የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ከታንክስ ጊቪንግ ቀን በፊት ረቡዕ፣ ኖቨምበር 24 ይዘጋሉ።

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

የትምህርት ቦርድ እሮብ ኖቨምበር 24 ለታንክስ ጊቪንግ (የምስጋና) ቀን ዋዜማ ቀደም ብሎ ሁሉም ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች እንዲዘጉ በዛሬው ቀን ውሳኔ አሳልፏል። ቀደም ሲል ኖቬምበር 24 ሁሉም ሰራተኞች እና ተማሪዎች በቅድሚያ የሚለቀቁበት ቀን እንዲሆን ታቅዶ ነበር። በዚህ ውሳኔ መሠረት ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ከረቡዕ፣ ኖቨምበር 24 እስከ አርብ፣ ኖቨምበር 26 ድረስ ዝግ ይሆናሉ። የልጆች እንክብካቤ አገልግሎት እንደ ቀድሞው መርሃ ግብር ሊኖር ይችላል፣ ነገር ግን እባክዎን ስለ ዝርዝር ሁኔታው እንክብካቤ የሚሰጡትን ያነጋግሩ። ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ሰኞ፣ ኖቨምበር 29 ይከፈታሉ። በተራዘመው የታንክስ ጊቪንግ/የምስጋና በዓል ጊዜ ለማረፍ እና ራስን ለማበርታት የተወሰነ ጊዜ እንደሚወስዱ ተስፋ እናደርጋለን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools

Resolution



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools