Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: Jan. 12, 2021


mcps logo

English | español |  中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ | Português


የቨርቹወል ትምህርት እስከ ማርች 15 ድረስ እንዲቆይ የትምህርት ቦርድ መርጧል።

የተወደዳችሁ ወላጆች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ተማሪዎች

የጤና አጠባበቅ ሜትሪክስ መሟላት ያለበትን ሁኔታ ወይም የክትባት ስርጭትን በሚመለከት የጤና ጥበቃ መመሪያን መጠበቅ በማስፈለጉ ምክንያት በአነስተኛ ቡድን ተማሪዎችን በአካል ለመማር እንዲመለሱ የሚጀመርበትን ጊዜ ከፌብሩወሪ 1/2021 ወደ ማርች 15/2021 እንዲዘገይ/እንዲቆይ ማክሰኞ፣ ጃኑወሪ 12 የትምህርት ቦርድ ወስኗል።, በዚህ ወቅት በካውንቲው የኮቪድ-19 አዳዲስ ህሙማን ብዛት እና የምርመራ ውጤቶች በካውንቲው እና በስቴት ከተደነገገው ወለል በከፍተኛ ደረጃ የሚበልጥ ነው።  COVID-19 new case rate and test positivity in the county
ፌብሩወሪ 1 በአካል ወደ መማር ማስተማር ለመመለስ ባለመቻላችን በርካታ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦችን እንደሚያሳዝናቸው እንገነዘባለን። የተማሪዎች እና የሠራተኞች ደህንነትና ጤንነትን የመጠበቅ ሁኔታ በአካል ለመማር ማስተማር የመመለሳችንን ሁኔታ የሚወስነው ከመሆኑም በላይ በዚህ ወቅት ያሉት ቁጥሮች በአሁኑ ጊዜ በአካል የመመለስን ሁኔታ የሚያስደፍሩ አይደለም።.

{Read the Resolution}

ለተማሪዎቻችን ቨርቹወል መማር ማስተማር ተሞክሮአችንን አጠናክረን እንቀጥላለን። በቦርድ ስብሰባችን ወቅት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሠራተኞች በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያተኮረ ለሁሉም ተማሪዎች የመማር ጥረታቸውንና ተሞክሮዎቻቸውን በተሻለ መልኩ የሚረዳ በመጪዎቹ ሣምንታት ሊተገበሩ የሚችሉ በርካታ ማሻሻያዎችን አጋርተውናል።
እነዚህ ማሻሻያዎች የሚያካትቱት፦

  • የሚያታግላቸው ተማሪዎችን የመርዳት አገልግሎት መስጠት ላይ ማተኮር
  • የእሮብ ቀኖችን ቨርቹወል የሚገኙባቸውን ጊዜያት አካደሚያዊ እና ማህበራዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች መጠቀም
  • በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የሚወሰዱ ኮርሶችን ብዛት የማቅለል እድል ለመስጠት በሠመር ወይም ወደፊት በሚኖሩ ሴሚስተሮች ኮርሶችን በመቀናነስ እንዲወስዱ ማድረግ request an abbreviated schedule
  • በፊደል ከሚሰጠው ውጤት ይልቅ ተማሪዎች ዘና ባለ ሁኔታ እስከ ሁለት ኮርሶችን መውሰድ እንዲችሉ ማድረግ የክሬዲት/ክሬዲት የሌለው (አልፏል/ወድቋል - አልፋለች/ወድቃለች በመባል የሚታወቀውን)
  • ለ “Advanced Placement and International Baccalaureate courses” ጨምሮ በቅዳሜ ቀኖች ተጨማሪ የማስተማር ጊዜዎችን መስጠት
  • የማስጠናት እና የቤት ሥራ ድጋፍ የመስጠት አማራጮችን መስጠት
  • ቨርቹወል የመማር ማስተማር ተሞክሮን ለማጠናከር እንዲረዳ ለሠራተኞች ተጨማሪ የሙያ ማዳበር ስልጠና መስጠት

በሁለተኛ ሴሚስተር በእነዚህ አማራጭ እድሎች ተጠቃሚ ለመሆን እና ለመመረቅ የሚያበቃ መስፈርት እንደሚሟላ ለማረጋገጥ እና የድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እቅዶችን ማሟያ እርምጃዎችን የጊዜ ሠሌዳዎች ለማመቻቸት እና ለማስተካከል ተማሪዎች/ወላጆች ከትምህርት ቤቶቻቸው ካውንስለሮች ጋር መነጋገር ይኖርባቸዋል።

እነዚህ ለሁለተኛው ሴሚስተር የሚደረጉት ማስተካከያዎች አሁን ተስተካክለው ባሉት የጊዜ ሠሌዳዎች ላይ ተጨማሪ የሚደረጉ ናቸው adjustments that are already in place የሁለተኛ ሴሚስተር የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ የከሪኩለም፣ መመዘኛዎች እና የውጤት አሰጣጥ።

በተጨማሪ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ፎል ላይ ስለሚካሄዱ የስፖርት እንቅስቃሴዎች የእቅድ ዝግጅቱን የሚቀጥል ሲሆን በትምህርት ቤቶች መካከል ስለሚካሄዱ የአትሌቲክስ እና ከከሪኩለም ባሻገር ስለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በመጪዎቹ ሣምንታት መግለጫዎች ይሰጣሉ።

{Read the Resolution}

ቀጣዩ ምንድነው
በማህበረሰባችን ውስጥ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለማስቆም እኛ ሁላችን በጋራ ተባብረን መስራት ይጠበቅብናል። ማርች 15 በጤናማ ሁኔታ በአካል ወደትምህርት መመለስ የጤና አጠባበቅ ሜትሪክሱ ሁኔታ ይፈቅድ እንደሆነ ለማረጋገጥ ቦርዱ ፌብሩወሪ 23/2021 እንደገና ይሰበሰባል። ፌብሩወሪ 23 የሚካሄደውን የትምህርት ቦርድ ውሳኔ አስመልክቶ የበለጠ መረጃ ለማህበረሰቡ እንዲደርስ ይደረጋል። ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ህንጻዎች የሚመለሱበት ሁኔታ ምን ሊመስል እንደሚችል አጠቃላይ ሁኔታዎችን ለመዳሰስ እና ለማረጋገጥ በሚቀጥሉት ጥቂት ሣምንታት፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች ጋር በቅርበት መሥራቱን ይቀጥላል።
ለተማሪዎቻችን በቀጣይነት ስለሚያደርጉላቸው ድጋፍ እናመሰግናለን።.

Montgomery County Public Schools