girls on laptop at home

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የቨርቹወል ትምህርት አካዳሚ የዝንባሌ/ፍላጎት ዳሰሳ ላይ ይሳተፉ

የተከበራችሁ ወላጆችና አሳዳጊዎች፦

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በ 2021-2022 የትምህርት ዓመት ከቅድመ መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል (PreK-12) ለሚገኙ ተማሪዎች በአካል ከሚማሩት መደበኛው ማስተማር በተጨማሪ በሣምንት አምስት ቀን ቨርቹወል አካዳሚ የመማር አማራጭ ለመስጠት እያቀደ ነው። ቨርቹወል አካዳሚ ተብሎ ለሚታወቀው የቨርቹወል ትምህርት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለሚያዘጋጀው እቅድ ፍላጎትን ለማወቅ የሚደረግ የዳሰሳ ጥናት የእርስዎ መልስ ይረዳል። ይህ ማለትትምህርቱን ለመከታተል መወሰን አይደለም ቨርቹወል አካዳሚም ለመቀበል ቃል አይገባም፤ ነገር ግን የቤተሰብን ፍላጎት ለመመዘን ብቻ ነው። ለቨርቹወል አካዳሚው እንዴት ማመልከት እንደሚቻል በቅርቡ የበለጠ መረጃ ለማህበረሰቡ ይገለጻል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ቨርቹወል ትምህርት ለብዙ ተማሪዎች አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ሌሎች ግን አዳብረውበታል። እንደ ሁኔታው በማመቻቸት (flexibility) ከቤት በኢንተርኔት የመስራት እድል መኖሩ ብዙ የቤተሰብ ፍላጎቶችንና የአንዳንድ ተማሪዎችን ማኅበራዊ ስሜት የመደገፍ እድል ፈጥሯል። በእነዚህ ምክንያቶች እና በሌሎችም፥ MCPS ኦንላይን የመማር-ማስተማር አማራጮችን ለማሻሻል አቅዷል።

አስፈላጊ ዝርዝሮች፦

  1. ቨርቹወል አካዳሚ የሚማሩ ተማሪዎች በአካባቢያቸው ትምህርት ቤት (ሆም ስኩል) ይገባሉ/ይቀጥላሉ። (በምርጫ ከሚወሰዱ ኮርሶች በስተቀር) በአካባቢያቸው ትምህርት ቤት (ሆም ስኩል) የምግብ አገልግሎት፥ የልዩ ትምህርት (ስፔሻል ኢጁኬሽን) አገልግሎት፥ እና የምክር አገልግሎትን ጨምሮ ሁሉንም አገልግሎቶች ያገኛሉ።
  2. ተማሪዎች በአካባቢያቸው ትምህርት ቤት (ሆም ስኩል) ከትምህርት ሰዓት ውጪ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች (ክለቦች፣ ከትምህርት ቤት በኋላ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች፣ በመካከለኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የሚካሄዱ ስፖርቶች) ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
  3. ሙሉ ጊዜ/ሙሉ ዓመት ቨርቹወል ፕሮግራም ላይ የሚማሩ ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ ውስጥ ባሉ መምህራን ሳይሆን ከቨርቹወል አካዳሚ በሚመደቡ መምህራን ይማራሉ።
  4. ቨርቹወል አካዳሚው ከቅድመ መዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ (Pre-K-12) ለሚማሩ ተማሪዎች ለሙሉ ጊዜ ብቻ የአመት ትምህርት አማራጭ ሆኖ እየተነደፈ ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የከፊል-ጊዜ አማራጭ ይሰጥ ይሆናል።

ስለ ቨርቹወል አካዳሚ የበለጠ መረጃ እዚህ ይገኛል፦
https://www.montgomeryschoolsmd.org/virtualacademy/

ለትምህርት ቦርድ የቀረበውን የቨርቹወል አካዳሚ ዝግጅት እዚህ ይመልከቱ፦ https://youtu.be/-qQ48OOw-KI?t=4892

እባክዎ በ MCPS ለተመዘገበ(ች) ለእያንዳንዱ ልጅ የዝንባሌ/የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ቅጽ ይሙሉ። ይህ የዳሰሳ ጥናት ሜይ 1/2021 ይዘጋል።

የዳሰሳ አገናኝ/ሊንክ/Survey link: https://forms.gle/ZqZnLCrHMswiAiyW8



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools