boy at desk

Community Update

የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

ስለ ሐምሌ 27 የትምህርት ቦርድ ስብሰባ እና በዚህ መኸር/ፎል ወቅት ምን እንደሚጠብቁ ማወቅ ያለብዎት አምስት ነገሮች እነሆ።

  1. ሁሉም የ MCPS ተማሪዎች እና ሰራተኞች የክትባት ሁኔታቸው ምንም ይሁን ምን   በዚህ መኸር/ፎል ወቅት በትምህርት ቤት ሕንፃዎች ውስጥ ሲገኙ የፊት መሸፈኛ መልበስ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ውሳኔ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከላት እና የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ እንዲሁም የአከባቢው የጤና ባለሥልጣናት ከሚሰጡት ምክሮች ጋር ይጣጣማል። የ COVID-19 በሽታ ቁጥር በመላ አገሪቱ እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ እየጨመረ ሲሆን ከ 12 ዓመት በታች ያሉ ተማሪዎች ክትባት እንደልብ አያገኙም። MCPS በሳምንት ለአምስት ቀናት በአካል ተገኝቶ ለመማር/ማስተማር እየተዘጋጀ ስለሆነ የሁሉንም ተማሪዎች እና የሰራተኞች ደህንነት ማረጋገጥ አለበት። የፊት ጭምብል/ማስክ አስፈላጊንት በመደበኛነት የሚገመገም ሲሆን ዲስትሪክቱ ከፌዴራል ፣ ከክልል እና ከአካባቢ ጤና ባለሥልጣናት የሚሰጠውን መመሪያ ታሳቢ በማድረግ ሊለወጥ ይችላል። የፊት መሸፈኛዎች  ለውጭ አያስፈልጉም ነገር ግን ክትባት ላልወሰዱ ግለሰቦች በጥብቅ ይመከራል።  
  2. ተማሪዎች የፊት መሸፈኛን የትምህርት ቤት አውቶቡሶች ላይ እንዲያደርጉ የጠየቃሉ ይህ በበጋ/ሰመር ትምህርት ቤት ውስጥ ለሚሳተፉ ተማሪዎች የወቅቱን  አሠራር እና ከስቴቱ ለህዝብ ማመላለሻ/ማጉዋጉዋዣ ከወጡ መስፈርቶች ጋር ይጣጣማል።  
  3. ሁሉም ትምህርት ቤቶች  የደወል ጊዜዎችን ፣ የአውቶቡሶች መርሃግብር ፣ በቀን ውስጥ የክፍለ-ጊዜው ርዝመት ፣ የምሳ እና የዕረፍት ሰአትን ጨምሮ ወደ ቅድመ- ኮቪድ መርሃግብራቸው ይመለሳሉ። ትምህርት ቤቶች በዚህ መኸር/ፎል ወቅት ለሁሉም ተማሪዎች በሳምንት ለአምስት ቀናት ለማስተማር 100 በመቶ በሆነ አቅም ይከፈታሉ። ሮስኮ ኒክስ እና አርኮላ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የዲስትሪክቱ የፈጠራ  ትምህርት ቤቶች የትምህርት ዓመቱን ሐምሌ 12  ጀምረዋል። ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱበመከር/ፎል ወቅት ከሁሉም ትምህርት ቤቶች ምን እንደሚጠብቁ ቅድመ እይታ ያሳያል።
  4. ለልምምድ ፣ ዝግጅት እና ግምገማ የሚሆኑ መገልገያዎች ለሁሉም የ MCPS ተማሪዎች ይገኛሉ MCPS መረጃዎችን አዘጋጅቷልተማሪዎች እና ቤተሰቦች ይዘትን እንዲገመግሙ ፣ ክህሎቶችን እንዲለማመዱ እና ለመጪው የትምህርት ዓመት እንዲዘጋጁ የሚረዱ የሂሳብ፣ ማንበብና መጻፍ እና ቋንቋዎች።
  5. ሁሉም ምግቦች በ 2021-2022 የትምህርት ዓመት  ውስጥ ያለክፍያ ይሰጣሉ። MCPS ቁርስ ፣ ምሳ እና እራት  ለሁሉም ትምህርት ቤቶች  በተመደበላቸው የምግብ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ለሁሉም ተማሪዎች ማቅረቡን ይቀጥላል።


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools