science class

ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ተመልሰናል!

ጁላይ 8፡2021

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ(MCPS) ማህበረሰብ፡-

የሐምሌ ወር በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በአዲስ የመማር ማስተማር ወቅት ላይ ይውላል።
የተማሪዎቻችንን ማህበራዊ፡ ስሜታዊ፡ አእምሯዊ ጤንነት እና የአካዳሚክ ፍላጎቶችን ለማርካት የበጋ/ሰመር ፕሮግራማችንን በስፋት አስፋፍተናል። ባለፈው ሳምንት የክረምት ትምህርት ፕሮግራሞቻችን ከ 52,000 በላይ ተማሪዎችን ማገልገል የጀመርን ሲሆን ብዙዎቹ በት / ቤታቸው ሕንፃዎች ተመልሰው እየተማሩ እና እያደጉ ናቸው።. በሚቀጥለው ሳምንት በፈጠራ የትምህርት ቀን አቆጣጠር የሚሠሩ ሁለቱ ት / ቤቶቻችን ሮስኮ ኒክስ እና አርኮላ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሕንጻዎች ሲመለሱ እያንዳንዱ ክፍል አስተማሪ ያለበት በሳምንት ለአምስት ቀናት በአካል ተገኝቶ ለማስተማር  በደስታ ይቀበላሉ። ለምናቀርባቸው ልምዶች ቅድመ-እይታ ለሁሉምተማሪዎቻችን በፎል የትምህርት ወቅት መጀመሪያ እናቀርባለን።

በሰኔ 1 መልእክቴ እንዳስተዋልኩት ፣የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ /MCPS ታላቅ የትምህርት ቤት ስርዓት ነው ምክኒያቱም እኛ የተሰራነው ከታላላቅ ሰዎች ነው። እናም የክረምት ፕሮግራማችን ለዚህ ጠንካራ ምሳሌ ነው። ታይቶ በማይታወቅ ቁጥር መምህራን እና ሌሎች የትምህርት ቤት ሰራተኞች የበጋ ፕሮግራምን ለመደገፍ  ተገኝተዋል። እነሱ ከማዕከላዊ እና በትምህርት ቤት ከተመሰረቱ ቡድኖች ጋር በመሆን የ 2021 - 2022 የትምህርት ዓመት የመጀመሪያ ቀን ነሐሴ 30 ሙሉ በሙሉ ወደ ትምህርት ለመመለስ የሎጂስቲክስ እና የትምህርት አሰጣጥ ድጋፎች መኖራቸውን ለማረጋገጥ እየሰሩ ናቸው።

teachers and students with masks

ትምህርት ቤቶቻችን በዚህ ክረምት እያዩ ያሉት የእንቅስቃሴ ጭማሪ እና የመኸር እቅዶች ለ MCPS ትልቅ ዕድል ነው - ይህ ትምህርት ቤት ስርዓት ለሁለት አስርት ዓመታት የሙያ ቤቴ ነበር። ላለፉት 15 ወራት በተፈጠረው ከባድ የመማር ማስተማር ሂደት እና ፈተናዎች ተማሪዎቻችን እና ሰራተኞቻችን ባሳዩት ጽናት ምክንያት ወደዚህ ክረምት ስንገባ ጠንካራ እንሆናለን።

ገደብ የለሽ አቅማችንን ተጠቅመን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ/MCPS ወደ ብልጽግና ገደብ ለማድረስ ጊዜው አሁን ነው። እንደ ጊዜያዊ የበላይ ተቆጣጣሪነት ለመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት እና ለሚቀጥለው የትምህርት ዓመት ትኩረት ይህ ነው፤ብልጽግና። ይህንን ትኩረት ሰሞኑን ከትምህርት ቤት ስርዓት አመራሮች ጋር አካፍያለሁ። ይህ ራእይ - “PROSPER 100” ተብሎ የሚጠራው -ተማሪዎች የሚገባቸውን የትምህርት ተሞክሮ ለመስጠት በምናደርገው ጥረት ለተማሪዎች፣ ለሠራተኞቻችን፣ ለማህበረሰባችን እና እኛ ለራሳችን ማድረግ ያለብንን ቁርጠኝነትን ያሳያል።

PROSPER 100 የሚያካትተው፤

Pለተማሪዎች ቅድሚያ መስጠት
Rገንኙነቶችን ማደስ
Oበሳምንት ለአምስት ቀናት በአካል እገኝቶ ለመማር መከፈት
Sየተማሪዎችን ፍላጎቶች ለማሟላት ሠራተኞችን መደገፍ
Pለወደፊታችን መዘጋጀት
Eለፍትሃዊነት ማስተማር
Rየመከባበር ባህልን እንደገና ማቋቋም

ይህ ራዕይ ለብሩህ መንፈስ ተስፋ እና እኛ ለማንደራረድባቸው መሰረታዊ ግቦች ቁርጠኝነት ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ/MCPS ለሁሉም ተማሪዎች ግሩም የሆነ የመማር ፕሮግራም ያቀርባል፣ ከ MCPS ማህበረሰብ ጋር ትብብርን ለማደስ ቃል ገብቷል፣ ለፍትሃዊነት ጥልቅ ቁርጠኝነት እና ተማሪዎችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ የማያቋርጥ ትኩረት ለተሻለየክረምት ትምህርት ልምድ ይሰጣል!

ቪዲዮ፡ ዶክተር ማክናይት ፕሮስፕር 100 ሲያብራሩ

ይህ ራዕይ ሁላችንንም ይጠይቃል። አብረን የምንሠራውን ሥራ ለማየት በጉጉት እጠብቃለሁ።  የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ/MCPS ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ተመልሶአል!

ከመልካም ወዳጅነት ጋር
ዶክተር ሞኒፋ ቢ ማክናይት/Dr. Monifa B. McKnight
ጊዜያዊ የት / ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ(MCPS)

prosper 100


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools