ጃኑወሪ 13፣ 2022— መታወቅ ያለባቸው ስድስት ነገሮች  

January 13, 2022

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ስለ ሐሙስ፣ ጃንዋሪ 13፣ 2022 ማወቅ ያለብዎት ስድስት ነገሮችን እነሆ። ከዚህ በታች የተገለጸው ጃኑወሪ 12 የ MCPS የማህበረሰብ ውይይት የተደረገባቸው ጉዳዮች ሲሆኑ፣ ማንኛውም ትምህርት ቤት በተናጠል ወደ ጊዜያዊ ቨርቹወል ትምህርት እንዲሸጋገር የሚያስገድዱ ቁልፍ ጉዳዮችን፣ ስለ ተማሪዎች ጭንብል መረጃ፣ ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ ዕቃዎችን ወደ ቤት ስለ መውሰድ እና ሌሎችንም ጉዳዮች ያካትታል።

  1. የ MCPS የማህበረሰብ ውይይቶች ማህበረሰብን የሚመለከቱ/ሁሉ አቀፍ ጥያቄዎችን ያካትታሉ

የትምህርት ዲስትሪክት አመራር እና የካውንቲ መሪዎች ጃንዋሪ 12 በተደረገ የቀጥታ ስርጭት አውታረመረብ የማህበረሰብ ውይይት ላይ ተሳትፈዋል፥ ውይይቱን እዚህ መመልከት ይችላሉ። ተመራጭ ባለስልጣናት እና የትምህርት ስርዓት መሪዎች በትምህርት ቤቶች የጤና አጠባበቅ እና ደህንነት ፕሮቶኮሎች፣ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እና ወደ ቨርቹወል ትምህርት የመሸጋገር መመሪያን የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

የማህበረሰብ ውይይቱን ተከትሎ፣ ከተማሪ የቦርድ አባል ሃና ኦሎኒ (Hana O’Looney) እና ከተማሪዎች ጋር በ Instagram ቀጥታ ስርጭት ውይይቱ ቀጥሏል። እዚህ ይመልከቱ

  1. ወደፊት ወደ ቨርቹወል ትምህርት ሊያሻግሩ የሚችሉ ሁኔታዎች

ወደፊት ማንኛውም ትምህርት ቤት ወደ ቨርቹወል ትምህርት የሚሸጋገር መሆኑን ለመወሰን፣ MCPS የሚከተሉትን ሁኔታዎች ያጤናል፦ የሰራተኞች መቅረት፣ ያልተሟሉ ተተኪ መምህራን ጥያቄዎች ብዛት፣ የበርካታ ተማሪዎች መቅረት፣ አገልግሎት መስጠት ያልቻሉ የት/ቤት አውቶቡስ መስመሮች ብዛት፣ እና ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች በ 10-ቀን ጊዜ ውስጥ ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤት ማሻቀብ የመሣሰሉትን ሁኔታዎች ከግምት ያስገባል። እነዚህን ቁልፍ የሆኑ ምክንያቶችን ምሳሌ ይመልከቱ። አንድ ትምህርት ቤት በተለያዩ ዘርፎች ከሌሎች ትምህርት ቤቶች ጋር ሲነጻጸር ሁኔታው ከፍተኛ ሆኖ ሲገኝ፣ MCPS ከጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት ጋር በመመካከር የዋና ጽ/ቤት ተወካዮችን፣ የትምህርት ቤቱን ርእሰ መምህር፣ የሰራተኞች ተወካዮች እና ወላጆችን ጨምሮ ቡድን ይሰበስባል። ይህ ቡድን ለሱፐርኢንተንደንቱ ካቢኔ ምክረ ሃሳብ ይሰጣል።

አንድ ትምህርት ቤት በተናጠል ወደ ቨርቹወል ትምህርት ለመሸጋገር ከወሰነ፣ለሰራተኞች፣ ለተማሪዎች እና ለማህበረሰቡ እንዲታወቅ በድረ-ገጹ ላይ፣ በኢሜል፣ በ Connect-ED፣ እና በትምህርት ቤት በሚገኝ ማህበራዊ ሚዲያ (ያለ ከሆነ) መግለጫ ይሰጣል። አጠቃላይ የውሳኔ አሰጣጥ፣ የማሳወቂያ ጊዜ፣ እና የሽግግር ሂደት ከሁለት የስራ ቀናት ያልበለጠ ጊዜ ይወስዳል፤ እና ወላጆች ለ 10 የካለንደር ቀናት ትምህርት ቤት ወደ ቨርቹወል ትምህርት እንደሚሸጋገር ቢያንስ አንድ ቀን አስቀድሞ ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል።

  1. ተማሪዎች ቨርቹወል ትምህርት በትክክል እንዲደርሳቸው የተዘጋጁ ዕቅዶች

ጃኑወሪ 13 በተካሄደው የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ወቅት፣ የ MCPS ሰራተኞች ራስን በማግለል እና በኳራንቲን ምክንያት ትምህርት ቤት መምጣት ለማይችሉ ተማሪዎች የማስተማሪያ እቅዶችን አቅርበዋል። የቀረበውን ዝግጅት እዚህ ይመልከቱ።

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (ከጃንወሪ 18 ጀምሮ)፡-

  1. እቤት ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በ MCPS Canvas portal (በዙም ሊሆን አይችልም) የሚፈልጉትን ክፍል የቪዲዮ ስክሪን ቀረጻዎችን ማግኘት ይችላሉ።
  2. ትምህርቱ ለሊተርሲ እና ለሂሳብ ቅድሚያ ይሰጣል
  3. ከአስተማሪዎች ጋር መስተጋብር አይኖርም ወይም ከፍተኛ ሥራ ከሚጠይቅ የቤት ሥራ ጋር ግንኙነት አይኖርም
  4. ይህ ሞዴል ከጃንዋሪ 18 ጀምሮ በኳራንቲን ላይ ለሚገኝ ማንኛውም ተማሪ ተግባራዊ ይሆናል።

በሁለተኛ ደረጃ (ቀድሞውኑ እየተካሄደ ነው)

  1. ግለሰብ አስተማሪዎች በአሁኑ ጊዜ በኳራንቲን ያሉ ተማሪዎችን እያገለገሉ ይገኛሉ፡ ተማሪዎችን ወደ ክፍላቸው በዙም የቀጥታ ስርጭት ያስገቧቸዋል ወይም በእለቱ ትምህርት በማይኖርበት ሠዓት ያገኟቸዋል

ኳራንቲን ላይ ሳይሆኑ ነገር ግን በኮቪድ-19 ምክንያት ስጋት ኖሯቸው ወደ ትምህርት ቤት መምጣት ለማይችሉ ተማሪዎች እንደየሁኔታው የትምህርት አቅርቦቱን እናሰፋለን። በዚህ አማራጭ ላይ ፍላጎት ያላቸው ቤተሰቦች የልጃቸውን ትምህርት ቤት ማነጋገር አለባቸው፥ እና ከት/ቤት የቀሩበት ጊዜ በምክንያት እንደሆነ ይቆጠራል። ይህ አማራጭ እስከ ሰኞ፥ ጃንዋሪ 31 ድረስ የሚገኝ ሲሆን ሊራዘምም ይችላል።

  1. KN95 ጭምብል ለተማሪዎች

በዚህ ሳምንት በትምህርት ቤቶች እና በዋና ጽህፈት ቤት የሚገኙ ሰራተኞች በሙሉ KN95 ጭንብል ተቀብለዋል። ለተማሪዎች የሚታደል KN95 ጭንብል ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደርሷል። MCPS በሚቀጥለው ሣምንት ወደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚመጡ ታዳጊ ተማሪዎች በህፃናት ልክ የተዘጋጀ KN95 ማስክ/ጭምብል እየተገዛ ነው። ተማሪዎች እና ሰራተኞች በ MCPS መገልገያዎች/ፋሲሊቲዎች ውስጥ ሲገቡ ጭምብል እንዲያደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን።

  1. ወደ ቤት የሚወሰዱ የምርመራ መሣሪያዎች/ኪትስ

ተማሪዎች እና ሰራተኞች ወደ ቤት የሚወስዱት ፈጣን የምርመራ እቃዎችን/ኪትስ አግኝተዋል። ተማሪዎች በቤት ውስጥ እነዚህን ምርመራዎች እንዲያደርጉ ወላጆች እንዲረዷቸው እና የልጆቻቸውን ፖዚቲቭ ወይም ኔጌቲቭ የምርመራ ውጤት MCPS የኮቪድ-19 ሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ በመጠቀም ሪፖርት እንዲያደርጉ እንጠይቃለን። (መረጃውን በኤሌክትሮኒክ ማስተላለፍ ካልቻሉ ወደ ልጅዎ ትምህርት ቤት መደወል ይችላሉ።) ሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች እነዚህን ኪቶች እንዲጠቀሙ እና ፖዚቲቭ እና ኔገቲቭ ውጤቶች እስከ አርብ ጃንዋሪ 14 ድረስ ሪፖርት እንዲያደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን።

    1. መመሪያዎች በእንግሊዝኛ | ስፓኒሽኛ 
    2. ፈጣን የቪዲዮ ስልጠና እንግሊዝኛ | ስፓኒሽኛ 

እባክዎ ከትምህርት ቤት ውጪ የተደረጉ የተማሪዎች እና የሰራተኞች ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤቶችን በሙሉ ማሳወቅዎን ይቀጥሉ። ማንኛውም የምርመራ ውጤት ፖዚቲቭ የሆነ(ች) ተማሪ ውጤቱ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ቀናት ወይም ምልክቱ ከታወቀበት ጊዜ አንስቶ (በቅድሚያ የታወቀው የትኛውም ቢሆን) ለ 10 ቀናት ራሱ(ሷ)ን ማግለል ይጠበቅበ(ባ)ታል። ከዋና ጽሕፈት ቤት እና ከትምህርት ቤት ውጪ የሚሠሩ ሰራተኞችም በዚህ ሳምንት ጭንብል እና ፈጣን የመመርመሪያ ኪቶች ተቀብለዋል እና ምንም አይነት ምልክቶች ከታዩ እነዚህን ኪቶች እንዲጠቀሙ እና ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤቶችን እንዲገልጹ በጥብቅ እናሳስባለን። የተማሪዎች እና የሰራተኞች ምርመራ በሚቀጥሉት ሳምንታትም ይቀጥላል።

 

  1. የት/ቤት አውቶቡስ ትራንስፖርት መቆራረጥ እየቀነሰ ነው።

ጃንዋሪ 5 ወደ ትምህርት ቤት ከተመለስን በኋላ በኮቪድ-19 ህመም ምክንያት እና በክፍት የስራ መደቦች ምክንያት የሰራተኞች እጥረት ስላጋጠመን በርካታ የት/ቤት አውቶቡስ መጓጓዣ መስመሮች መቆራረጥን አስከትሏል። እነዚህ ቁጥሮች ወደ ታች በመውረድ ላይ ናቸው፣ ከ100 በላይ የት/ቤት መጓጓዣ መስመሮች ከፍተኛ የት/ቤት አውቶቡስ ትራንስፖርት መቆራረጥ ጫፍ ደርሶ ከነበረበት ዛሬ፣ ጃንዋሪ 13 ወደ 29 ወርዷል።

በ MCPS የትራንስፖርት መምሪያ ውስጥ ያሉ ሰራተኞች የአውቶቡስ ሹፌሮችን መመልመል፣ መቅጠር እና ማሰልጠን እንደቀጠሉ ናቸው። የትራንስፖርት ዲፓርትመንት ግንኙነቱን ይቀጥላል፡-

  1. ዕለታዊ መረጃዎችን በዚህ ገጽ ላይ በመለጠፍ የተወሰኑ የመጓጓዣ መስመሮችን እና ችግሩ የባሰባቸው ትምህርት ቤቶች።
  2. በልዩ ሁኔታ መስተናገድ ያለባቸው ተማሪዎችን የሚያገለግሉ መስመሮች ቅድሚያ ያገኛሉ።
  3. አንድን ትምህርት ቤት የሚያገለግሉ በርካታ መስመሮችን ለመንዳት ያሉትን ሰራተኞች መጠቀም እንቀጥላለን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools