Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: Feb. 9, 2021


mcps logo

ወደ ትምህርት ቤት ስለመመለስ እቅዶች
የማህበረሰብ ወቅታዊ መግለጫ

የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞች

ዛሬ፣ ፌብሩወሪ 9/2021 የትምህርት ቦርድ ተማሪዎች ከማርች 1/2021 ጀምሮ በአካል ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ወስኗል። ይኼውም ልዩ ስፔሻል ትምህርት፣ የሙያ ስልጠና እና የቴክኒካል ትምህርት ፕሮግራሞች በሚሰጣቸው ተማሪዎች ይጀመራል። በተጨማሪም ከሱፐርኢንተንደቱ በቀረበው እቅድ መሠረት፣ ከማርች 15/2021 ጀምሮ ተማሪዎች በፈረቃ እየመጡ በአካል እንዲማሩ የትምህርት ቦርድ አፅድቋል። በተጨማሪም ቦርዱ የ 2020-2021 የትምህርት ቤት ካላንደርን በማስተካከል፣ ተማሪዎች ከመመለሳቸው በፊት ሠራተኞች ህንጻዎችን የማዘጋጀት ሥራ እንዲያጠናቅቁ እና በሙያ ማዳበር እንዲሳተፉ ለማስቻል ማርች 8 ትምህርት የማይሰጥበት ቀን እንዲሆን ወስኗል።

የልዩ ትምህርት ፕሮግራሞች
Specific Special Education Programs

March 1 Return

የልዩ ትምህርት ፕሮግራሞች
Specific Special Education Programs
ሣምንታዊ የጊዜ ሠሌዳ
 • የአእምሮ ዝግመት ተጠቂዎች (ኦቲዝም) መዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ፕሮግራም
 • Autism K–12 Program
 • የሚራዘም ፕሮግራም
 • የትምህርት ቤት ማህበረሰብን መሠረት ያደረገ
 • ልዩ ት/ቤቶች

በአካል ተገኝተው የሚማሩበት ጊዜ:

ሰኞ
ማክሰኞ
ሀሙስ
አርብ
ረቡዕ
ቨርቹወል ትምህርት

ቴክኒካዊ ፕሮግራሞች:

ማርች 1 የሚመለሱበት ቀን

ት/ቤቶች ፕሮግራሞች ሞጁሎች
Models

ቶማስ ኤድሰን የቴክኖሎጂ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
(Thomas Edison High School of Technology)

 • አውቶሞቲቭ
 • ኮንስትራክሽን
 • የቁንጅና ሙያ ትምህርት/Cosmetology
 • የጤና እንክብካቤ ሙያዎች
 • የምግብ ቤት ማኔጅመንት
 • በ “A” Day ቀን የጠዋት ተማሪዎች
 • በ “B” Day ቀን የከሰዓት በኋላ ተማሪዎች
 • ሁለቱንም ሣምንት ከማርች 1 – 12
 • በማፈራረቅ ቀኖች ቨርቹወል ትምህርት በሆም ስኩል ይሰጣል
 • እሮብ ቀኖች - ቨርቹወል ትምህርት
 • ቅይጥ የማስተማር ሞጁሎች

ሴኔካ ቫሊ፣ ጌትስበርግ፣ ደማስከስ፣ ፔይንት ብራንች
(Seneca Valley, Gaithersburg, Damascus, Paint Branch)

 • ሁለቱንም ሣምንት ከማርች 1–12 ይሳተፋሉ
 • በተመደቡበት የመማሪያ ክፍለጊዜዎች፣ በየፕሮግራሙ የቅይጥ ሞጁሎች ትምህርት ክፍሎችን በአካል ይሳተፋሉ

የሚመለሱበት ፈረቃ (አመቺ ቀናት/Optimal Dates)

ቡድን 1.1 (ማርች 15)
 • የተለያዩ ፕሮግራሞች እና የልዩ ትኩረት ማህበረሰብ
 • Discrete Programs and Special Populations
 • CTE ፕሮግራሞች
 • METS
 • CREA
 • አማራጭ ፕሮግራሞች
 • ከK እስከ 3 ክፍሎች

[የማገገሚያ እቅድ/Recovery Guide ያንብቡ]

{የቦርድ ውሳኔ/Board resolution ያንብቡ}

ተማሪዎች በሚመለሱበት ጊዜ፣ በትምህርት ቤት ህንጻዎች ላይ ቀደም ሲል ከነበራቸው ልምድ የተለየ ገጽታ እንዳለው ይሰማቸዋል። የፊት መሸፈኛ፣ አካላዊ ርቀት መጠበቅ እና አዘውትሮ እጅን መታጠብ አስፈላጊ ነውየኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቀነስ። በተጨማሪም፣ ተማሪዎች በምን ያህል ጊዜ በትምህርት ቤት እንደሚማሩ እና ከአስተማሪዎቻቸው፣ ከሌሎች ሠራተኞች እና ከጓደኞቻቸው ጋር እንዴት እንደሚገናኙ ጭምር የተለየ ይሆናል።

በቦርድ ስብሰባ ወቅት፣ ወላጆች፣ ተማሪዎች እና ሠራተኞች በአካል ተገኝተው በሚማሩበት ጊዜ ምን መጠበቅ እንዳለባቸው ከሠራተኛ መግለጫ ተሰጥቷል። ፊትለፊት ከሚሰጣቸው ትምህርት በተጨማሪ፣ ተማሪዎች የሚከተሉት ተሞክሮዎች ይኖራቸዋል፦

 • አካደሚያዊ ጣልቃ ገብነት ወይም በአነስተኛ ቡድን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስነጥበባት/ሒሳብ ይማራሉ
 • ጽንሰ-ሐሳቦችን ድጋሚ ይማራሉ እና ይከልሳሉ
 • በመቧደን የክፍል ውይይቶች ወይም እኩያ-ከ-እኩያ ጋር በመተባበር የመማር እድሎች ይኖራቸዋል
 • በመናፈሻ፣ የምሳ እረፍት እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ላይ የመሳተፍ እድል ይኖራቸዋል።
 • የማህበራዊ ስሜት ማዳበር ትምህርት ወይም ደህንነት እንቅስቃሴዎች (ማለት፦ የመማሪያ ክፍል ማህበረሰብ ግንባታ)

የግንዛቤና የአረዳድ ስህተቶችን መፍትሔ መስጠት

በትምህርት ቤት ህንጻዎች ውስጥ ስለሚሰጥ ትምህርት የተሳሳተ አረዳድ በተመለከተ ከሠራተኛ ለቦርዱ የተጣራ መረጃ-መግለጫ ተሰጥቷል፦

የተሳሳተ ግንዛቤ #1: ተማሪ ህንጻ ውስጥ ከፓራ ኤጁኬተሮች ጋር ብቻ ይገናኛል-ትገናኛለች የሚል አረዳድ

ሐቁ/FACT—በአካል የሚሳተፉ ተማሪዎች ከአስተማሪዎች እና ከሌሎችም የሥራ ባልደረቦች ጋር ግንኙነት ይኖራቸዋል።

የተሳሳተ ግንዛቤ #2: ርእሰመምህራኑ በትምህርት በት ህንጻ እንዲሰጥ “የሚመርጡት” አንድ አይነት የማስተማር አቀራረብ ነው የሚለው ሲሆን

ሐቁ/FACT—ተማሪዎች በቀን በርካታ የማስተማር አቀራረብ ይኖራቸዋል።

የተሳሳተ ግንዛቤ #3: በአካል መማር ማለት እንደው "ህጻን እንደመንከባከብ/babysitting" የሚለው ሲሆን

ሐቁ/FACT—እንደመደበኛው "brick-and-mortar" አይነት ተሞክሮ ባይሆንም፣ ተማሪዎች በአካል ተገኝተው በሚማሩበት ጊዜ ከበርካታ ሠራተኞች እና ከእኩዮቻቸው ጋር በሚኖራቸው ተሳትፎ ይጠቀማሉ።

{ይመልከቱ: ስለ ትምህርት አሰጣጥ ተሞክሮዎች መግለጫ የሚሰጥ ቪድኦ እና ስለ ፈረቃ መርሃግብር መግለጫ የሚሰጥ ቪድኦ } 

ቀጣዩ ምንድነዉ

በ 1ኛ እና 2ኛ ፈረቃዎች የሚገኙ ቡድኖች የሚመለሱባቸው ቀኖች እንደሚከተለው ይሆናል:

የሚመለሱበት ፈረቃ (አመቺ ቀናት/Optimal Dates)

ቡድን 1.1 (ማርች 15) ቡድን 1.2 (ከኤፕሪል 6 አስቀድሞ)
 • የተለያዩ ፕሮግራሞች እና የልዩ ትኩረት ማህበረሰብ
 • Discrete Programs and Special Populations
 • CTE ፕሮግራሞች
 • METS
 • CREA
 • አማራጭ ፕሮግራሞች
 • ከK እስከ 3 ክፍሎች
 • የተለያዩ ፕሮግራሞች እና የልዩ ትኩረት ማህበረሰብ
 • Discrete Programs and Special Populations
 • ተጨማሪ CTE ፕሮግራሞች
 • 4–5 ክፍሎች
 • ቅድመ ምዋእለ ህጻናት
 • Pre-kindergarten
 • 6ኛ ክፍል
 • 12ኛ ክፍል
ቡድን 2.1 (ከኤፕሪል 19 አስቀድሞ) ቡድን 2.2 (ከኤፕሪል 26 አስቀድሞ)
 • 8ኛ ክፍል
 • 9ኛ ክፍል
 • 11ኛ ክፍል
 • 7ኛ ክፍል
 • 10ኛ ክፍል

እያንዳንዱን ትምህርት ቤት የሚመለከቱ እቅዶች ፌብሩወሪ ውስጥ ለቤተሰቦች መረጃ ይደርሳቸዋል። የማገገሚያ እቅድ መመሪያው ስለ ቨርቹወል እና በአካል ተመልሰው የሚማሩበትን ተሞክሮዎች፣ ከካሪኩለም ባሻገር ስላሉት አክቲቪቲዎች እና አትሌቲክስ፣ እና አፈጻጸሞችን፣ ደህንነት እና መገልገያ ሎጂስቲክስ የእቅዳችንን አጠቃላይ ገጽታ ይገልጻል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ተማሪዎች በተቻለ ፍጥነት ዳግመኛ በሰላም እንዲመለሱ ለማድረግ ቁርጠኛ ነው። ነገር ግን፥ የወረርሽኙን አመጣጥና አካሄድ ለመተንበይ ስለማንችል፣ አሁን የሚታየው የአዳዲስ ህሙማን መቀነስ ሁኔታ ከተለወጠ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተማሪዎቻችንን እና ፊትለፊት የሚጋፈጡ ሠራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል የፀደቀውን መርሃግብር ክለሳ ማድረግ ያስፈልግ ይሆናል።

Montgomery County Public Schools
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ