boy at desk

Community Update

የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

ስለ ሐምሌ 16ቱ የትምህርት ቦርድ ስብሰባ እና የ 2021-2022 የትምህርት ዓመት ክረምት የ MCPS ዕቅዶች ማወቅ ያለብዎት አራት ነገሮች እነሆ።

  1. የ 2021-2022 የትምህርት ዓመት መጀመሪያ ላይ የጭምብል/ፊት መሸፈኛ መመሪያን ለትምህርት ቦርድ እና ለ MCPS ማህበረሰብ በሐምሌ 27 ያጋራል። የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን ፍላጎት የሚያሟላ እና ደህንነትን የሚያረጋግጥ የጭምብል/የፊት ሽፋን መመሪያን እና ሌሎች የጤና እና ደህንነት ልምዶችን ለመወሰን MCPS ከአከባቢ እና ከክልል የጤና ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየሰራ ነው።
  2. ቦርዱ በ PROSPER 100 ላይ ማሻሻያ ደርሶታል —የ ዶ / ር ሞኒፋ ማክናይት/Dr Monifa McKnight’s vለመጀመሪያዎቹ 100 ቀናቶችዋ ያላት ራእይ እንደ             ጊዜያዊ የበላይ ተቆጣጣሪነትዋ። PROSPER 100 ከስርዓቱ ስትራቴጂካዊ ቅድሚያዎች ጋር የሚስማማ እና MCPS ለተማሪዎች፣ ለሠራተኞች እና ለማህበረሰቡ ለመተግበር በሚያደርጋቸው ጥረቶች ላይ ተማሪዎች የሚገባቸውን የትምህርት ተሞክሮ እንዲያገኙ ለማድረግ ቁርጠኝነትን ያሳያል።
  3. የ PowerPoint ማብራሪያውን ይመልከቱ

  4. MCPS በዚህ ክረምት በመላው ካውንቲ ተከታታይ  ዝግጅቶችን ያስተናግዳል። የ 2021-2022 የትምህርት ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት የ MCPS ሰራተኞች በእነዚህ ዝግጅቶች ላይ ይገኛሉ።
  5. የዝግጀቶች ወቅታዊ መርሃግብር


    ጁላይ 23

    Summer of Peace/Germantown Park Homes Community Center(የጀርመን ታውን ማህበረሰብ ማእከል)ከቀኑ 4 ሰአት እስከ ቀኑ 8 ሰአት18400 Cinnamon Drive, Germantown, MD 20874

    ጁላይ 30

    Summer of Peace/Lakeforest Mall Parking (ሊክ ፎረስት ሞል የመኪና ማቆሚያ) Lot፤ ከቀኑ 4 ሰአት እስከ ቀኑ 8 ሰአት, 701 Russell Avenue, Gaithersburg, MD 20877

    ኦገስት 13

    Summer of Peace/East County White Oak State Park(ዋይት ኦክ የከተማ መናፈሻ) ከቀኑ 4 ሰአት እስከ ቀኑ 8 ሰአት በ 1700 April Lane, Silver Spring, MD 20904

    ኦገስት 21

    የ MCPS ተንቀሳቃሽ ቦታዎች ወደ ትምህርት ቤት  ተመልሰዋል ፣
    ሰአት/ቦታ የሚወሰን ይሆናል

  6. 10 ኛው ዓመታዊ የ MCPS GIVE BACKPacks/የተማሪ ቦርሳ ልገሳ ዘመቻን ለመደገፍ አሁንም ጊዜ አለ። የ 10 ዶላር ልገሳ ለተቸገረ ተማሪ በትምህርት ቤት ቁሳቁሶች የተሞላ የሻንጣ ቦርሳ ለማቅረብ ይረዳል። ልገሳ ተማሪዎች በትምህርታቸው ውስጥ በተሳካ ሁኔታ እንዲሳተፉ አስፈላጊ አቅርቦቶችን እንዲያገኙ ይረዳቸዋል። ለተጨማሪ መረጃ ይህንን ድር ጣቢያ ይጎብኙ  እንዲሁም ለመለገስ።


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools