Say Yes to the test

October 20, 2021

እንፈልግዎታለን!

የኮቪድ -19 ምርመራ የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን ደህንነትና ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፡-

ልጆቻቸው በየትምህርት ቤቶቻቸው ነፃ የኮቪድ -19 ምርመራ እንዲደረግላቸው መስማማታቸውን የገለጹልንን በርካታ ቤተሰቦች እናመሰግናለን። ትምህርት ቤቶች ክፍት ሆነው እንዲቆዩ እና የተማሪዎች እና የሰራተኞች ደህንነትና ጤንነት እንዲጠበቅ ለማገዝ የኮቪድ ምርመራ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው። ቤተሰቦች በሁሉም ደረጃ "ለምርመራ አዎንታዊ መልስ እንዲሰጡ እንፈልጋለን።" ብዙ ቤተሰቦች “አዎን” የሚሉ ከሆነ የእኛ የኮቪድ ምርመራ ፕሮግራም ይበልጥ ውጤታማ ይሆናል። ምርመራው በብዛት የበሽታውን ምልክቶች ለመለየት እና ተገልለው (ኳራንቲን) የሚቆዩ ተማሪዎችን ቁጥር ለመቀነስ ይረዳል።

አንድ ቅጽ ልጅዎ እንዲሳተፍ ወይም እንድትሳተፍ መርጠው ፈቃድ መስጠት ያስችልዎታል። ሁለት ዓይነት ምርመራዎች ያሉ ሲሆን እነርሱም ፈጣን፣ አስተማማኝ፣ እና የማያሳምሙ ናቸው። ከአፍንጫ የናሙና መውሰጃ ጥጥ መጎርጎርያ ይጠቀማሉ።
ምርመራዎቹ፦

  •  የኮቪድ -19 ምልክቶች ለሌለባቸው የዘፈቀደ ናሙናዎች ሳምንታዊ የማጣሪያ ምርመራዎች ይደረጋሉ። በአሁኑ ጊዜ በሳምንቱ መጨረሻ በሁሉም የአንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲደረግ የጊዜ ሠሌዳ ተዘጋጅቷል።
  • የኮቪድ -19 ምልክቶች ላላቸው ተማሪዎች ፈጣን ምርመራዎች ይደረጋሉእነዚህ ምርመራዎች የሚሰጡት ተማሪዎች ትምህርት ቤት ውስጥ እያሉ ነው። በአሁኑ ጊዜ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይደረጋል

የፈቃድ መስጫ ቅጹ በብዙ ቋንቋዎች የሚገኝ ሲሆን በኦንላይን መሙላት ይቻላል፥ ወይም ትምህርት ቤቶች ለቤተሰቦች የወረቀት ቅጂዎችን መስጠት ይችላሉ።
ምርመራዎቹ ተማሪዎች በሳምንት አምስት ቀናት በትምህርት ቤት እንዲማሩ ለማድረግ እና የማህበረሰባችንን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆነ የ MCPS ዕቅድ አካል ናቸው። MCPS ምን እያደረገ እንደሆነ እና ሁሉም የድርሻውን እንዴት እንደሚወጣ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ

የምርመራ ስምምነት ቅጾች፦

English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ /

ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ

Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools