Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: Dec. 4, 2020


mcps logo

English | español |  中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ | Português


አስፈላጊ የሆነ የማህበረሰብ ወቅታዊ መረጃ —የትምህርት ቦርድ ወደ ት/ቤት ስለመመለስ ዲሰምበር 15 የመጨረሻ እርምጃ ይወስዳል

የተከበራችሁ ወላጆችና አሳዳጊዎች፣

የትምህርት ቦርድ ዲሰምበር 3 ላይ ተማሪዎች በአካል ለመማር ወደ ት/ቤት ስለመመለስ የዲስትሪክት ማእቀፍ በሚመለከት ዲሰምበር 15 በሚያደርገው ስብሰባ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት አስተላልፏል። የጤና አጠባበቅ ሜትሪክሱ የሚሟላ ከሆነ አንዳንድ ተማሪዎች ከጃኑወሪ 12/2021 ጀምሮ በአካል ተመልሰው እንዲማሩ ዲስትሪክቱ ያዘጋጀውን የማእቀፍ እቅድ በሚመለከት በኖቨምበር 10፣ ቦርዱ በጊዜያዊነት ማጽደቁ ይታወቃል። በ MCPS እቅድ የመጀመሪያ ቅድሚያ የተሰጠው በተለይ ስፔሻል ትምህርት ለሚሰጣቸው ተማሪዎች እና የቴክኖሎጂ ሙያ ትምህርት ፕሮግራሞች/Career Technology Education (CTE) programs ነው። በርካታ ቁጥር ያላቸው የተማሪዎች ቡድኖች ከፌብሩወሪ 1/21 ጀምሮ በፈረቃ ይጀምራሉ። ቦርዱ ዳግም ስለመክፈት የቀረበውን ሜትሪክስ እንደገና እንዲገመግም እንዲሁም ተማሪዎች እንዲመለሱ የቀረበውን የቅደም ተከተል ሁኔታ እንደገና እንዲጤን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) ጠይቋል። በአነስተኛ እድሜ የሚገኙ ተማሪዎቻችንን በፍጥነት ለመመለስ የሚያስችል ስትራቴጂ ዲስትሪክቱ እንዲያጠና ጠይቀዋል።

MCPS የቤተሰብ ምርጫ ዳሰሳው ቀነ ገደብ እስከ ሰኞ፣ ዲሰምበር 7 እንዲራዘም አድርጓል። በዚህ እጅግ አስፈላጊ በሆነ ዳሰሳ፣ ልጆቻቸው ቨርቹወል ብቻ ሞዴል በመማር እንዲቆዩ ወይም በአካል እየመጡ ለመማር ወላጆች ምርጫዎቻቸውን ለመግለጽ ይችላሉ። ዳሰሳውን ያላጠናቀቁ ከሆነ፣ እባክዎ ዛሬውኑ በዚህ አውታረመረብ ላይ ይሙሉ www.mcpsfamilypreference.org
ስለ ዳሰሳው ጥያቄዎች ካሉዎት በዚህ አውታረመረብ mcpsinfo@mcpsmd.netመገናኘት ይችላሉ።
ጠቃሚ ማሳሰቢያ፦ እስከ ዲሰምበር 7 ዳሰሳውን ካልሞሉ የእርስዎ ልጅ ቨርቹወል ትምህርት ላይ ብቻ ይቀጥላል/ትቀጥላለች።

ወደ ሕንጻዎች ከተመለስን በኋላ የትምህርት አሰጣጡ፣ ለተማሪዎች የተለየ እንደሚሆን፣ የአቅም ውስንነት፣እና በቂ ሠራተኞች የመገኘታቸው ሁኔታ የሚወስን መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ነው። ጃኑወሪ ላይ ወላጆች ስለ ትምህርት ቤት ዝርዝር ዕቅድ ተጨማሪ መረጃ ያገኛሉ። የዳሰሳ ምላሾቹ ለማህበረሰብ እና በየክፍል ደረጃቸው ያተኮሩ ሞዴሎችን ለማዳበር ጥቅም ላይ ይውላሉ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎችን የመመለስ እቅድ ሥራውን ይቀጥላል፣ ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች ጤንነት አስተማማኝ መሆኑን በማረጋገጥ ስራችንን እንቀጥላለን። ኮቪድ-19 ወደፊት ላልታወቀ ያክል ጊዜ ከእኛ ጋር ስለሚቆይ የተማሪዎቻችንን ፍላጎት ለማሟላት እንዴት ማከናወን እንዳለብን በአንክሮ ማሰብ አለብን።
በእነዚህ ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ስንሰራ ለምታደርጉልን ድጋፍና ትብብር እናመሰግናለን።

Montgomery County Public Schools
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ