Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: Aug. 28, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

ለ 2020-2021 የትምህርት ዓመት እንኳን ደህና መጣችሁ!

ከ 166,000 በላይ ተማሪዎቻችንን ሰኞ፣ ኦገስት 31 እንኳን ደህና መጣችሁ! ለማለት እየጠበቅን ነን። የሥራ ባልደረቦቻችን በስፕሪንግ እና በሠመር ወቅት የትምህርት ዓመቱ የሚጀመርበትን በርካታ ሥራዎች በማከናወን እና ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ አሳልፈዋል። ይኼውም፣ እቅዶችን ማዘጋጀት ሁሉንም ተማሪዎች ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት ላይ እንደሚሳተፉ እና በከፍተኛ ጥራት ለማስተማር የቅድመ-ዝግጅት መሰናዶዎችን በማድረግ ነው።

ከጥቂት ወራት በፊት፣ ሁላችንም—ተማሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ አስተዳዳሪዎች እና ወላጆች—በአዲስ መንገድ ማስተማር እና መማር እንዲሁም የእርስበርስ ግንኙነት ሁኔታ ጋር በፍጥነት ለመስተካከል ያደረግናቸውን ጥረቶች ለመገመት ያዳግታል። በጋራ፣ ያጋጠመንን ከዚህ በፊት ያልነበረ ሁኔታና ክስተት ተጋፍጠን የተቻለውን ያክል መልካም ውጤት ለማግኘት ጥረናል።

ይህንን የትምህርት ዓመት ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ ስንጀምር፣ ለመስተካከል ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል እንገነዘባለን። እጅግ በጣም ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ለቆዮት አስተማሪዎች፣ አስተዳዳሪዎች እና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ስለትጋታቸው እባካችሁ ክብር ስጧቸው። በተጨማሪ፣ ለእናንተ የሚመች ሲስተም በመገንዘባችሁ ስለራሳችሁም ክብር መስጠት ያስፈልጋል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለሁሉም ተማሪዎች የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለመስጠት፣ እንደሚያመች ለማድረግ-flexibility፣ ውጤታማ ማስተማር እና የተማሪዎችን ትኩረት የሚስቡ እና የሚያሳትፉ ከካሪኩለም ተጨማሪ እንቅስቃሴዎችን-extracurricular activities ለመስጠት በሁሉም አቅጣጫ በመተለም እየሠራን እንገኛለን።

ስለተማሪዎቻችን መልካም አስተሳሰብ እና ጥሩ ልብ ያላቸው በርካታ የሥራ ባልደረቦች እና የማህበረሰብ አባላት ስላሉን በጣም እድለኞች ነን። አብረን ለመሥራት በቁርጠኝነት ከተነሣን ካሰብነው እጅግ የበለጠ ለማከናወን እንደምንችል እምነት አለን።
የትምህርት ዓመቱን ለመጀመር ለምታደርጉት ዝግጅት እንዲረዳችሁ ተጨማሪ ሪሶርሶችን እና መረጃዎችን በዚህ የሣምንቱ መጠናቀቂያ ላይ እንልክላችኋለን።

መልካም የትምህርት ዓመት ይሁንላችሁ!

Montgomery County Public Schools
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ