የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦
የትምህርት ቦርድ ሜይ ሜይ 11 ስላካሄደው ስብሰባ፥ ስለ MCPS የማገገሚያ እቅድ እና ስለ ወደፊት ማወቅ ያለባችሁ አምስት አስፈላጊ ጉዳዮችን እነሆ፦
የሞንትጐመሪ ካውንቲ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱትን ህብረተሰብ በመቶኛ/ፐርሰንት ላይ ተሞርኩዞ እንደገና ከተከፈተ ወዲህ ወደ መጀመሪያው ምዕራፍ መገባደጃ ገብቷል። ኤፕሪል 27 የሞንቶጐመሪ ካውንቲ የጤና ጥበቃ ካውንስል ቦርድ የመጀመሪያውን ዙር የኮቪድ-19 ክትባት የወሰደ የሕዝብ ብዛት ቢያንስ አንድ በመቶ በሚደርስበት ጊዜ እንደገና የሚከፈትበትን ደንብ ምእራፍ ማካተቱ ይታወሳል።
ምዕራፍ 1፦ 50 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ከኮቪድ-19 ክትባት ቢያንስ አንድ ዶዝ በመቀበል በቤት ውስጥ የመሰብሰብ ገደቡን ወደ 50 ሰዎች ከፍ ማድረግና ከቤት ውጭ የመሰብሰብ ገደቡን ወደ 100 ሰዎች ከፍ ተደርጓል።
ምዕራፍ 2፦ 60 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ከኮቪድ-19 ክትባት ቢያንስ አንድ ዶዝ በመቀበል ቤት ውስጥ የመሰብሰቡ ገደብ ወደ 250 ሰዎች ከፍ እንዲል የሚያደርግ ሲሆን ከቤት ውጭ የሚደረጉ ስብሰባዎች ገደብ የላቸውም።
የሠመር ፕሮግራሞች ምዝገባ ጁን 4 ይዘጋል። በወረርሽኙ ምክንያት የባከኑ የትምህርት ጊዜያትን ለማካካስ ዲስትሪክቱ የሚያደርጋቸው ጥረቶች አካል በመሆናቸው የሠመር ፕሮግራሞች አስፈላጊና ጠቃሚ ናቸው የደስታ ጊዜ ለማሳለፍእናበፕሮግራሞች ላይ ለመሳተፍ ለአንደኛና ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሚቀርቡት ፕሮግራሞች በሒሳብ፣ በሊተርሲ፣ በስፔሻልስ፣ በአእምሮ ማዳበር እና ተማሪዎችን ለሚቀጥለው የትምህርት ደረጃ በመዘጋጀት ላይ ያተኮሩ ናቸው። በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለመመረቂያ አስፈላጊ በሆኑ በሁሉም ትምህርቶች ዙርያ ዳጋሚ ለሚወሰዱ ወይም ኦርጅናል ክሬዲት ክሬዲቶችን የማግኘት እድሎች ያሉ ሲሆን ክሬዲት የማይኖራቸው አማራጮችንም በአካባቢ ትምህርት ቤቶች መውሰድ ይችላሉ። ፕሮግራሞቹ፦
እንደፕሮግራሙ ሁኔታ በአካባቢዎ ት/ቤት ParentVUE በመጠቀም ምዝገባ ይካሄዳል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራሞች ሰኞ ጁን 28 ይጀመራል፥ እና የአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራሞች ማክሰኞ፣ ጁላይ 6 ይጀመራል። ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል። የእርስዎን ParentVUE አካውንይ እንዲሠራ ለማድረግ ድጋፍ ከፈለጉ፥ Community Support Hotline በስልክ ቁጥር 240-740-7020 ወይም በኢሜይል communitytechsupport@mcpsmd.org ይጠይቁ።
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org