Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: Feb. 5, 2021


mcps logo

English | español |  中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ | Português


ወደ ትምህርት ቤት የመመስ እቅድን የሚመለከት የማህበረሰብ ወቅታዊ መግለጫ

የተወደዳችሁ ወላጆች፣ አሳዳጊዎች፣ ሰራተኞች እና ተማሪዎች ፦

ስለዲስትሪክቱ ወደ ት/ቤት የመመለስ እቅድ ጃኑወሪ 29፣በተሰጠው ወቅታዊ መግለጫ በገለጽነው መሠረት፤ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለቦርዱ ወቅታዊ መረጃ ተሰጥቷል። የ ጃኑወሪ 28 መግለጫ ያተኮረው፤ በአካል ለመማር መመለስን ለመረጡት ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ደህንነት፣ የስራና የአገልግሎቶች እቅድና ዝግጅትን በሚመለከት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

የዚያን ውይይት ቪድኦ እዚህ መመልከት ትችላላችሁ።

ወደፊት ምን ይጠብቀናል?

ፌብሩወሪ 9፣ ስለ ተማሪዎች በአካል መመለስ እና ቨርቹወል መማር እቅድን በተመለከተ ወላጆች፣ ተማሪዎች እና ሠራተኞች ምን መጠበቅ እንደሚችሉ ጭምር ዋና ዋና ሃሳቦችን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የበለጠ መረጃ ለቦርድ ያቀርባል። ቦርዱ በአካል ለመማር የመመለሻ ጊዜን ይወስናል።ተማሪዎች በአካል ወደ ት/ቤት ከመመለሳቸው በፊት ሠራተኞች ህንጻዎችን የማዘጋጀት ሥራዎቻቸውን እንዲያጠናቅቁ እና በሙያ ማዳበር ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ ማርች 8 ትምህርት የማይሰጥበት ቀን እንደሚሆን ቦርዱ በት/ ቤት ካላንደር ላይ ማስተካከያ ያደርጋል።

ምን መሰማት አለበት

ወደ ትምህርት ቤት ህንጻዎች ስለመመለስ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሠራተኞች ማርች 1/2021፣ የሚያቀርቡትን ሃሳብ:

  1. በልዩ ትምህርት ፕሮግራሞች የሚገኙ ተማሪዎች (የአእምሮ ዘገምተኛነት ያላቸው ከመዋእለ ህጻናት - 12ኛ (K-12 ) ፕሮግራም፣ የኤክስቴንሽን ፕሮግራም፣ የት/ቤት ማህበረሰብን መሠረት ያደረጉ ፕሮግራሞች እና ልዩ (ስፔሻል) ትምህርት ቤቶች በልዩ የሙያ እና የቴክኒክ ትምህርት ፕሮግራሞች የሚገኙ ተማሪዎች

በተጨማሪም ማርች 15 እንደሚጀመር በተያዘው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት፣ ከምዋእለ ህጻናት እስከ 2ኛ ክፍል (ከመዋእለ ህጻናት እስከ 3ኛ ክፍል በታይትል I እና የልዩ ትኩረት ትምህርት ቤቶች (Title I and Focus Schools) የሚገኙ ተማሪዎች ስለሚመለሱበት ሁኔታ ሠራተኞች ዝርዝር መረጃ ይሰጣሉ። እንደዚሁም ሠራተኞች ከመዋእለ ህጻናት እስከ 3ኛ ክፍል ስለሚገኙ ተማሪዎች (ማርች 15 እንደሚጀመር በጊዜ ሠሌዳ እንደተቀመጠው (ፈረቃ I. I) ስለሚመለሱበት ሁኔታ ሠራተኞች ዝርዝር መረጃ ይሰጣሉ። ስለ ፈረቃ I. 2 ገና አልተወሰነም።
የሁሉንም ተማሪዎች እና የሠራተኞችን ደህንነት ለማረጋገጥ ሲባል፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በእያንዳንዱ ፈረቃ የሚመለሱትን ተማሪዎች ብዛት እና በመማሪያ ክፍሎች የሚመደቡትን የተማሪዎች ቁጥር ውስን ያደርገዋል። የራሳቸው ፈረቃ እስከሚጀመር ድረስ ተማሪዎች ቨርቹወል ብቻ በመማር ይቆያሉ።

ማርች 15—በፈረቃ መመለስ ይጀመራል

phases

* የ የፈረቃዎችን ቀጣይ ሁኔታ የሚወስነው የቀዳሚዎቹ ፈረቃዎች በተሳካ ሁኔታ መተግበር እና የካውንቲው የጤና እና የደህንነት ሁኔታ በሚፈቅድልን መጠን ይሆናል።

የተማሪ ተሞክሮ

ተማሪዎች በአካል ለመማር በሚመለሱበት ወቅት፣ በትምህርት ቤት ህንጻዎች ውስጥ በፊት ከነበራቸው ልምድ በጣም የተለየ ስሜት ሊፈጥርባቸው ይችላል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቀነስ የፊት መሸፈኛ፣ አካላዊ ርቀት መጠበቅ እና አዘውትሮ እጅ መታጠብ አስፈላጊ ነው።

በተጨማሪ፦ ተማሪዎች በምን ያህል ጊዜ በአካል በት/ቤት እንደሚማሩ እና ከአስተማሪዎቻቸው ጋር፣ ሌሎች ሠራተኞች እና ጓደኞቻቸው ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በሦስት ቁልፍ ምክንያቶች የተለየ ይሆናል።

ቦታ —የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከሎች (CDC) የተሰጡ አካላዊ ርቀትን የመጠበቅ መመሪያ ይከተላል። ይህ ማለት በመማሪያ ክፍሎች ወይም በትምህርት ቤት ህንጻዎች ውስጥ በጣም በቁጥር አነስተኛ ተማሪዎች ብቻ ሊገኙ ይችላሉ ማለት ነው። በእነዚህ የጤና አጠባበቅ መመሪያዎች መሠረት፣ የትምህርት ቤት አሠራር እና የቦታ አጠቃቀም ማስተካከያ ተደርጎባቸዋል።

የሠራተኛ ምደባ—ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ህንጻዎች በሚመለሱበት ጊዜ በርካታ አስተማሪዎች፣ ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች እና አስተዳዳሪዎችም የሚመለሱ መሆናቸው ቢታወቅም፣ በቦታ ውስንነት ምክንያት አንዳንዶቹ ሠራተኞች (በ CDC እና በካውንቲው መመሪያ) እና በሜዲካል/የጤና ሁኔታ ምክንያት ወደ ት/ቤት ህንጻዎች አይመለሱም።

የቤተሰብ ምርጫ የዳሰሳ ጥናት ውጤቶች —በአጠቃላይ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በአካል ወደ ት/ቤት ለመመለስ የመረጡ ቤተሰቦች ቁጥር በጣም ይለያያል። በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎቹ ፍላጎት በጣም ጥቂት ሲሆን በአንዳንዶቹ ደግሞ በጣም ከፍተኛ ፍላጎት ይታያል። ትምህርት ቤቶች በአካል ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ እቅድ በሚያዘጋጁበት ጊዜ እነዚህ ቁጥሮች እንደ ግብአት ተወስደዋል።

በእነዚህ ነባራዊ ሁኔታዎች ምክንያት፣ ትምህርት ቤቶች አንዳንድ የክፍል ደረጃዎችን በየሣምንቱ አራት ቀኖችን በአካል እየመጡ እንዲማሩ ሊያደርጉ ይችላሉ፣ ሌሎች ክፍሎች ደግሞ በቀጣዩ ሣምንት ፈረቃ አራት ቀን ሊማሩ ይችላሉ (እሮብ ቀኖችን ለሁሉም ተማሪዎች ቨርቹወል የሚማሩበት ቀን ይሆናል)። የፈረቃዎቹን ሁኔታ በሚመለከት ት/ቤቶች በመጪዎቹ ሣምንታት ለቤተሰቦች ዝርዝር መረጃ ይሰጣሉ።

ለተማሪዎች ትምህርት ስለሚሰጥበት ሁኔታ

ቨርቹወል-ብቻ ትምህርት ላይ የሚቆዩ ተማሪዎች በተዘጋጁላቸው አውዶች (established platforms) ከአስተማሪዎቻቸው እና ከክፍል ጓደኞቻቸው ጋር ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ። በአካል መጥተው ለመማር የሚመለሱ ተማሪዎች እንደየፍላጎታቸው ለማሟላት የተለያየ አይነት የትምህርት አቀራረብ ይኖራቸዋል። ለሁሉም ተማሪዎች እጅግ የላቀ እና ሚዛናዊነትን የጠበቀ አዲስ የአፈጻጸም እና የማስተማር ሂደትን ተግባራዊ ለማድረግ ትርጉም ያለው ማስተካከያዎችን ማድረግ ያስፈልጋል።

በአካል እየመጡ ለሚማሩትም ሆነ ቨርቹወ ለሚማሩ ተማሪዎች የሚሰጡ ትምህርቶችን ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት፣ ትምህርት ቤቶች ቀጥታ ማስተማርን፣ ለተለያዩ ክፍሎች በአንድ ጊዜ ማስተማር እና ለቨርቹወል የማስተማር ሞዴሎች ድጋፍ መስጠትን በህብር እንደሚጠቀሙ እባክዎ ልብ ይገንዘቡ። ተማሪዎች ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በፊት ያደርጉት እንደነበረው፥ ከአስተማሪዎች፣ ከድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች እና ከአስተዳዳሪዎች ጋር በቅርበት ይሠራሉ።

ለእኔ ልጅ ይሄ ምን ማለት ነው?

ፌብሩወሪ እስከሚጠናቀቅ ስለ መማሪያ ክፍሎች እቅድ ዝርዝር መረጃዎችን ለቤተሰቦች ይገለጻል። ወደ ትምህርት ቤት የሚመለሱት ተማሪዎች ብዛት፣ የሠራተኞች አመዳደብ እና የትኞቹ የክፍል ደረጃዎች እንደሚሆኑ ዝርዝር ሁኔታው በእርስዎ ልጅ ትምህርት ቤት አፈጻጸም ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር እባክዎ ይገንዘቡ።

ምን ማድረግ እንደሚችሉ

ከትምህርት ቤትዎ ጋር የሚያደርጉትን ክትትል እንዲቀጥሉ፣ ከእርስዎ ልጅ ትምህርት ቤት የሚተላለፍ የግንኙነት መረብ እና አፈጻጸሞችን እንዲመለከቱ፣ ለቤተሰቦች ከዲስትሪክቱ የሚተላለፉ መልእክቶችን በሙሉ እንዲያነቡ እና ቪድኦዎችን እንዲመለከቱ አበክረን እናበረታታለን። ወደ ትምህርት ቤት መመለስ ምን ሊመስል እንደሚችል የተሻለ ግንዛቤ ለማግኘት እነዚህ ነገሮች ይረዱዎታል።

ሀሳብዎን ለመግለጽ ይፈልጋሉ? ለእርስዎ የሚያስፈልግዎት ምን እንደሆነ እንዲገልጹልን ይህንን በይነመረብ www.MCPSSubmitFeedback.org ይጎብኙ።

Montgomery County Public Schools
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ

ሪሶርሶች
ስለ ደህንነት ተሞክሮዎችን የሚገልጽ ቪድኦ
ስለ አካላዊ ርቀት የሚገልጽ ቪድኦ
በአካል ስለሚካሄድ አትሌቲክስ ቪድኦ