community update

September 8, 2021

የተወደዳችሁ የ MCPS ማህበረሰቦች

የኮቪድ -19 ምልክቶችን ከሚያሳይ ግለሰብ ጋር ንክኪ ለነበራቸው ተማሪዎች የኳራንቲን ፕሮቶኮሎች ወቅታዊ መመሪያን በተመለከተ ለማህበረሰቡ የተላለፈው መልእክት ስጋቶችን እና ተጨማሪ ጥያቄዎችን አስነስቷል። ስለዚህ መመሪያ ተጨማሪ መረጃ መስጠት እፈልጋለሁ፦ ይኼውም ማግለል የሚያስፈልጋቸውን የተማሪዎች ቁጥር ለመቀነስ ስለሚረዱን መሣሪያዎች አንዳንድ አዲስ መረጃን ማካፈል እፈልጋለሁ። ከዚህ ጋር አባሪ የተደረገው የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና ኦፊሰር ከዶክተር ትራቪስ ጋይለስ (Dr. Travis Gayles) የተጻፈ ደብዳቤ ነው።

የሚከተሉት አንዳንድ የእኛ የመከላከያ ስትራቴጂዎች ገጽታዎች ናቸው።


MCPS ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ (DHHS) የተሰጠውን መመሪያ ይከተላል።

የሜሪላንድ ጤና መምሪያ እና የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት መምሪያ፣ CDC የተሰጡትን ምክሮች በመጠቀም፣ የአከባቢ ትምህርት ቤቶችን ዲስትሪክት ለመርዳት መመሪያ ይሰጣሉ። ነገር ግን ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን፣ ልጆችን፣ መምህራን እና ሠራተኞችን ደህንነትና ጤንነት ለመጠበቅ በአካባቢያቸው የሚያስፈልጉትን ተደራቢ የመከላከያ ስትራቴጂዎች ለመወሰን ከአከባቢ ጤና መምሪያዎች ጋር እንዲሠሩ ይመክራሉ።"  ስለመከላከል ለአካባቢ ጤና መምሪያዎች ኦገስት 13 ቀን 2021 የተሰጠው መመሪያ ትምህርት ቤቶች ከአካባቢያቸው የጤና መምሪያዎች ጋር እንዲሠሩ “አጥብቀው ይመክራሉ” በሚለው ተዘርዝሯል። ምክንያቱም የመከላከል ስልቶችና ውሳኔዎችን “ለማህበረሰብ የማሰራጨትና የማስተላለፍ ደረጃዎችን በመከታተል ማሳወቅ አለባቸው። የ COVID-19 ክትባት ሽፋን ከቅድመ መዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል (K-12) ትምህርት ቤቶች ውስጥ ወረርሽኙን ለመለየትና ስርጭቱን ለመግታት፣ የማጣሪያ ምርመራን መጠቀም፣ ምርመራ የተደረገላቸው ልጆችን ዕድሜ እና የተለያዩ የመከላከል ስልቶችን መጠቀም የትኛው የተሻለ ውጤት ማስገኘት እንደሚችል ተጓዳኝ ምክንያቶችን የመለየት ስልት ይጠይቃል።

ኮቪድ -19 ስለመከላከል እና የጤና ፕሮቶኮሎቹን በማዘጋጀት፣ MCPS ከፌዴራል እና ከስቴት ኤጀንሲዎች የተሰጡ ምክሮች ላይ ይሞረኮዛል፥ ነገር ግን በመጨረሻ ከ DHHS የተሰጠውን መመሪያ ይከተላል፥ ኤጀንሲው በማኅበረሰባችን ውስጥ እያንዳንዱን የአከባቢ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጉዳይ ይገመግማል።


የኮቪድ -19 ምልክቶች የታዩበ(ባ)ት ተማሪ ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸውን ለማግለል የተወሰነው በ DHHS መመሪያ መሠረት ነው።

DHHS የስቴት መመሪያዎችን የሚከተል ቢሆንም፣ ኦገስት 13 በስቴቱ ከተጠቀሰው መመሪያ ውጭ በአንድ አካባቢ ላይ ከሚኖረው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር የተለየ አቋም ይወስዳል። በተለይም፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ዋና ጤና ኦፊሰር የሆኑት ዶ/ር ትራቪስ ጋይልስ (Dr. Travis Gayles)“ እንደገለጹት የእኛን መመሪያ ከስቴት መመሪያ የሚለይበት አንድ ሁኔታ፥ የበሽታ ምልክቶች ያሏቸው ሰዎች፣ ኔጋቲቭ የምርመራ ውጤት የሌላቸው ሰዎች፣ ምልክቶችን ለመለየት አማራጭ ምርመራ ከሌለ፣ እና የሚታወቅ የኮቪድ ንክኪ ታሪክ አለመኖር እንደሆነ ገልጸዋል።”

የ ኮቪድ-19 ምልክቶች ያለበትን ተማሪ የቅርብ ግንኙነቶችን/ንክኪዎችን ለማግለል የ MCPS ውሳኔ ከአካባቢያችን የጤና መምሪያ በተሰጠው መመሪያ ላይ የተመሠረተ ነው። ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤት እስኪገኝ ድረስ እነዚህ ተማሪዎች እንዲገለሉ የስቴት መመሪያ ባያዝም፣ DHHS ለነዚህ አይነት የተማሪዎች ምድብ የተለየ ስልት (ስትራቴጂ) ይመክራል።   Dr. ዶ/ር ጌይልስ (Dr. Gayles) እንደሚሉት፥ “በአከባቢው፣ ከእነዚህ ሁኔታዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው ተለይተው የታወቁ ተማሪዎችን ከመረጃ ጠቋሚው የምርመራ ኔጋቲቭ ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ እንዲገለሉ ጠይቀናል፤ ይህ አይነት የአከባቢ ውሳኔ የተሰጠበት ምክንያት ከተለዋዋጭ የኮቪድ ዓይነቶች ተላላፊነት መጨመር እና ገና ለክትባት ብቁ ያልሆኑ ተማሪዎች በመቶኛ ስሌት ጋር በተያያዙ ስጋቶች ላይ የተመሠረተ ነው።


አዳዲስ መሣሪያዎች ማግለልን ለመቀነስ ይረዳሉ።

MCPS በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ላይ ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ከስቴቱ እና ከካውንቲው ፈጣን ምርመራዎችን ይቀበላል። የእነዚህ ምርመራዎች አጠቃቀም እኛ ካለን ሌሎች የጤና አጠባበቅ እርምጃዎች ጋር በመቀናጀት ብዙ ተማሪዎችን በትምህርት ቤት ውስጥ ለማቆየት ይረዳናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። በዚህ ፈጣን የምርመራ ፕሮግራም ትግበራ ላይ ከ DHHS ተጨማሪ መመሪያ እንዳገኘን በተቻለ ፍጥነት መረጃ እንሰጥዎታለን።


ከ DHHS በሚሰጡ መመሪያዎች ላይ በመመርኮዝ MCPS ፕሮቶኮሎችን እያስተካከለ ይቀጥላል።

ሁላችንም የዚህን ወረርሽኝ ተለዋዋጭ ባህርይ ስለተገነዘብን የጤና ባለሥልጣናት በሚያውቁት እና በት/ቤቶች እና በማህበረሰብ ውስጥ በሚከሰቱት አዝማሚያዎች ላይ በመመርኮዝ እርምጃ መውሰድ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝበናል። DHHS ተማሪዎችን ለይቶ የማቆየት ዘዴን ለማስተካከል “ወረርሽኙን እና የክትትል መረጃን ለመቆጣጠር” ቃል ገብቷል። በተጨማሪም፥ ዶ/ር ጌይልስ (Dr. Gayles) DHHS በሁሉም ደረጃ ተግባራዊ እንዲሆን በሠራተኞች መመሪያ ላይ በማካተት መተግበሩን እና የ CDC መመሪያዎችን የሚያሟሉ የቅርብ ንክኪዎችን በተሻለ ለመለየት ከ MCPS ሠራተኞች ጋር በቅርበት መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

MCPS በትምህርት ቤቶች ተማሪዎች መካከል ርቀትን ለመጠበቅ የሚያስችል የፈጠራ መፍትሄዎችን ለማግኘት ቁርጠኛ ከመሆኑም በላይ ይህንን በማድረጋቸው ርእሰ መምህራኖቻችንን እናመሰግናለን።  መምህራን በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ተማሪዎች በአካል እንዲራራቁ የሚያግዙ የፈጠራ ስትራቴጂዎችን በመጠቀም እንዲቀጥሉ እና አብረው የሚሰሩ የተማሪ ቡድኖችንም ጥንቃቄ ማድረጋቸውን በትኩረት እንዲከታተሉዋቸው እናበረታታለን። በምናደርጋቸው ጥረቶች ማግለል የሚያስፈልጋቸውን ተማሪዎች ቁጥር ሊቀንስ ይችላል።


የሚገለሉ ተማሪዎችን ቁጥር በመቀነስ ረገድ የመከላከያ ስትራቴጂዎች ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ።

የእኛ ቀዳሚ ትኩረት ትምህርት ቤቶች ክፍት እንዲሆኑ እና ተማሪዎች እና ሰራተኞች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። እኛ ያስቀመጥናቸው የመከላከያ ስትራቴጂዎች በሙሉ በትምህርት ላይ መስተጓጎልን ለመቀነስ ይረዳሉ። ክትባቶች፣ ጭምብሎች፣ የእጅ መታጠብ፣ የውጭ ቦታዎችን አጠቃቀም ከፍ ማድረግ እና ሲታመሙ ቤት መቆየት የ COVID-19 ስርጭትን ለመቀነስ ይረዳል።

የማህበረሰባችንን ፍላጎት የሚያሟሉ የመከላከያ ስትራቴጂዎችን በማዘጋጀት ከ DHHS እና ከሌሎች የካውንቲ ኤጀንሲዎች ጋር ያለንን አጋርነት እናደንቃለን። በእነዚህ አስቸጋሪ ጊዜያት እንደሁኔታው ስለሚያሳዩት ትዕግስት፣ እና ስለግንዛቤዎ እናመሰግናለን። አብረን መስራታችንን በመቀጠል ተማሪዎቻችን በሳምንት ለአምስት ቀናት በትምህርት ቤት እንዲማሩ በሮቻችንን ክፍት እናደረጋለን።

ከአክብሮት ጋር

Monifa B. McKnight, Ed.D. Interim Superintendent of Schools
ሞኒፋ ቢ. ማክነይት ዶ/ር ተጠባባቂ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት