classroom

የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

ስለ ጁን 10 የትምህርት ቦርድ ስብሰባና ለተማሪዎችና ለሠራተኞች 2021-2022 የትምህርት ዓመት ምን እንደሚመስል ማወቅ የሚያስፈልጋችሁ አምስት ነገሮች ከዚህ በታች ቀርበዋል፦

  1. በዚህ ፎል የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በሙሉ በሣምንት አምስት ቀን እንዲማሩ 100 ፐርሰንት ክፍት ይሆናሉ። ትምህርት ቤቶች የደወል ጊዜ፣ የአውቶቡስ ፕሮግራም፣ በቀን ስንት ክፍለጊዜ እና የክፍለ ጊዜ ርዝመት፣ የምሳ ሰዓትና የመናፈሻ ሠዓትን ጨምሮ የቅድመ ኮቪድ መደበኛ ፕሮግራሞችን ያከናውናሉ።
  2. የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የመማር መስተጓጎልን ለመቅረፍ እና ሁሉም ተማሪዎች በሚገኙበት የትምህርት ደረጃ ልክ ማከናወን የሚያስችላቸው ተደራሽነት እንዲኖራቸው የድጋፍ ዕቅዶችን አዘጋጅቷል። ዲስትሪክቱ ሁሉም ተማሪዎች ያመለጣቸውን የትምህርት ይዘቶች ማጠናቀቅ እንዲችሉ እና ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ የብዙ አመት እቅዶችን አዘጋጅቷል (ለምሳሌ፦ የሂሳብ ትምህርት ማገገሚያ)። መመሪያ፣ ድጋፍና የሙያ ትምህርት መምህራን ተማሪዎችን ባመለጣቸው ትምህርት ወይም በጠበቁት ትምህርት ላይ ያተኮረ ጠንካራ መሠረት እንዲገነቡ ያስችላቸዋል። መምህራን በሠመር እና በፎል ወራት፥ የትምህርት ዝግጅት በሚያቅዱበት ጊዜ በዋና ዋናዎቹ መደበኛ (ስታንዳርድ) መሥፈርቶችና የተማሪዎችን ፍላጎት በማሟላት ላይ ትኩረት የማድረግ ጥረት ያደርጋሉ።
  3. በዚህ ሠመር በትምህርት ቤት ህንፃዎች ውስጥ ጭምብል/ማስክ መጠቀም ያስፈልጋል። ፎል ላይ ተማሪዎች ሲመለሱ ከበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል፥ ከስቴት፥ እና ከካውንቲው በሠመር ወራት ጭንብል ስለመጠቀም ወቅታዊ መመሪያ እንደሚሰጠን እንጠብቃለን።
  4. ለቨርቹወል አካደሚ ለማመልከት ጁላይ 2 ቀነገደቡ ያበቃል። ፕሮግራሙ ለልጆቻቸው እንደሚጠቅም የሚሰማቸው ቤተሰቦች በሙሉ፣ እንዲያመለክቱና ሊደግፏቸው የሚችሉ ቁሳቁሶችን ቢሰጡ ጥሩ እንደሚሆንላቸው እናበረታታቸዋለን። ሁሉም ማመልከቻዎች ተገምግመው ምላሾች በቅደም ተከተል ይሰጣሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለቨርቹወል አካዳሚ እና የማመልከት ሒደት ጥያቄዎችን የመጠየቅ እና መልሶችን የማግኘት እድል ለመስጠት ለቤተሰቦች በርካታ የመረጃ ልውውጥ ክፍለጊዜዎችን ያካሄዳሉ። ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎችን (FAQs) ይመልከቱ
  5. የኮቪድ-19 ክትባት በመውሰድ የትምህርት ቤቶቻችንን እና የማህበረሰባችንን ደህንነት በመጠበቅ ያግዛሉ። ለእርስዎ እና ለልጅዎ (12 ዓመት እድሜ እና ከዚያ በላይ) የኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት በካውንቲው ማናቸውም የክትባት መስጫ ክሊኒክ ቀጠሮ ያዙ። በርካታ የ MCPS ትምህርት ቤቶች ውስጥ የኮቪድ-19 ክትባት ለመስጠት እንዲቻል የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤናና ሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ ጋር በትብብር መሥራቱን ይቀጥላል።


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools