Is this email not displaying correctly? View it in your browser  Date: January 25, 2021


mcps logo

English | español |  中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛportuguês


በይነመረብ/ኦንላይን የቤት ሥራ ድጋፍ የመስጠት አገልግሎት ፌብሩወሪ 1/2021 ይጀመራል


የተወደዳችሁ ቤተሰቦች
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በሁለተኛ ሴሚስተር ከፌብሩወሪ 1 ጀምሮ ተማሪዎችን ለማስጠናት እና የቤት ሥራ ድጋፍ ለመስጠት አዲስ ነፃ የበይነመረብ-ኦንላይን አገልግሎት እንደሚጀመር በደስታ ይገልጻል። "Tutorme.com" ደህንነቱ የተጠበቀ የበይነመረብ መገልገያ ሲሆን በ "MCPS student Canvas እና StudentVUE" አካውንቶች አማካይነት እንደአስፈላጊነቱ ከ3ኛ እስከ 12ኛ ክፍሎች በማናቸውም ትምህርት ድጋፍ ለመስጠት በቀላሉ ተደራሽነት ያለው ነው።
Tutorme.com ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሥርዓተ ትምህርት ጋር የሚጣጣም፣ በአሁኑ ወቅት እየተሠራባቸው ያሉ አዳዲስ የከሪኩለም መሣሪያዎችን እውቀት ጭምር አገልግሎት ይሰጣል። አገልግሎቱ ከፍተኛ ጥራት ያለው፣ የተለያዩ አስጠኚዎች፣ በጥራታቸው ምሳሌነት ተመርጠው ስክሪን ላይ የሚቀርቡ (ከወንጀል ድርጊት ነጻ መሆናቸው ጭምር ተጣርቶ) ጥብቅ የሆነ ስታንዳርድ ያለው ነው።
አገልግሎቱ፦

  1. በሣምንት ሰባቱንም ቀናት በየቀኑ 24 ሠዓት ይኖራል
  2. ከ3ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች በነፃ የሚገለገሉበት ግብአት ነው

በአገልግሎቱ የተካተቱ ገጽታዎች፦

  1. ቨርቹወል ትምህርት መስጫ ነጭ ሠሌዳ 
  2. ጽሑፍ አርታኢ እና የጭውውት ቦታ
  3. የድምፅ/ቪድኦ ጭውውት (ምንም እንኳ ይህንን መለያ ባትጠቀም(ሚ)ም ወይም ካሜራ ባትከፍት(ቺ)ም)
  4. አስጠኚዎች ድጋፍ እንዲሰጡ የተሠሩ ምሳሌዎችን በስክሪንሾትስ ለማሳየት የሚረዳ ፈንክሽን
  5. 300 በላይ ትምህርቶች ከሒሳብ፣ ሳይንስ፣ ማህበራዊ ትምህርቶች እና ቋንቋዎች

አገልግሎት ሰጪው የ MCPS የኮንትራት ደምቦችና ህግጋቶችን በጠቅላላ የተከተለ ከመሆኑም በላይ የመረጃ ልውውጥ እና የግል መረጃ መጠበቅን ጭምር መልካምነት ያለው ተማሪዎችን ለመርዳት ባስፈለገ ጊዜ የቤት ሥራቸውን ለማሰራት የተመቻቸ ሁኔታን ለመስጠት ቁርጠኛ ነው። በተማሪው(ዋ) የ MCPS ኦንላይን አካውንቶች ላይ አገልግሎት ስለሚሰጥ ሌላ የተለየ አካውንት መክፈት አያስፈልግም።
በአገልግሎት ሰጪው ድረ-ገጽ ላይ የበለጠ መረጃ ይገኛል፦ www.tutorme.com
Montgomery County Public Schools


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ