classroom

Community Update

July 01, 2021

የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

ጁን 29 ስለተካሄደው የትምህርት ቦርድ ስብሰባ እና የ MCPS ማህበረሰብ በዚህ ሠመር እና ፎል ላይ ወደፊት የሚከናወኑ ጉዳዮችን በተመለከተ ማወቅ ያለባችሁ አምስት ጉዳዮችን እነሆ።

  1. የ 2021-2022 የትምህርት ዓመት ኦገስት 30 ይጀመራል፥ በዚህ ወቅት ትምህርት ቤቶች በሙሉ በአካል በመመለስ 100 ፐርሰንት ባላቸው አቅም በየሣምንቱ አምስት ቀን ትምህርት ይሰጣሉ። ስለ ፎል 2021 የትምህርት ቤቶች ራእይ ይበልጥ ለማወቅ ይህንን ቪድኦ ይመልከቱ

 

  1. ለ 2020-2021 የትምህርት ዓመት የተሰጠው የጭምብል (ማስክ) አጠቃቀም መመሪያ በሠመር ወቅት እንዳለ ይቀጥላል። በሠመር ፕሮግራሞች የሚሳተፉ ተማሪዎች እና ሠራተኞች በትምህርት ቤት ህንጻዎች ውስጥ በሚገኙበት ጊዜ ፊታቸውን የሚሸፍኑበት ጭምብል/ማስክ እንዲያደርጉ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፥ ከህንጻዎች ውጪ በሚሆኑበት ጊዜ ጭምብል/ማስክ የመጠቀም ግዴታ ባይኖርም ቢጠቀሙ በጣም ይበረታታል። ነገር ግን እንደየግለሰቡ(ቧ) ፍላጎት ይሆናል
    ኦገስት ላይ ስለ 2021-2022 የትምህርት ዓመት ጊዜያዊ የጭምብል/ማስክ አጠቃቀም መመሪያ ይሰጣል።
  1. ለቨርቹወል አካደሚ (Virtual Academy) ለማመልከት የጊዜ ገደቡ ጁላይ 2 ይጠናቀቃል። ፕሮግራሙ ለልጆቻቸው ጥሩ ጥቅም እንዳለው የሚሰማቸው ቤተሰቦች በሙሉ እንዲያመለክቱና ማናቸውንም አስፈላጊ ድጋፍ የሚሰጡ ሠነዶችን እንዲያቀርቡ እናበረታታለን። ሁሉም ማመልከቻዎች ተገምግመው ምላሾች በቅደም ተከተል ይሰጣሉ።

 

  1. የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከፎል ጀምሮ ለተማሪዎች አዲስ የማህበራዊ-ስሜት ትምህርት (SEL) ከሪኩለም ይሰጣል። ሠራተኞች ስለ አዲሱ የማህበራዊ-ስሜት ትምህርት (SEL) ከሪኩለም—"the Leader in Me" ስልጠና ጀምረዋል። ከሪኩለሙ ለእያንዳንዱ ተማሪ ስለ ትምህርት፥ ስለ መሪነት፥ እያንዳንዱ(ዷ) ተማሪ ብቁነት እንዲኖረው/እንዲኖራት የማድረግ ባህልን ስለመፍጠር፥ እና የትምህርት ሲስተሞች በአካደሚያ ስኬታማ እንዲሆኑ ለማስቻል የትምህርት ባለሙያዎችን ሁለንተናዊ በሆኑ ውጤታማ ተሞክሮዎች እና መገልገያዎች ያነቃቃል/ያበረታታል። ሥራ ላይ የሚውለው በሦስት ዓመት የጊዜ ፈረቃ ሲሆን በዚህ ፎል እነዚህ ትምህርት ቤቶች ይጀምራሉ።
  1. የ MCPS የኤለመንተሪ እና የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የሠመር ፕሮግራሞች በአካባቢ ት/ቤት በአካል፥ ስፔሻል ፕሮግራም፥ ወይም በ MCPS ቨርቹወል ፕሮግራም በሙሉ ጁላይ 6 ይጀመራል። በ MCPS የሠመር ፕሮግራሞች ከ 53,000 የሚበልጡ ተማሪዎች ይሳተፋሉ። በሚቀጥለው ሳምንት ስለሚጀመሩት ፕሮግራሞች፥ ምን እንደሚጠበቅ ዝርዝሩ በሣምንቱ መጨረሻ ለቤተሰቦች ኢሜይል ይደርሳቸዋል። በእርስዎ የአካባቢ ት/ቤት በአካል ስለሚሰጡ ፕሮግራሞች ማረጋገጫ እስካሁን ካልደረሰዎት፤ እባክዎ የልጅዎን ት/ቤት ያነጋግሩ። ለሁሉ ቨርቹወል ፕርግራም (all-virtual program) ጁላይ 2 ማብቂያ ድረስ የእንኳን ደህና መጡ መልክት ካልደረሰዎት፥ እባክዎ ለ፦ CentralSummerMS@mcpsmd.org (middle school) ወይም CentralSummerES@mcpsmd.org (elementary school) ኢሜይል ያድርጉ።

 



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools