Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: Dec. 23, 2020


mcps logo

English | español |  中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ | Português


ብሩህ አመለካከት መያዝ፣ እና የወደፊት ብሩህ ተስፋን መሠነቅ

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፡-

ያሳለፍነው ዓመት ከባድ ጊዜ እንደነበር ይታወቃል።

በማህበረሰባችን፣ በስቴት እና በአገሪቱ በጠቅላላ የሚገኙ ቤተሰቦች በ 2020 ብዙ ነገሮች ገጥመዋቸዋል። ለተማሪዎቻችን የቨርቹወል ትምህርት ፈታኝና አዳጋች ነበር፤ ጭምብል መልበስ የየዕለት ተግባር እውነታ ሆኗል፤ ከጓደኞቻችን እና ከቤተሰባችን መገለል ደግሞ በጣም የሚያስከፋ ነው። በርካታ ሠዓታትን በስክሪኖች ፊት ለፊት እናሳልፋለን።

ወደ ክረምት እረፍት እና የአዲስ ዓመት መግቢያ ጫፍ ተቃርበን ሳለ፥ ቀጣዩን አመት በጉጉት አሻቅቤ እመለከታለሁ። አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙንም ወደፊት የተሻለ ጊዜ ይመጣል ብለን መጠበቅ ተፈጥሮአችን ነው። ነገ የተሻለ ቀን ይሆናል። ሰዎች የጋራ ግቦች ላይ ለመድረስ በአንድነት የሚንቀሳቀሱት ለዚህ ነው፤ እኔም ነገ የተሻለ ጊዜ ይመጣል የሚል ተስፋ ሁልጊዜ የሚሰማኝ ለዚህ ነው። ተስፋን መሠነቅ ነገ በእርግጠኝነት የተሻለ እንዲሆን ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስችል ውስጣዊ ግፊት ነው።

በቅርቡ ስለቀጣዩ የትምህርት ዓመት የሥራ ማስኬጃ ባጀት አቅርቤአለሁ። ስለ ወደፊቱ ጊዜ በርካታ ያልታወቁ ነገሮች ቢኖሩም፣ በጀቱ በተስፋ ላይ የተገነባ ነው። እንደማህበረሰብ እና ለተማሪዎቻችን አገልግሎት ሰጪዎች እንደመሆናችን መጠን፣ ወደፊት ስለሚኖረን ጊዜ በአንድነት መቆምና መተባበር አለብን።

የትምህርት ሲስተም/ተቋም እንደመሆናችን መጠን የሚከተሉትን ነገሮች ለማከናወን ተነሳስተናል፦

  • ቨርቹወል ትምህርትን ማሻሻል
  • ማድረግ በምንችልበት ወቅት ተማሪዎችን በሰላም-በጤና ወደ ሕንፃዎቻችን እንዲመለሱ ማድረግ
  • ለሠራተኞች የሙያ ማዳበር እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ መስጠት
  • ለተማሪዎች የአእምሮ ጤንነት እና አካደሚያዊ ድጋፎችን ማግኘታቸውን ማረጋገጥ

ከዚህም በላይ በርካታ ጉዳዮችን ማከናወን።

ተስፋ ማለት ነገሮች አሁን ካሉበት ሁኔታ የተሻሉ እንደሚሆኑ የሚደረግ መሻት ነው። ተስፋ መሰነቅ ማለት አሁን ያለንበትን ሁኔታ ከወደፊቱ ሕይወታችን ጋር በደንብ ማያያዝ ማለት ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና ይህ ማኅበረሰብ ወደተሻለ ቀን እንድንሻገር የሚያደርጉ ሰዎች አሉን።

ለሚያውቋቸው ሰዎች ሁሉ "የተሻለ ነገን" በመመኘት ረገድ እባክዎ ከጎኔ ይሁኑ። በክረምቱ የእረፍት ጊዜ መልካም እረፍት እንድታደርጉና፣ ጭምብሎችን እንድትለብሱ እንዲሁም ደህንነታችሁን እንድትጠብቁ፣ በተለይም ለሚቀርቧችሁ ሰዎች የደስታ ምንጭ በመሆን በበዓል ሰሞን እንድትደሰቱ አበረታታችኋለሁ።

አስተዳዳሪዎችን፣ ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎችን እና መምህራንን ላከናወኗቸው ሥራዎች በሙሉ እጅግ ማመስገንና እውቅና መስጠት እወዳለሁ፤ እነርሱ የማህበረሰባችን የልብ ትርታዎች ናቸው። የሚቀጥለው ዓመት፣ 2021 — ለመጪ ሕይወታችን ሁላችንም በአንድነት ጸንተን መቆም እንደምንችል ተስፋ አደርጋለሁ። ለእርስዎ እና ለሚወዷቸው በሙሉ መልካም በዓል ይሁንላችሁ!

Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of School
ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር)
የት/ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት