girl at home

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ በኳራንቲን መመሪያዎች ላይ የተደረጉ ለውጦች ዝርዝር።

2ኖቨምበር 4, 2021

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

በትምህርት ቤቶች ከ ኖቬምበር 8/2021 ጀምሮ በሥራ ላይ የሚውል የኳራንቲን ሂደቶችን የቅርብ ጊዜ መመሪያ ልንገልጽላችሁ እንፈልጋለን። የሜሪላንድ የጤና ዲፓርትመንት (MDH) እና የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት (MSDE)የተሻሻለ የት/ቤት የኳራንቲን መመሪያ አስተላልፈዋል። የተወሰኑ መመዘኛዎች ከተሟሉ፣ተማሪዎች ኳራንቲን መቆየት አይኖርባቸውም፣ ወይም ለትንሽ ጊዜ ብቻ ማግለል ያስፈልግ ይሆናል። ይህ አዲስ መመሪያ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎችን በኳራንቲን ማግለል እና በቨርቹወል ትምህርት መሣተፍ ያለባቸውን ተማሪዎች ቁጥር ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ምን አዲስ ነገር አለ፦
MDH እና MSDE፣ በተሰጠው መመሪያ መሰረት እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት (DHHS) ጋር በመተባበር ከዚህ በኋላ ሁለት ምድቦች ይኖራሉ ኳራንቲን ማግለል አይኖርም ወይም ለአጭር ጊዜ ብቻ ተለይቶ የመቆየት ጊዜ በኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት ፖዚቲቭ የሆነ(ች) ሰው ጋር ቅርብ ግንኙነት ያደረገ(ች) ሰው። የተቀራረበ ግንኙነት ማለት ፖዚቲቭ ከሆነ ሰው ጋር በ 24 ሰአት ውስጥ ከ 6 ጫማ በታች በሆነ ርቀት በጠቅላላ 15 ደቂቃዎች ወይም በትምህርት ክፍል ውስጥ ከ 3 ጫማ ርቀት በታች የተቀራረበ ግንኙነት ሲኖር ማለት ነው።

  1. በበሽታው የተያዘ(ች) ተማሪ እና የተቀራረበ ግንኙነቱ በተጋላጭነት ጊዜ ጭምብል ያደረጉ ቢሆን እና ተጋላጭነቱ ከፍተኛ ስጋት ባለበት ወቅት ካልነበረ የተቀራረበ ግንኙነት ያላቸው ተማሪዎች ለ MCPS COVID-19 የማጣሪያ ምርመራ መመዝገብ አለባቸው። በማጣሪያ ምርመራ ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ እስከተስማሙ ድረስ ፣ በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት መምጣት መቀጠል ይችላሉ። ነገር ግን ከፍተኛ የተጋላጭነት ስጋት በሚያስከትሉ የት/ቤት አክቲቪቲዎች/እንቅስቃሴዎች መሳተፍ አይችሉም፤ እና ከት/ቤት መቼት ውጭ ተገልለው መቆየት ይጠበቅባቸዋል። ቤተሰቦች በማጣሪያ ምርመራ ፕሮግራሙ እዚህ በሚገኘው ሊንክ ቅጽ በመሙላት መመዝገብ ይችላሉ።

 

  1. ጭምብሎች ያልተለበሱባቸው ቦታዎች ወይም በበሽታ የተያዘ(ች) ሰው አዋቂ በሚሆንበት/በምትሆንበት ጊዜ ጭምር ሁሉም ሌሎች ሁኔታዎች ማለትም፦ በምሳ ወቅት ወይም ከፍተኛ የተጋላጭነት ስጋት የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ወይም እንቅስቃሴዎች ላይ የሚከሰት የተቀራረበ ግንኙነት ተጋላጭነትን ይጨምራል። ስቴቱ ከፍተኛ ስጋት ያለባቸውን መቼቶች ወይም እንቅስቃሴዎችን “የቤት ውስጥ ወይም ከፍተኛ ግንኙነት ያላቸው አትሌቲክስ፣ እና የቤት ውስጥ አየር የመተንፈስና የማስወጣት የትንፋሽ እንቅስቃሴዎች፣ እንደ ዘፈን፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ ወይም በትንፋሽ እየተነፉ የሚሠሩ የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጫወት” በማለት ይገልፃል። በእነዚህ አጋጣሚዎች፣ ያልተከተቡና የተቀራረበ ግንኝነት ያደረጉ ሰዎች ለ10 ቀን በኳራንቲን መቆየት ይኖርባቸዋል፣ ነገር ግን ለተጋላጭነት የሚዳርግ የተቀራረበ ግንኙነት ካደረጉ ከ 5ኛው ቀን በኋላ የ PCR ምርመራ ወስደው ኔገቲቭ ውጤቱ ኔገቲቭ ከሆነ ከ 7 ቀን በኋላ ወደ ትምህርት ቤት ሊመለሱ ይችላሉ።

ያልተለወጡ ነገሮች፦
የኮቪድ-19 ምልክት ያለባቸው ሰዎች ለ10 ቀናት ኩራንቲን ተለይተው መቆየት አለባቸው፣ ለ14 ቀናት ራሳቸውን መከታተል እና ከ ኮቪድ-19 ምልክቶች ነፃ ከሆኑ ብቻ ወደ ትምህርት ቤቶች መመለስ የሚችሉት 100.4 ወይም ከዚያ በላይ ትኩሳት ከሌለባቸው፣ የጉሮሮ መቁሰል፣ ሳል፣ የመተንፈስ ችግር፣ ተቅማጥ፣ ማስታወክ እና ጣዕም ወይም ሽታ ማጣት ከሌለባቸው ብቻ ወደ ት/ቤቶች መመለስ ይችላሉ። ልክ እንደበፊቱ፣ የኳራንቲን መመሪያው የሚመለከተው ያልተከተቡ ግለሰቦችን ብቻ ነው። በዚህ የትምህርት ዓመት እንደታየው የተከተቡ ግለሰቦች ኳራንቲን ማግለል አያስፈልጋቸውም።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools