elementary school student on computer at home

የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

ስለ ማገገሚያ ጥረታችን፣ ስለ ፎል እቅዶችን እና ለተማሪዎችና ለሠራተኞች ተገልሎ ስለመቆየት የመሣሠሉ መመሪያዎችን በሚመለከት ጠቃሚ መረጃዎችን ልንሰጥዎት እንፈልጋለን። ወደ ሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ስናመራ፥ ስለ 2020-2021 የትምህርት ዓመት የመጨረሻ ሣምንታት ማወቅ የሚገባዎት ስድስት ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፦

  1. ረቡዕ ለሁሉም ተማሪዎች ቨርቹወል የምናስተምርበት ቀን ይሆናል። በአሁን ጊዜ ለሁሉም ተማሪዎች የቨርቹወል ትምህርት የተመደቡ ረቡዕ ቀናትን በአካል የሚማሩበት ቀን ለማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ ካለ የትምህርት ቦርድ MCPS ን ጠይቋል። ሱፐርኢንተንደንቱ(ቷ) ጥያቄውን በጥንቃቄ ከገመገመ(ች) በኋላ፣ ለውጥ ማድረጉ ከዚህ ቀጥሎ ባሉት ተግባሮች ላይ በሚኖረው ጉልህ ተፅዕኖ ምክንያት ረቡዕ ቨርቹወል ትምህርት የሚሰጥበት ቀን ሆኖ እንደሚጥል ተወስኗል፦

    • አካዳሚያዊ ጣልቃ ገብነቶች እና ለተማሪዎች የሚደረጉ ድጋፎች
    • የልዩ የትምህርት ስብሰባዎችና ድጋፎች
    • በወቅታዊ የግል እና መደበኛ ምዘናዎች
    • ለሰራተኞች የእቅድ ዝግጅት ጊዜ

    በተጨማሪም፥ MCPS ለተቀረው የትምህርት ዓመት በ A/B ፈረቃ የሚቀጥል ቢሆንም አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ግን እንደተማሪዎቻቸው የተለየ ፍላጎት ሁኔታ አገልግሎት ለመስጠት የሚያመቻቸውን ማስተካከያ ማድረግ ይችላሉ። ርእሰ መምህራን እነዚህን ማስተካከያዎች ለማድረግ ማመቻቸት የሚችሉ ሲሆን፥ ይህም A/B ፈረቃ ለሚማሩ ተማሪዎች በየሳምንቱ ለየብቻ ቀጠሮ በመስጠት ማስጠናትና የመሣሠሉ ድጋፎችን መስጠት ይጨምራል።

  2. MCPS ለተማሪዎችና ለሠራተኞች የሚሰጠውን የኳረንቲን መመሪያ እያሻሻለ ነው። የበሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል (CDC)፥ ከስቴት እና ከአካባቢው ባለስልጣናት በተላለፈ መመሪያ መሠረት MCPS እና በሽታ እንዳይዛመት ራስን ማግለል ጋር የተያያዙ መመሪያዎቹን አሻሽሏል፣ ይኬውም ወዲያውኑ ተግባራዊ ሆኗል። MCPS ቀደም ሲል በኮቪድ-19 ምርመራ ፖዚቲቭ የሆኑ ሰዎች ለ 14 ቀናት ራሳቸውን አግልለው እንቆዩ ይጠበቅባቸው ነበር። አሁን ግን ራስን ማግለል የሚያስፈልገው ጊዜ 10 ቀን ሆኗል። በተጨማሪም አስፈላጊ የሚሆነው የኳራንቲን ጊዜ አሁን ወደ 10 ቀናት ዝቅ ብሏል (በአንዳንድ ሁኔታዎች)። የበለጠ መረጃ እዚህ ይገኛል፦ https://www.montgomeryschoolsmd.org/reopening/#Isolation
  3. MCPS ፎል ላይ፥ በሣምንት አምስት-ቀን ለተማሪዎች በአካል ትምህርት ይሰጣል። ኤፕሪል 27፣ በ 2021-2022 የትምህርት ዓመት ት/ቤቶች 180 የትምህርት ቀናት ለማሟላት በአካል ትምህርት ለመስጠት መክፈት እንዳለባቸው የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ቦርድ ውሳኔ ሰጥቷል በቅርብ ጊዜ በገለጽንላችሁ መሠረት፥ ፎል ላይ በተሣካ ሁኔታ መክፈት እንዲቻል ለመዘጋጀት ሠራተኞች ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ናቸው። በመጪዎቹ ሣምንታት፥ MCPS ፎል ላይ ስለሚከፈትበት ዝርዝር እቅድ በማጠናቀቅ ለትምህርት ቦርድ እና ለ MCPS ማህበረሰብ ያቀርባል። ይህ እቅድ ከቅድመ መዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች ስለ MCPS Virtual Academy፥ የሙሉ ጊዜ ቨርቹወል ትምህርት ፕሮግራም በርካታ መረጃዎችን ያካትታል። ቨርቹወል ትምህርት ለበርካታ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች በደንብ ጠቅሟቸዋል ቨርቹወል አካዳሚ በማእከል የሚካሄድ ፕሮግራም በመሆኑ ከተማሪዎች የአካባቢ ት/ቤቶች ጋር በመቀናጀት ለተማሪዎች በቨርቹወል ትምህርት ማግኘት የሚፈልጉትን አካዳሚያዊ እና ማህበራዊ-ስነልቦናዊ ድጋፍ ይሰጣል። ከሜይ 1 በፊት የፍላጎት ዳሰሳ መጠይቅ መሙላትዎን እርግጠኛ ይሁኑ፥ እርስዎ የሚሰጡት መልስ MCPS ስለ ቨርቹወል ትምህርት ለማቀድ ይረዳል። ይህ ቃል መግባት ማለት አይደለም ቨርቹወል አካዳሚ ለመሣተፍ እናም ለማስገባትም ዋስትና መስጠት አይደለም፥ የቤተሰብን ፍላጎት ለማወቅ ብቻ የታሰበ ነው። ለቨርቹወል አካዳሚ እንዴት ማመልከት እንደሚቻል የበለጠ መረጃ በቅርቡ ይገለጻል። ለምዝገባ ዝርዝር መስፈርት ይወጣል።
  4. በሞንትጎመሪ ካውንቲ የፊት መሸፈኛ ጭምብል መጠቀም አስፈላጊነቱ እንደቀጠለ ነው። ገቨርነር ላሪ ሆገን (Governor Larry Hogan) ኤፕሪል 28 ባስተላለፉት መልእክት መሠረት ከቤት ውጭ ከሆነ የፊት መሸፈኛ እና ጭምብሎችን መጠቀም አስፈላጊ ባይሆንም የካውንቲ አመራር ዋና ኃላፊ ማርክ ኤልሪክ/County Executive Marc Elrich ባስተላለፉት መልእክት መሠረት፥ ከስቴት ተሻሽሎ የተላለፈውን ግዴታ ካውንቲው አሁኑኑ በፍጥነት ተግባራዊ አያደርግም። በዚህ ጊዜ፥ በ MCPS ንብረት ውስጥ፥ እና ህንጻዎች ውስጥ፥ እንዲሁም በ MCPS ይዞታ ከቤት ውጭ ቢሆንም የፊት መሸፈኛ ጭምብል መጠቀም አስፈላጊ ነው። ስለ ፊት መሸፈኛ ጭምብል አጠቃቀም የካውንቲው መመሪያ እዚህ ይገኛል፦ https://montgomerycountymd.gov/covid19/face-coverings.html
  5. የሠመር ፕሮግራሞች ምዝገባ ሜይ 3 ይጀመራል። በወረርሽኙ ምክንያት የባከኑ የትምህርት ጊዜያትን ለማካካስ ዲስትሪክቱ የሚያደርጋቸው ጥረቶች አካል በመሆናቸው የደስታ ጊዜ ለማሳለፍ እና በፕሮግራሞች እንቅስቃሴዎች ላይ ለመሳተፍ የሠመር ፕሮግራሞች አስፈላጊና ጠቃሚ ናቸው። የኤለመንተሪ እና ሚድል ስኩል ፕሮግራሞች የሚያተኩሩት በሒሳብ እና ሊተርሲ፥ als and enrichment፥ እና ተማሪዎችን ለሚቀጥለው የክፍል ደረጃ በማዘጋጀት ላይ ይሆናል። በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለመመረቂያ አስፈላጊ በሆኑ በሁሉም ትምህርቶች ዙርያ ድጋሚ ለሚወሰዱ ወይም ኦርጅናል ክሬዲት ክሬዲቶችን የማግኘት እድሎች ያሉ ሲሆን ክሬዲት የማይኖራቸው አማራጮችንም በአካባቢ ትምህርት ቤቶች መውሰድ ይችላሉ። ፕሮግራሞቹ፦

    • ያለምንም ወጪ ለሁሉም ተማሪዎች የሚሰጡ ሲሆን መጓጓዣም ይኖራል።
    • በሁሉም የአካባቢ ትምህርት ቤቶች/ክለስተሮች ይሰጣል
    • በጠቅላላ-ቨርቹወል እና/ወይም በአካል የመማር አማራጮች ይኖራሉ

    እንደፕሮግራሙ ሁኔታ በአካባቢዎ ት/ቤት ParentVUE በመጠቀም ምዝገባ ይካሄዳል። የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ፕሮግራሞች ሰኞ፥ ጁን 28 የሚጀመሩ ሲሆን የኤለመንተሪ እና ሚድል ስኩል ፕሮግራሞች ማክሰኞ፥ ጁላይ 6 ይጀመራል። የበለጠ መረጃ እዚህ ይገኛል። የእርስዎን ParentVUE አካውንይ እንዲሠራ ለማድረግ ድጋፍ ከፈለጉ፥ Community Support Hotline በስልክ ቁጥር 240-740-7020 ወይም በኢሜይል communitytechsupport@mcpsmd.org ይጠይቁ።

  6. MCPS ከቤት ውጭ በሆኑ ቦታዎች የምረቃ ሥነ ሥርዓቶችን ማካሄድ እንዲቻል ካውንቲው አጽድቋል። ተመራቂ ተማሪዎች ሁለት እንግዶቻቸው በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዲገኙላቸው ይፈቀድላቸዋል። በተጨማሪም፥ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ስንየሮች ህብረት የሚያደርጉባቸውን ቀኖች ዝግጅቶችን ለማከናወን የተፈቀደላቸው ሲሆን መደረግ ያለባቸው ከቤት ውጭ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶቻችን ስቴዲየሞች እና በግቢ ውስጥ ነው። ሁነቶቹ ተማሪዎች አካላዊ ርቀታቸውን ጠብቀው በፈጠራ ሥራ ከእኩዮቻቸው ጋር እንዲሣተፉ ያበረታታሉ።


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools