ክቶበር 1, 2021


ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ

ተማሪዎች የዲጂታል ዘመን አካል ናቸው። በይነመረብ ለመረጃ ልውውጥ እጅግ ጠቃሚ መገልገያ ሊሆን ይችላል፤ እንዲሁም ሰዎችን በፈጣን ተለዋዋጭ የማህበራዊ ሚዲያ ሊያገናኝ ይችላል። የሆነ ሆኖ ልጆች በደህና ሁኔታና በጥንቃቄ ካልተጠቀሙበት የተጋላጭነት ትኩረት ሊሆን ይችላል። በቤት እና በትምህርት ቤት፣ተገቢ የአጠቃቀም ባህሪን አስፈላጊነት እና እንዴት ደህንነቱ የተጠበቀ እና አክብሮታዊ የዲጂታል ዜጎች መሆን እንዳለባቸው ለልጆቻችን ማስረዳትና እንዲገነዘቡ ማድረግ የጋራ ሀላፊነታችን ነው።

የኦንላይን አንዱ አደገኛ አዝማሚያ፤ በተለይም TikTok የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ላይ ልጆችን ወደ አጥፊነት፣ አደገኛ እና ሕገወጥ ባህሪ እንዲሄዱ የሚያበረታታ ‹የተንኮል ድርጊት/Devious Licks› ተግዳሮት ነው። ይህ ተግዳሮት ተማሪዎች በተለይም ከት/ቤታቸው እየሰረቁ፣ ንብረት እያወደሙ ወይም የሠረቁትን ንብረት የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን እንዲለጥፉ ይጠይቃል።

ሌሎች ተግዳሮቶችም እንደዚሁ ሁከትን፣ ስርቆትን እና ማስጨነቅ፣ መነዝነዝ፣ ማዋከብ የመሣሰሉትን ድርጊቶች ያበረታታሉ።

የት/ቤቶቻችን ማህበረሰቦች ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጠው ነው፤ እና እንደዚህ ዓይነት ባህሪዎች ጎጂ፣ አደገኛ፣ አክብሮት የጎደላቸው እና የት/ቤቶቻችንን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው። በዝምታ አይታለፉም። በእነዚህ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚሳተፍ ወይም የምትሣተፍ ማንኛውም ተማሪ የትምህርት ጓደኞቻቸውን እና የት/ቤቶቻችንን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ስለሆነ የ ተማሪዎች የስነምግባር ደንብ ላይ በተገለጸው መሠረት ተገቢው የዲስፕሊን እርምጃ ይወሰዳል።

አብዛኛዎቹ ተማሪዎቻችን መልካም አርአያ ያላቸው እና በማንኛውም ጊዜ የመከባበር ባህሪ እንደሚያሳዩ እንገነዘባለን። ሌሎች ከላይ የተገለጹት ድርጊቶች ግን የ MCPS ተማሪዎቻችን ሊረዱት እና ሊቀበሏቸው የሚገባቸው የመማር፣የመከባበር፣ የግንኙነቶች፣ የልህቀት እና የፍትሃዊነት ዋና እሴቶች ነፀብራቅ አይደሉም።

ሁሉም ተማሪዎች የተማሪን ትምህርት ለማበልጸግ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አዎንታዊ እና አክብሮት ያለው የትምህርት ቤት አካባቢ የማግኘት መብት አላቸው። ስለዚህ እባክዎን ከልጅዎ (ከልጆችዎ) ጋር ከላይ የተገለጸውን ዓይነት አጥፊ ባህሪ ከባድነት እንዲረዱ እና ኦንላይን ላይ በአስተዋይነት እና ሃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ እንዲሠሩ ይነጋገሩ እና ያበረታቷቸው። ከልጅዎ (ከልጆችዎ) ጋር እንዲሰሩ እና “የ MCPS የተማሪ ስነምግባር ደንብ እና የተማሪ መብቶች እና ኃላፊነቶች መመሪያ” ለመረዳት ጠቃሚ የሆኑ ሪሶርሶችን ከዚህ በታች አካተናል።

ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ

ጠቃሚ ሪሶርሶች፦

ዲጂታል ዜግነት፦ የአንተ(ቺ) ባህርይ ፋይዳ ይኖረዋል

የተማሪ መብቶች እና ኃላፊነቶች መመሪያ (ይህ ሰነድ በሌሎች ቋንቋዎች)

የ MCPS የተማሪ ስነምግባር ደንብ (ኮድ)Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools