thanksgiving

November 23, 2021

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦
የምስጋናን በዓል "Thanksgiving" ለማክበር ስንቃረብ፣ ይህንን የምንጽፍላችሁ አስደሳች፣ የሚያዝናና እና የሚያነቃቃ እረፍት እንደምንመኝላችሁ ለመግለጽ ነው።
በዓሉ ቆም ብሎ ለማሰላሰል እድል ይሰጣል። ይህን ስናደርግ፣ የትምህርት ስርዓታችን የልጆቻችንን ትምህርት በከፍተኛ ደረጃ የሚያደንቅ ንቁ ማህበረሰብን በማገልገል ምን ያህል እድለኛ እንደሆነ ለማስታወስ እንገደዳለን።
በዚህ ፎል ወቅት ሙሉ በሙሉ በአካል ወደ ትምህርት እንድንመለስ ማህበረሰባችን በአንድነት በመተባበር ስለተደረገልን እገዛ በጣም እናመሰግናለን። ወደ ህንጻዎቻችን ስንመለስ በነበረው ሽግግር የተደረገው እንቅስቃሴ ትብብርን፣ ወዳጅነትን፣ እና ግንኙነትን አዳብሯል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰባችን ባደረጉት ልዩ ጥረት - ተንከባካቢ መምህራኖቻችን፣ አስተዳዳሪዎች፣ ድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች እና ሌሎች ሰራተኞች ባደረጉት ቁርጠኝነት፣ ተማሪዎቻችንን ከነዚህ ልምዶች ጋር ማገናኘት ተችሏል። ከሁኔታው ጋር በሚለማመዱበት ወቅት የተማሪዎቻችን ጽናት፣ እና ከቤተሰቦች እና ከአጋሮቻችን በተገኘው ጽኑ ድጋፍ እጅግ ከፍተኛ ብርታት አግኝተንበታል። ሴሚስተሩ ሁልጊዜ ቀላል ባይሆንም ተባብረን በመስራት ከፊታችን የሚኖሩ ተግዳሮቶችን በጽናት ለመሻገር እየተዘጋጀን ነው።
በዚህ የምስጋና ጊዜ "Thanksgiving" እንደ ወላጆች፣ አሳዳጊዎች፣ አስተማሪዎች እና አጋሮች ተማሪዎቻችንን በህይወታችን ለማክበር ከእኛ ጋር አብራችሁ እንደምትሆኑ ተስፋ እናደርጋለን። እባክዎ ልጅዎን በትምህርት ቤት ስላደረገ(ች)ው ጥረት እና ተማሪዎች ለትምህርት ቤቶቻቸው ማህበረሰብ ስላበረከቱት አስተዋፅኦ እውቅና ይስጡ። እና እባክዎ የወደፊት ሕይወታችንን በመቅረጽ ረገድ አስተማሪዎች የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና ለማድነቅ ትንሽ ጊዜ ይውሰዱ።
ስለ ጠቃሚ ድጋፍዎ እና ስላደረጉልን ብዙ አስተዋጾዎ እናመሰግናለን።
አስደሳች እና ሠላማዊ የበዓል ጊዜ እንደሚሆንላችሁ ተስፋ እናደርጋለን።
ከአክብሮት ጋር
Dr. Monifa B. McKnight
Interim Superintendent, Montgomery County Public Schools
ሞኒፋ ቢ. ማክነይት (ዶ/ር)
ተጠባባቂ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools