girl on computer

የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞች

ዳግመኛ ስለመክፈት እና ተማሪዎች እና ሠራተኞች በአካል ለመማር-ማስተማር በሚመለሱበት ጊዜ ተሞክሮዎቹ ምን እንደሚመስሉ ማርች 11 በተካሄደው የትምህርት ቦርድ ስብሰባ የ MCPS ሠራተኞች ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን እና መልስ ስለተሰጠባቸው ጥያቄዎች አጋርተውናል። ስለ MCPS የማገገሚያ እቅድ ውይይት ማወቅ ያለብዎት አስፈላጊ ነገሮች እነሆ፦

 1. ስለ ተማሪዎች ቡድን የመመለሻ ጊዜ ሁኔታዎችን MCPS ለማፋጠን እንዲችል ቦርዱ አማራቾችን ለመተግበር እያሰበ ነው። የማርች 15 የተማሪዎች መመለስ ሁኔታ ስኬታማ ስለነበር፥ 2.1 እና 2.2 ሁለቱም ቡድኖች ኤፕሪል 19 በአንድ ላይ በፈረቃ እንዲመለሱ ከ MCPS ሃሳብ ቀርቧል። ቦርዱ በዚህ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ ማርች 23 በሚደረገው ስብሰባ ይወስናል።

  ፈረቃII (Phase II)
  ቡድን 2.1 (ኤፕሪል 19)
  ቡድን 2.2 (ኤፕሪል 26)
  • 8ኛ ክፍል
  • 9ኛ ክፍል
  • 11ኛ ክፍል
  • 7ኛ ክፍል
  • 10ኛ ክፍል
 2. ከሜሪላንድ እና ከአጎራባች ስቴቶች ውጭ ቤተሰቦችን እና ሠራተኞች በዚህ ወቅት እንዳይጓዙ MCPS በአጽንኦት ያሳስባል። ተማሪዎች ወይም ሠራተኞች ከተጓዙ፣ ከጉዞአቸው ከተመለሱ በኋላ በ 72 ሠዓታት ውስጥ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲያደርጉ እና ውጤት እስከሚያገኙ ድረስ ራሳቸውን አግልለው እንዲቆዩ (ኳራንቲን እንዲያደርጉ) በአጽንኦት እናሳስባለን። ብዙ ሠራተኞች እና ቤተሰቦች በስፕሪንግ እረፍት ጊዜ ከስቴት ውጭ የመጓዝ እቅድ እንዳላቸው እንገነዘባለን። ነገር ግን፦ ሰዎች ከስፕሪንግ እረፍት ከተመለሱ በኋላ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ኮቪድ-19 በከፍተኛ ሁኔታ እንዳይሠራጭ ለመቀነስ እንዲረዳ ማክሰኞ፥ ኤፕሪል 6 ለሁሉም ተማሪዎች ቨርቹወል ሚማሩበት ቀን ይሆናል። ሮብ፣ ኤፕሪል 7 በመርሃግብሩ መሠረት ቨርቹወል ትምህርት የሚሰጥበት ቀን ይሆናል። ኤፕሪል 6 እንደሚመለሱ የጊዜ ሠሌዳ የተያዘላቸው ተማሪዎች (ቡድን 1.2/Group 1.2) ወደ ህንፃዎች የሚመለሱት ሐሙስ፣ ኤፕሪል 8 ይሆናል።  

 3. በትምህርት ቤቶቻችን የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል ሁላችንም የራሳችንን ድርሻ ማከናወን አለብን። ይኼውም፦ ተማሪ ወይም ሠራተኛ ምልክት ሳይታይበ(ባ)ት በሽታው እንዳለበ(ባ)ት/እንደሌለበ(ባ)ት ለመለየት እንዲቻል ትምህርት ቤት በሚሰጠው የኮቪድ-19 ምርመራ መሣተፍን ይጨምራል። ለሁሉም ተማሪዎች እና ለሠራተኞች በሙሉ በየሣስምንቱ ምርመራ ይሰጣል። ለአንድ የመማሪያ ክፍል ወይም ቡድን መጎርጎሪያ አይነት ይቀመጥና ከዚያ ወደ ማእከላዊ የምርመራ ላቦራቶሪ ይላካል። በተወሰደው ናሙና ላይ ኮቪድ-19 ቫይረስ መኖር አለመኖሩን በምርመራው ይረጋገጣል። ትምህርት ቤቶች ከ 2-3 ቀኖች ውስጥ ውጤቶቹን ማግኘት ይችላሉ። ማርች 15 በሚውልበት ሣምንት ውስጥ ለሁሉም የ MCPS ቤተሰቦች የስምምነት ማረጋገጫ ቅጽ ይላካል። ቅጹን ሞልተው ካልመለሱ፣ የእርስዎ ልጅ ምርመራ አይደረግለ(ላ)ትም።

  swab

 4. የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ቦርድ (MSDE) የሚከተሉትን የስፕሪንግ 2021 ምዘናዎች ሠርዟል፦

  • የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስነጥበባት/English Language Arts (ELA) (Grades 3-8, 10)
  • ሒሳብ/Mathematics (Grades 3-8 and Algebra 1)
  • ELA እና Reading አማራጭ ፈተናዎች/Alternate Assessments in ELA and Reading (Grades 3-8, 11)
  • የሜሪላንድ ኢንተግሬትድ ሳይንስ አሰስመንቶች/Maryland Integrated Science Assessments (MISA) in Grades 5, 8 and high school
  • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስለ ስነመንግስት ምዘና/Government Assessment

  ፎል 2021 ላይ ለሚማሩ ተማሪዎች የ "ELA and Math" ምዘናዎች የሚሰጡት በአነስተኛ መጠን/ስኬል ነው። የትምህርት ቤት ሠራተኞች የተማሪን የእውቀት ደረጃ ለመመዘን ከበፊት የመመዘኛ መረጃ/ዳታ ይጠቀማሉ። በአካል ትምህርታቸውን መከታተል ለሚቀጥሉ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች "ACCESS for ELLs assessment" ተደራሽነቱ ይቀጥላል። እነዚህ የስፕሪንግ ወቅት መመዘኛዎች መሠረዛቸው የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መመረቂያ አስፈላጊ መስፈርቶች ላይ እንዴት ተጽእኖ እንደሚያደርግ ከ MSDE በቅርቡ ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል።

 5. ፎል የተለየ የትምህርት ዓመት እንደሚሆን MCPS እያቀደ ነው። ልጆቻቸው እቤት ሆነው ቨርቹወል እንዲማሩ የመረጡ ወላጆች ምርጫቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፥ በአካል ለመማር ለሚመለሱ ተማሪዎች በሣምንት አምስት ቀን ሙሉ በሙሉ በአካል ትምህርት ለመስጠት ሠራተኞች እየተዘጋጁ ናቸው። ነገር ግን፦ በዚህ ጊዜ ያለው የጤና አጠባበቅ መመሪያ ተማሪዎች አንዱ ከሌላው ስድስት ጫማ አካላዊ ርቀት እንዲጠብቁ ስለሚያዝ፥ ሁሉንም ተማሪዎች (ለመመለስ የሚፈልጉትን) ወደ ትምህርት ቤት ህንጻዎች በአንድ ጊዜ በአንድ ላይ ለመቀበል MCPS አዳጋች የሚሆንበት በርካታ የአሠራር እና ሎጅስቲካዊ ሁኔታዎች አሉ። ፎል ላይ በተሳካ ሁኔታ ዳግመኛ ለመክፈት የሚያስችሉ ወሳኝ ሥራዎችን ስንሠራ ስለቆየን በየጊዜው መረጃዎችን ለማህበረሰቡ እናጋራለን።


ወደፊት ምን ይጠብቀናል?

ከመዋእለ ህፃናት እስከ 3ኛ ክፍል 20,000 የሚያህሉ ተማሪዎችን ሰኞ፣ ማርች 15 ሲመለሱ ለመቀበል ዝግጁ ነን። በርካታ ተማሪዎች ወደ ት/ቤቶች ህንጻዎች የመመለስ ጉጉት አ፤አቸው። ነገር ግን፦ ልክ አዲስ የትምህርት ዓመት መጀመሪያ ላይ እንደሚሆነው ሁሉ አንዳንድ ተማሪዎች መደናገጥ/ጭንቀት ሊሰማቸው ይችላል። ተማሪዎች ምንም አይነት የጭንቀት ስሜት ሲሰማቸው ለመርዳት ጥቂት ጠቃሚ ሃሳቦችን እነሆ፦

tips

በተጨማሪ፤ አሽከርካሪዎች በርካታ ተማሪዎች በሠላም ወደ ህንጻዎች እንዲመለሱ ለመርዳት ጠቃሚ ማሳሰቢያ፦ ለእግረኞች ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፥ የቆመ የትምህርት ቤት አውቶቡስ ማለፍ አይገባም። በአካል መማር የተለየ እንደሚመስል እና አስተማሪዎቻችን፣ አስተዳዳሪዎች እና ድጋፍ የሚሰጡ ሠራተኞች ተማሪዎች የተቻለውን ያክል ምርጥ ትምህርት እንዲያገኙ እና በትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ ለመርዳት አቅማቸው የሚችለውን ሁሉ እያደረጉ ናቸው። በቀጣይነት ስለሚያደርጉልን ድጋፍ እናመሰግናለን።


ተጨማሪ ሪሶርሶችEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools