Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: Jan. 29, 2021


mcps logo

English | español |  中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ | Português


የተከበራችሁ ወላጆች፣ አሳዳጊዎች፣ ሰራተኞች እና ተማሪዎች

በአካል ወደትምህርት ስለመመለስ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS’) እቅድ ላይ ለመወያየት የትምህርት ቦርድ ትላንትና (ጃኑወሪ 29) ስብሰባ አድርጓል። ተማሪዎችን በአካል ተገኝተው እንዲማሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩል (MCPS) ሠራተኛ የጤና አጠባበቅን በሚመለከት በካውንቲው ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ፣ ስለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩል (MCPS) ሠራተኞች የክትባት እቅድ እና ተማሪዎችን እና ሠራተኞችን ለመመለስ የትምህርት ቤት ህንፃዎች መዘጋጀታቸውን ለማረጋገጥ እየተሠሩ ያሉ ስራዎችን በሚመለከት ከ MCPS ባልደረባ ወቅታዊ መግለጫ ተሰጥቷል። በዚህ ስብሰባ ትምህርት ቤቶችን እንደገና የመክፈት እቅድን የሚመለከት እርምጃ አልተወሰደም።

እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን እንደገና ስለመክፈት ከገቨርነር ላሪ ሆገን (Governor Larry Hogan) ስለተሰጠው ወቅታዊ መግለጫ ቦርዱ ውይይት አድርጓልMCPS የልዩ ትምህርት አገልግሎት የሚሰጣቸውን ተማሪዎች እና የተለየ የቴክኖሎጂ ሙያ ትምህርት (CTE) ፕሮግራሞች ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን ቡድን ማርች 1 ለመመለስ በ MCPS የታለመ መሆኑን ሱፐርኢንተንደንት ጃክ ስሚዝ/Superintendent Jack Smith ከቦርድ ጋር ተነጋግረዋል። በዚህ እቅድ ዙርያ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ፌብሩወሪ 9 የበለጠ መረጃ ለቦርዱ የሚያቀርብ ሲሆን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተጨማሪ የተማሪ ቡድኖችን ከማርች 15 ጀምሮ በፈረቃ በሚመለሱበት እቅዱ እንደቀጠለ ነው።

(በፓወርፖይንት የቀረበውን የስብሰባ ሪኮርድ ይመልከቱ።)

ጤና፣ ደህንነት እና የሥራ እንቅስቃሴ አገልግሎት
በስብሰባው፥ ስለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS’) የማገገም ጥረቶችን በሚመለከት በርካታ የቪድኦ ቅኝቶችን ቦርዱ ገምግሟል/ተመልክቷል፤ እነዚህም የሚያካትቱት፦

የአትሌቲክስ ወቅታዊ ሁኔታ
እንደገና የመክፈት ስትራተጂ አካል እንደመሆኑ መጠን፣ ከጃኑወሪ 29 ጀምሮ በፎል ለሚካሄዱ ስፖርቶች በ "ParentVue" አማካይነት ምዝገባ ክፍት ይሆናል። የመጀመሪያው ታርጌት/target ፌብሩወሪ 27/2021 ይጀመራል።

(ስፖርቶች በሚካሄዱበት ወቅት ስለ አካላዊ ርቀት እና ደህንነት ቪድኦ ይመልከቱ።)

ወደፊት ምን ይጠብቀናል?
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS’) የማገገሚያ እቅድ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ቦርዱ ፌብሩወሪ 9 እና ፌብሩወሪ 23 በድጋሚ ይሰበሰባል። ዝርዝር የጊዜ ማእቀፍ፣ የተማሪዎች በአካል የመገኘት ተሞክሮ ምን ሊመስል እንደሚችል (ለምሳሌ፦ ተማሪዎች በሣምንት ስንት ቀኖችን በአካል ተገኝተው ይከታተላሉ፣ የትምህርት አሰጣጥ ሞዴሎች፣ ወዘተ) ከፌብሩወሪ 9 ስብሰባ ቀጥሎ ይገለጻል።

Montgomery County Public Schools
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ