students arriving at school

 የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

ስለ ኦገስት 24/2021 የትምህርት ቦርድ ስብሰባ እና ትምህርት ቤቶችን ስለመክፈት ማወቅ ያለብዎት 10 ነገሮችን እነሆ። ለ MCPS ተማሪዎች የትምህርት የመጀመሪያ ቀን ሰኞ ኦገስት 30 ቀን 2021 ነው።

ሠራተኞች፣ ወላጆች እና ተማሪዎች የሚወዱትን የትምህርት ቤት-መጀመሪያ-ቀን ፎቶዎች እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። ከት/ቤት የመጀመሪያው ቀን ፎቶዎችን ከወሰዱ በኋላ፣ የመረጡትን ፎቶ በ pio@mcpsmd.org ኢሜል ያድርጉ። ለማህበራዊ ሚድያ፣ ወላጆችና ተማሪዎች በ "Twitter using the hashtag #MCPS1stday" ላይ ፎቶግራፎች መለጠፍ ይችላሉ። ምሥሎቹ በኦንላይን የፎተግራፍ ማሳያ ላይ ይለጠፋሉ።

 1. ጤና እና ደህንነት የእኛ ቀዳሚ ትኩረት ነው። የኮቪድ -19 ስርጭትን ለመከላከል እና የት/ቤት ማህበረሰብ አባላትን ከበሽታ ለመከላከል MCPS  ብዙ-የጤና እና ደህንነት ፕሮቶኮሎችን ተግባራዊ ያደርጋል ። ስትራቴጂዎቹ እንደ አስፈላጊነቱ ከቅድመ መዋዕለ ሕጻናት እስከ 6ኛ ክፍል ተማሪዎችን መመርመር፥ ጭምብሎችን መጠቀም፣ የተሻሻለ ንፅህና አጠባበቅ፣ እና የተሻሻለ የአየር ማናፈሻ መጠቀምን ያካትታሉ። በተጨማሪም፣ ሁሉም ሠራተኞች የክትባት ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ ወይም በየሳምንቱ በ COVID-19 ምርመራ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
 2. ት/ቤቶች በሁሉም ደረጃ ቨርቹወል እንደገና ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ምሽቶችን እና ቨርቹወል ከቤት ውጭ የሚከናወኑ outdoor Open Houses በኤለመንተሪ ደረጃ ያስተናግዳሉ። ይህ የሆነው በመላ ካውንቲው እና በስቴት COVID-19 በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ነው። ለተማሪዎች የሚሰጠው መግለጫ በተያዘለት መርሃ ግብር መሠረት በአካል ይከናወናል።
 3. MCPS ከቅድመ መዋዕለ ሕጻናት እስከ 6ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የ COVID-19 የማጣሪያ ምርመራ ይሰጣል። ቤተሰቦች የናሙና ምርመራ እንደሚደረግ መፍቀድ አለባቸው፤ የዘፈቀደ የተማሪዎች ናሙና በየሳምንቱ ይደረጋል። ይህ የመከላከያ ምርመራ ስለ ኮቪድ-19 ቀደም ብሎ ለይቶ ለማወቅና ለመከላከል ይረዳል።
 4. ትምህርት ቤቶች በምሳ ወቅት በት/ቤት ህንፃዎች ውስጥ እና ከቤት ውጭ ያሉትን ክፍት ቦታዎች አጠቃቀም ለማስፋት እያዘጋጁ ናቸው። ይህ በትምህርት ቤት ካፌዎች ውስጥ የተማሪዎችን ቁጥር ይቀንሳል።
 5. MCPS በሰፕተምበር ወር የተማሪን የመማር ሁኔታ መገምገም ይጀምራል። ከእነዚህ ምዘናዎች የተገኘ መረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ፍላጎት በተሻለ ሁኔታ ለማሟላት ዕቅዶችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
 6. በሜሪላንድ የጤና መምሪያ በተደነገገው መመሪያ መሠረት ተማሪዎች በመነጠል ተገልለው ሲቆዩ የሚያጋጥማቸውን የትምህርት መቋረጥ ለመቀነስ MCPS ጥረት ያደርጋል። በአንደኛ ደረጃ ደረጃ፣ ተነጥለው የሚገኙ ግለሰብ ተማሪዎች ከእኩዮቻቸው በተለየ የጊዜ ሰሌዳ የቀጥታ፣ ቨርቹወል ትምህርት ከአስተማሪ ይቀበላሉ። ክፍሉ በሙሉ የሚገለል ከሆነ መምህሩ ለክፍሉ ቨርቹወል ትምህርት ይሰጣል/ትሰጣለች። በሁለተኛ ደረጃ፣ ተገልለው የሚቆዩ ተማሪዎች በቀጥታ ከአስተማሪዎቻቸው ጋር ለመገናኘት እድሉ ይኖራቸዋል።
 7. "Student Well-Being Teams" ለ 2021-2022 የትምህርት ዓመት ባሉበት ሁኔታ ይቆያሉ። እነዚህ ቡድኖች ለመማር እንቅፋቶችን ለመቀነስ፣ ለቤተሰቦቻቸው በማሳወቅ፣ የተማሪዎችን የአእምሮ ጤና ፍላጎቶች ለመደገፍ እና/ወይም በትምህርት ፕሮግራሙ ውስጥ የማይሳተፉ ተማሪዎችን በማግኘት ለተማሪዎች ወሳኝ ድጋፍ ይሰጣሉ።
 8. ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሠራተኞች እና የኮቪድ -19 የክትባት ክሊኒኮችን ለማስተናገድ MCPS ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ ጋር አጋርነቱን ይቀጥላል። ለሚቀጥሉት 10 ቀናት የታቀዱ በርካታ ክሊኒኮች አሉ። ቀጠሮ አያስፈልግም፣ ነገር ግን ቀጠሮ ለመያዝ ከፈለጉ እባክዎን ከዚህ በታች ያሉትን (links) በመጠቀም ይመዝገቡ፦
  • አርብ ኦገስት 27 ከጠዋቱ 9 a.m. እስከ 6 p.m. Paint Branch High School, 14121 Old Columbia Pike, Burtonsville። እዚህ ይመዝገቡ
  • ረቡዕ ሴፕተምበር 1 ከጠዋቱ 9 a.m. እስከ 6 p.m. Shady Grove Bus Depot, 16651 Crabbs Branch Way in Rockville። እዚህ ይመዝገቡ
  • ቅዳሜ ሴፕተምበር 4 ከጠዋቱ 10 a.m. እስከ 4 p.m. Watkins Mill High School, 10301 Apple Ridge Road in Gaithersburg እዚህ ይመዝገቡ
 9. ወደ MCPS ፋሲሊቲዎች የሚገቡ ሁሉ የክትባት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን የፊት መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀሙ ይጠበቃል። በትምህርት ቤት አውቶቡሶች ላይ የፊት መሸፈኛ ጭምብል መጠቀም ያስፈልጋል። ስለዚህ ጭምብል ይጠቀሙ፥ (MCPS) ብልጥ ይሁኑ! ድርሻዎን ይወጡ። ጤንነትዎን ይጠብቁ።
 10. የስቴት ባለሥልጣናት የትምህርት ሥርዓቱ ይህን እንዲያደርግ ካላዘዙ በስተቀር፣ MCPS የትምህርት ቤት ሕንፃዎችን አይዘጋም፥ ሁሉም ተማሪዎች ወደ ሙሉ ቨርቹወል ትምህርት አይመለም። የስቴት መንግስት በት/ቤት ህንፃዎች ውስጥ የመያዝ አቅምን እንዲቀንስ ካዘዘ፣ MCPS ተማሪዎች በአንዳንድ ቀናት ልዩነት በአካል እየተገኙ እንዲማሩ እና በሌሎች ቀናት ቨርቹወል ትምህርት የሚቀበሉበትን ቅይጥ የማስተማር እቅድ እያዘጋጀ ነው።


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools