ቨርቹወል ትምህርት መሸጋገር አለባቸው የሚለውን ለመወሰን የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች፣ ወረርሽኙ ያስከተለውን የትምህርት መስተጓጎል ለመፍታት ትኩረት የመስጠት አስፈላጊነት እና ተጨማሪ ምርመራ ማድረግ እና ንክኪ ያደረጉትን ፍለጋ የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ያካትታሉ።

6. Equity Hubs በአካል ከሚማሩበት ወደ ቨርቹወል ትምህርት ለተሸጋገሩ ትምህርት ቤቶች ከቅድመ መዋእለ ህፃናት እስከ 5ኛ ክፍል ተማሪዎች ደህንነቱ አስተማማኝ በሆነ መንገድ በአካል ተሞክሮዎችን ይሰጣል።
 
ወላጆቻቸው በሚሰሩበት ጊዜ ልጆቻቸው ቨርቹወል ትምህርት ለመማር አስተማማኝ ቦታ ለሚያስፈልጋቸው፣ እና ከቤታቸው ቨርቹወል ትምህርት ማግኘት ለማይችሉ ወይም የበለጠ የተሠናዳ የትምህርት አካባቢ ለሚያስፈልጋቸው ቤተሰቦች ፈታኝ ሊሆን ይችላል። "Black and Brown Coalition and The Children’s Opportunity Fund" ከህፃናት እንክብካቤ አቅራቢዎች ጋር በመተባበር ፍትሃዊነትን እንደ መፍትሄ ለመመስረት እየሠሩ ናቸው። 

ልጆቻቸው በቨርቹወል ትምህርት ላይ የተሰማሩ ቤተሰቦች በሞንትጎመሪ ካውንቲ ካሉት 103 Equity Hubs ውስጥ በአንዱ በቨርቹወል ትምህርት ወቅት የሙሉ ቀን የልጅ እንክብካቤ እና ድጋፍ በነጻ መመዝገብ ይችላሉ።

በዚህ ሳምንት ወደ ቨርቹወል ትምህርት ከሚገቡት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስምንቱ  አጋር የህጻን እንክብካቤ ማዕከላት ያሏቸው ስለሆነ ተማሪዎችን አርብ ጃንዋሪ 21 ለማስጀመር ይመዘግባሉ።
የ MCPS የተማሪዎች ሰራተኞችም ለቤተሰቦች መረጃ ለመስጠትና እና የምዝገባ ሂደቱን ለመርዳት ይችላሉ። MCPS በሚቀጥሉት ሳምንታት ይህንን ሪሶርስ ለተጨማሪ ቤተሰቦች ተደራሽ ለማድረግ እነዚህን እድሎች ያሰፋል። የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎን የልጅዎን ትምህርት ቤት ያነጋግሩ። ይህንን እድል የመጠቀም ፍላጎት ያላቸው ቤተሰቦች የትምህርት ቤታቸውን ካውንስለር ማነጋገር ይችላሉ።

7. በበርካታ የ MCPS ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ የተማሪ መሪዎች   ኮቪድ-19 በትምህርት ቤቶች ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ሀሳባቸውን ለመግለጽ ጥር 21 ቀን የእግር ጉዞ ለማድረግ አቅደዋል። MCPS ወረርሽኙ የተማሪዎችን ትምህርታዊ ልምዶች በከባድ ሁኔታ እንደጎዳ ይገነዘባል፥ ስለሆነም የተማሪዎችን በሲቪክ የህይወት ተሞክሮ አካል በመሆናቸው ሃሳባቸውን እንዲገልጹ እና ጉዳያቸውን ለመናገር ያላቸውን ፍላጎት ይደግፋል።

ተማሪዎች በግቢ ውስጥ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሃሳባቸውን እንዲገልጹ እድል የሚሰጥ እቅድ ለማውጣት ከትምህርት ቤታቸው አስተዳዳሪዎች ጋር በቅርበት እንዲሰሩ ማበረታቻ ተደርጓል። 

እባክዎን ያለፍቃድ ከትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ መልቀቅ ወይም ከክፍል ውጪ መውጣት ያለምክንያት ከትምህርት ቤት እንደመቅረት የሚቆጠር መሆኑን እንዲያውቅ/እንድታውቅ ከልጅዎ ጋር ተነጋገሩ። 

ሁሉም ሰራተኞች፣ የትምህርት ስርዓቱ አመራርን ጨምሮ፣ ተማሪዎች የትምህርት ተሞክሮአቸውን እንዴት ማሻሻል እንደሚችሉ ውይይቶችን ለማድረግ ቁርጠኛ ናቸው። በጊዜያዊ ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ማክላይት (Dr. Monifa McKnight) እና ተማሪ የቦርድ አባል ሃና ኦ ሎኔይ (Hana O’Looney) መካከል የተደረገ የዚህ አይነት የውይይት ዘይቤ የቅርብ ጊዜ ምሳሌ እዚህ ይገኛል።

8. KN95 ማስክ ለተማሪዎች እየተሰጠ ነው።  መደበኛ መጠን ያላቸው (Regular-sized) KN95 ጭምብሎች ለተማሪዎች ለሁሉም ትምህርት ቤቶች ደርሰዋል፣ እናለልጆች የሚሆን መጠን ያላቸው (child-sized) KN95 ጭምብሎች ለትናንሽ ተማሪዎች ወደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በማድረስ ሂደት ላይ ናቸው።  ተማሪዎች እና ሰራተኞች በ MCPS መገልገያዎች/ፋሲሊቲዎች ውስጥ ሲገቡ ጭምብል እንዲያደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን።

9. ጊዜያዊ ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ማክኒት በ "NAACP" አማካይነት በተካሄደው (Montgomery County Parents’ Council and the Black and Brown Coalition for Educational Equity and Excellence) የበይነመረብ ዝግጅት ላይ ስለ ትምህርት ፍትሃዊነት እና ልቀት የጥያቄ እና መልስ ክፍለ ጊዜ ቀርበው አስረድተዋል። ጃንዋሪ 19፣ ዶ/ር ማክላይት ስለ ኮቪድ-19 ምላሽ አሰጣጥ፣ ስለ ጠንካራ የኮርስ ተደራሽነት፣ የፀረ ዘረኝነት ኦዲት ጉዳይ፣ ተማሪዎች የሚሰጣቸው ዕድል ክፍተቶችን በሚመለከት፣ ከወረርሽኙ በመማር የተደረገ ማገገም፣ የባህል ብቃት እና የሰራተኞች ስብጥርን በሚመለከቱ ከማህበረሰቡ በተነሱ ጥያቄዎች ዙርያ Dr. McKnight ንግግር አድርገዋል። ዶ/ር ማክኒት በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ዙርያ የማህበረሰቡን ልምዶች በመስማታቸው እና የትምህርት እድሎችን ለማጠናከር በጋራ ለመስራት ቁርጠኝነት ያላቸውን አድንቀዋል። ስለ ስብሰባው እንደገና እዚህ ማየት ይችላሉ።

10. በዚህ ወቅት ስለ ተማሪ ማግለል (ኳራንቲን) ወይም በለይቶ ማቆያ መመሪያዎች ላይ ምንም ለውጥ አልተደረገም። ምንም እንኳን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ኳራንቲን ማግለልን በተመለከተ የተሻሻሉ መመሪያዎች ቢኖሩም፣ MCPS አሁን ያለውን መመሪያ ይጠብቃል።
ጃንዋሪ 9  በተላለፈው የማህበረሰብ መልዕክት ላይ እንደተገለጸው፣ የቫይረሱ ስርጭት መጠን መቀነስ ወይም መስፋፋት ስለ ኳራንቲን የለይቶ ማቆያ ቀናት ብዛት መቀነስ ይቻል እንደሆነ ይመራናል።

11. በቅርብ ጊዜ ለተፈጠረው ከባድ የአየር ሁኔታ ቀናት የማካካሻ ቀናት አልተወሰኑም።
 
በዚህ ወር አራት አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ቀናት ነበሩ፣ እና በትምህርት-ዓመት ካለንደር ባሉት የትምህርት ቀናት መሰረት ሦስቱን ማካካስ ይኖርብናል።  የእነዚህን ቀናት የማካካሻ ዕቅዶች በሚቀጥሉት ሳምንታት ከማህበረሰቡ ጋር እናጋራለን።  ሰኞ፣ ጃንዋሪ 24 እና ማክሰኞ ፌብሩዋሪ 1 የታቀዱት ፕሮፌሽናል ቀኖች በታቀደው መሰረት ይከናወናሉ።



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools