ሰኞ፣ ጃኑወሪ 3 ሁሉም ትምህርት ቤቶች እንደገና ይከፈታሉ።

ጃኑዋሪ 2, 2022

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

እንኳን ለኣዲሱ ዓመት አደረሳችሁ! በክረምት ዕረፍት እንደተደሰታችሁ ተስፋ እናደርጋለን፣ እናም ተማሪዎቻችን በአካል ለመማር ነገ እንደሚመለሱ በጉጉት እንጠብቃለን። በዝግጅታችን ላይ፣ የኮቪድ-19 ሁኔታዎች መጨመርን ሁኔታዎች እየተጋገጥን በአካል የመማር ማስተማር ሥራችንን ለመጠበቅ በምናደርጋቸው ጥረቶች እንዴት ከእናንተ/ከማህበረሰባችን ጋር እንደምንገናኝ በሚቀጥሉት ሳምንታት እንገልጽላችኋለን።

ስለ መጥፎ የአየር ጠባይ
የጃንዋሪ 3 የአየር ሁኔታ ዝናብ እስከ ሰኞ ማለዳ ድረስ ወደ በረዶነት እንደሚቀየር ይተነብያል። ሌሊቱን ሙሉ የአውራ መንገዶችን እና የእግረኛ መንገዶችን ሁኔታ እንከታተላለን እና እንደ አስፈላጊነቱ ስለ ት/ቤት ዘግይቶ መጀመር ወይም ለእለቱ መዘጋት እንወስናለን። እንደዚህ አይነት ማሳወቂያዎች በመደበኛነት የሚተላለፉት ማለዳ 5 a.m. ላይ ነው።

ፖዚቲቭ ሁኔታዎችን ሪፖርት ማድረግ
ማንኛውም ተማሪ ወይም ሰራተኛ ኮቪድ-19 ፖዚቲቭ ሆኖ(ና) ከተገኘ(ች)፣ እባክዎ ይህን ቅጽ በመጠቀም ለ MCPS ያሳውቁ። ይህ በክረምት ዕረፍት ወቅት የምርመራ ውጤታቸው ፖዚቲቭ የሆነ ተማሪዎችን ወይም የስራ ባልደረቦችን መረጃ ለመሰብሰብ ጥቅም ላይ የዋለው ተመሳሳይ ሂደት ነው። ከሰኞ፣ ጃንዋሪ 3 ጀምሮ መረጃውን በኤሌክትሮኒክስ ማቅረብ ካልቻሉ ወደ ትምህርት ቤትዎ ሊደውሉም ይችላሉ።

መረጃ/ውሂብ ሪፖርት ማድረግ
ቅዳሜ ጃንዋሪ 1፣ እስከ 10 ፒ.ኤም. በ MCPS የክረምት ዕረፍት ወቅት በተማሪዎች እና በሰራተኞች መካከል 3,686 ፖዚቲቭ ሁኔታዎች ሪፖርት ተደርጓል። በሜሪላንድ እና በዩናይትድ ስቴትስ ካሉት አዝማሚያዎች ጋር ሲመዛዘን ባለፉት በርካታ ሳምንታት ውስጥ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የኮቪድ ወረርሽኝ ብዛት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። በእኛ የዲሰምበር 30 የማህበረሰብ መረጃ መግለጫ ላይ እንዳሳወቅነው የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ በርካታ እርምጃዎችን እየወሰድን ነው።

በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የፖዚቲቭ ሁኔታዎችን ቁጥር በእዚህ አገናኝ መመልከት ይችላሉ። ትምህርት ቤቶች በክረምት ዕረፍት ወቅት ሪፖርት የተደረጉ ፖዚቲቭ ሁኔታዎችን በሚመለከት ለማህበረሰብ የማሳወቂያ ደብዳቤ አይልኩም። ከሰኞ፣ ጃንዋሪ 3 ጀምሮ በእለቱ በእያንዳንዱ የትምህርት ቤት ጣቢያ የተዘገቡት ፖዚቲቭ የኮቪድ ሁኔታዎች ዝርዝር የኮቪድ-19 መግለጫ ዳሽቦርድ ድረገፅ ላይ በእያንዳንዱ የትምህርት ቀን በ 7 p.m. ሪፖርት ይደረጋል። ዳሽቦርዱ በየሳምንቱ በጠቅላላ የኮቪድ ፖዚቲቭ ሁኔታዎችን እና በለይቶ ማቆያ (ኳራንቲን) ያለውን መረጃ ሪፖርት ማድረጉን ይቀጥላል።

የማህበረሰብ ወቅታዊ መረጃዎች
ለቤተሰቦች ወቅታዊ መረጃ ስለመስጠት፦ በጃኑወሪ ወር ሁሉም የ MCPS ማህበረሰብ አባላት ኮቪድ-19 ወረርሽኝን በተመለከተ በጣም ወቅታዊ መረጃዎችን ለመስጠት እና ተማሪዎችን፣ ሰራተኞችን፣ እና ቤተሰቦችን በጤናማ ሁኔታ ለመጠበቅ ከምንወስዳቸው እርምጃዎች አኳያ በየሣምንቱ ሐሙስ ከሰአት በኋላ ለማህበረሰብ የኢሜል መግለጫ ይተላለፋል።

ትምህርት ቤት በተናጠል ወደ ቨርቹወል ትምህርት የሚሸጋገርበት ሁኔታ
በየቀኑ የወረርሽኙን ስርጭት ሁኔታ መከታተል እንቀጥላለን። ቀደም ሲል እንደተገለጸው፣ 5% ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑት ንክኪ የሌላቸው ተማሪዎች/መምህራን/ሰራተኞች (ቢያንስ 10 ግለሰቦች) በ14 ቀናት ጊዜ ውስጥ ኮቪድ ምርመራ ፖዚቲቭ ውጤት ካላቸው፣ የ MCPS ዋና ጽ/ቤት ሰራተኞች እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ (DHHS) በት/ቤት ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ለ14 የካላንደር ቀናት ወደ ቨርቹወል ትምህርት መሸጋገር እንዳለባቸው ለመወሰን አብረው ይሠራሉ። እባክዎን የ 5% ገደብ ብቻውን የትምህርት ቤት መዘጋትን እንደማያስከትል ያስተውሉ፥ ሊታሰብበት የሚገባው ዋናው ነገር በትምህርት ቤት ውስጥ የቫይረስ ስርጭት ደረጃ ነው። ወደ ቨርቹወል ትምህርት ለመሸጋገር ውሳኔ ከተወሰነ ወላጆች እና አሳዳጊዎች እንዲያውቁ ይደረጋል።

ጠቃሚ/አስፈላጊ ማሳሰቢያዎች

  • ህጻናት ምንም አይነት የበሽታ ምልክት ካላቸው ቤት ያቆዩዋቸው እና የኮቪድ-19 ምርመራ ያድርጉ።
    ምርመራ ማድረግ ተማሪዎች ህመማቸውን ወደሌሎች እንዳያስተላልፉ መደረግ ያለበት አስፈላጊ እርምጃ ነው። እባክዎ ሲታመሙ እቤት ያቆዩዋቸው እና ለኮቪድ-19 ተጨማሪ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያድርጉ።
  • ለምርመራ አዎ ይበሉ/ፈቃድ ይስጡ።
    ተማሪዎች በትምህርት ቤት ውስጥ ምርመራ እንዲደረግላቸው ወላጆች ፈቃድ መስጠት አለባቸው። መስማማታቸውን ይህንን ቅጽ በመሙላት መግለጽ ይችላሉ። ለተጨማሪ ዝርዝሮች፣ እባክዎ የእኛን "Say Yes to the Test" ድረ ገጽ ይጎብኙ።

አትሌቲክስ
ለአትሌቶች እና ተመልካቾች ስለጨዋታ መርሃ ግብሮች፣ ጭንብል ማድረግ፣ የሌሊት አዳር ጉዞ እና ሌሎችም መመሪያ የሚሰጥ ጠቃሚ መረጃ በ "Return to R.A.I.S.E. athletics update" ላይ ቀርቧል። ስለ አትሌቲክስ ወቅታዊ መረጃ በዚህ ሊንክ መመልከት ይችላሉ።

ለ 2022 የመጀመሪያው የትምህርት ቀን ስንዘጋጅ ስለምታደርጉልን ድጋፍ እናመሰግናለን.

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools

ጠቃሚ መረጃዎችEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools