Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: Aug. 16, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞች

አሁን የምጽፍላችሁ ስለ 2020 - 2021 የትምህርት ዓመት ወቅታዊ መግለጫ ለመስጠት ሲሆን ይኼውም ትምህርት የሚጀመረው ሰኞ፣ ኦገስት 31/2020 ነው። ኦገስት 6 የትምህርት ቦርድ ረቂቅ እቅዱን ከተመለከተ በኋላ በዲስትሪክቱ ውስጥ የመጀመሪያው ሴሚስተር ቨርቹወል ብቻ ትምህርት እንዲሰጥ ወስኗል

ከኦገስት 6 ወዲህ፣ በሺዎች ከሚቆጠሩ ተማሪዎች፣ ወላጆች እና የማህበረሰብ አባላት ግብረመልስ አግኝተናል። እነዚህን ግብረመልሶች አንዳንድ ማሻሻያዎችን ለማድረግ እና እቅዳችንን በማዳበር ለማህበረሰባችን ፍላጎቶች የተሻለ ምላሽ ለመስጠት ተጠቅመንባቸዋል። እነዚህም ማሻሻያዎች የሚያካትቱት፦

  1.  በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መርሃግብር ላይ፣ በእሮብ ቀኖች 20-ደቂቃ ቨርቹወል የክፍል ጊዜ የሚጀመርበት የመግቢያ ጊዜ እንዲሆን። ይህም በግላዊ ሁኔታ የሚረዳ-የምትረዳ ተማሪን ይበልጥ ለመርዳት ይጠቅማል።
  2. ለመጀመሪያ ደረጃ ክፍሎች ተማሪዎቻችን ሪኮርድ በተደረጉ ትምህርቶች እና ሌሎችም አመቺ አሠራር በመፍጠር ይበልጥ ትኩረት መስጠት።
  3. ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ምግብ ቦታ ለመድረስ በቂ ጊዜ እንዲኖራቸው የምሣ ሠዓትን ከ60 ደቂቃ ወደ 75 ደቂቃ ማራዘም። የኤለመተሪ የምሣ ሠዓትንም ከ75 ደቂቃ ወደ 90 ደቂቃ ማራዘም።
  4. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አስተማሪዎች ለቨርቹወል ማስተማር እቅድ ለመሥራት ተጨማሪ የዝግጅት ጊዜ። በእሮብ ቀኖች ከሰዓት በኋላ ለኤለመንተሪ እና ለሁለተኛ ደረጃ አስተማሪዎች እቅድ ለማዘጋጀት እና የትብብር ጊዜ ቅድሚያ በመስጠት በተለያየ ሠዓት የመጀመር አሠራር ይሠጣል።
  5. ከሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ክፍለጊዜዎች ጋር እንዳይጋጭ ለማድረግ የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ኮርሶችን መውሰጃ ጊዜ ከ9 a.m. በፊት እና ከ 2:30 p.m. በኋላ እንደሚጀመር ይቀየራል።
  6. ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከሙሉ/ጎደሎ የጊዜ ሠሌዳ ወደ ቁጥር ቅደምተከተል ሲለወጥ ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሙሉ/የጎደሎ ቁጥሮች የነበረው አማራጭ ወደ ቅደምተከተል መቀየር።

የኦገስት 25 የትምህርት ቦርድ ስብሰባ እየተቃረበ ሲሄድ እቅዳችንን እያዳበርን ለማህበረሰባችን ማጋራታችንን እንቀጥላለን። ቦርዱ በስብሰባው ወቅት እቅዱን ከገመገመ በኋላ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጥበታል።

የመጪውን ዓመት እቅድ ለማጠቃለል በምንሠራበት ወቅት የእናንተንም ስጋትና፣ ውጥረት የምንገነዘብ መሆናችንን እባክዎ ይረዱልን። ከትውልዶች ዘመናት በኋላ የህዝባዊ ትምህርትን ካጋጠሙት አዳጋች ሁኔታዎች መካከል ከባድና አስቸጋሪ የሆነውን ሁኔታ መፍትሔ ለመሻት ጥረት ስናደርግ ትዕግሥት እና ግንዛቤ እንዲኖርዎት መጠየቄ ይታወሳል።

በአገሪቱ ውስጥ እንደሚገኙት እንደሌሎቹ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች ሁሉ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እያንዳንዱን ሥራ የሚተልመው ለሁሉም ተማሪዎች መፃዒ ጊዜአቸው የለመለመና የበለፀገ እንዲሆን የሚያዘጋጃቸውን ትምህርት ለመስጠት ነው። ይህ እቅድ ፍጹም ይሆናል ተብሎ ባይጠበቅም፣ ለተማሪዎቻችን በሚያመቻቸው አኳኋን ከፍተኛ ጥራት ያለው የማስተማር ተሞክሮ እንደምንሰጣቸው ልናረጋግጥላችሁ እንችላለን።

ከምናዉቀዉ፦

ትምህርት የሚጀመርበት የመጀመሪያው ቀን ሰኞ፣ ኦገስት 31 ይሆናል። ቦርዱ ስለ ትምህርት ቤት መርሃግብሮች ኦገስት 25 የመጨረሻ እርምጃ ይወስዳል።
አስተማሪዎች እና የሥራ ባልደረቦች ኦገስት 24-28 በቅድመ-አገልግሎት ሣምንት ይሣተፋሉ። አዲሱ ዓመት ከመጀመሩ በፊት ቅድመ-አገልግሎት በጣም አስፈላጊ ጊዜ ስለሆነ፣ በተናጠል እና በጋራ እቅድ ለማዘጋጀት፣ የትምህርት ቤት አመራር የቡድን ተግባሮችን ለማከናወን፣ ቡድን ለመመሥረት እና የሲስተም-ደረጃ ስልጠና የመውሰድ ጊዜን ያካትታል።
ስለ ማህበራዊ ስሜት ማዳበር ትምህርቶች እና ድጋፎች በየሣምንቱ ለተማሪዎች ይሰጣሉ።
አዲስ "parent portal፣ Synergy ParentVue" በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል። ይህም ለሁሉም ትምህርት ቤቶች ስለ ክፍል ደረጃዎች፣ የትምህርት ክትትል፣ የጊዜ ሠሌዳ እና ሌሎች በርካታ መረጃዎችን ለመለዋወጥ በዋናነት ያገለግላል። ወላጆች እነዚህን ዲቫይሶች ከፍተው ለመጠቀም የሚያስችላቸውን መረጃ የያዘ ደብዳቤ በቅርቡ በፖስታ ይደርሳቸዋል። ስለ ትምህርት ቤት እና ስለማህበረሰብ ጠቃሚ መረጃዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመለዋወጥ እንድንችል እባክዎ መሣሪያዎቹን ለመጠቀም ይመዝገቡ-ይክፈቱ። አስፈላጊ ከሆነ፣ የእርስዎን ወቅታዊ መረጃ በ portal መስጠት ይችላሉ።
ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ኦገስት 26 የማጠቃለያው መርኃግብር ይደርሳቸዋል።
በሚቀጥሉት ሁለት ሣምንቶች (ኦገስት 17-28) ትምህርት ቤቶች በጠቅላላ ቴክኖሎጂ እና የትምህርት ቁሳቁሳሶችን ያከፋፍላሉ። ከእርስዎ ልጅ ትምህርት ቤት ገና ያልሰሙ ከሆነ፣ ስለ ሚከፋፈልበት ቀን እና እንዴት እንደሚረከቡ የሚገልጽ መልእክት በፍጥነት ይደርስዎታል። ለ MCPS ተማሪዎች በሙሉ Chromebook ዲቫይስ አለን። የኤለመንተሪ ተማሪዎች ስክሪን በእጃቸው እየነካኩ የሚሠሩበት-touchscreen የተሻሻሉ ዲቫይሶችን ያገኛሉ።
በመጀመሪያው ሴሚስተር ተማሪዎች ቨርቹወል ከ ከሪኩለም ተጨማሪ ተግባሮች-አክቲቪቲዎች እና አትሌቲክስ ላይ በመሥራት የመሣተፍ እድሎች ይኖራቸዋል።
MCPS ለወላጆች ስለ ማህበራዊ ስሜት ማጎልበት፣ ጤነኛ ቁመና፣ ስለ ርቀት ትምህርት ስልቶች እና ድጋፎች፣ የወላጅና ልጅ መልካም ግንኙነቶችን ስለመጠበቅ፣ እና ስለ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጨምሮ ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን፣ አውደጥናቶችን-ዎርክሾፖችን እና በቅድሚያ ሪኮርድ የተደረጉ ቪድኦዎችን ይሰጣል። በተጨማሪ የእርስዎ ልጅ (ልጆች) በ ቨርቹወል ትምህርት ስኬታማ እንዲሆኑ ለማዘጋጀት እንዲረዳዎት የክንዋኔ ዝርዝር-ቼክ ሊስት አዘጋጅተናል

አሁን በሒደት ላይ የሚገኙ ክንውኖች፦

ስፔሻል ኢጁኬሽን እና የእንግሊዝኛ ትምህርት ለሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች (ESOL) አገልግሎት የሚያገኙ ተማሪዎችን በትንንሽ ቡድኖች ለማምጣት የምንችልበትን ሒደት በሚመለከት ከካውንቲ የጤና ሃላፊዎች ጋር እየሠራን እንገኛለኝ። በሴሚስተሩ መሃከል-አጋማሽ እነዚህን ድጋፎች በአካል የመስጠት እቅዳችንን በመጪዎቹ ወራት ሴፕቴምበር አጋማሽ ላይ ይበልጥ መረጃ እንሰጣለን።
MCPS ለፎል ሴሚስተር የተለመደውን መደበኛ የውጤት አሰጣጥ ሲስተም ይጠቀማል። በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ የውጤት አሰጣጥ ሲስተማችንን ማሻሻል እንዳለብን ግምት ቢኖረንም፣ የተማሪዎቻችንን ሥራ፣ መማራቸውን እና ያሳዩትን ለውጥ እርምጃ የሚያንፀባርቅ መመዘኛ ማእቀፍ ያለን መሆኑን ማረጋገጥ እንፈልጋለን።
ለቤተሰብ በሌላ ጊዜ ለማግኘት እንዲችሉ MCPS ትምህርቶችን ሪኮርድ የማድረግ ሒደት ላይ ነን። ምስጢራዊነትን እና ብህትውነትን ለመጠበቅ ቅድመ ጥንቃቄ ይደረጋል።
ለመመረቂያ የተማሪ የአገልግሎት ትምህርት አስፈላጊነትን የሜሪላንድ የትምህርት ቦርድ ባለፈው ስፕሪንግ ላይ ያስቀረ ቢሆንም፣ ስለዚህኛው ዓመት ገና ውሳኔ እየተጠባበቅን ነው። እስከዚያ፣ ቨርቹወል እና የርቀት-የአገልግሎት ትምህርት እድሎችን መቀበላችንን እንቀጥላለን
የቁርስ እና የምሣ ምግቦች ይዘጋጃሉ። የምግብ ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ቁጥር ለመወሰን እና ተማሪዎች እነዚህን ምግቦች ለማግኘት ስለሚችሉበት ሒደት ዝርዝር ተግባሮችን በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን።
በዚህ ፎል በትምህርት ቤቶቻችን ህንፃዎች ላይ በትምህርት እድሜ ክልል ለሚገኙ ህፃናት የእንክብካቤ አገልግሎት ሰጪዎች መሥራት ስለሚፈልጉበት ሁኔታ MCPS ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት እና የህዝብ ፋሲሊቲዎች የማህበረሰብ አጠቃቀም መስሪያ ቤት (CUPF) ጋር በጋራ እየሠራን እንገኛለን። እነዚህ በ CUPF የሚተዳደሩ ትምህርት በመጀመር እድሜ ለሚገኙ ልጆች በትምህርት ቤቶቻችን ቦታዎችን በመጋራት ቅድመ እና ድህረ እንክብካቤ የሚሰጡ ናቸው። በትምህርት ቤቶች አንዳንድ የትምህርት እድሜ ልጆችን እንክብካቤ ለመስጠት የሚታሰበው የመጀመሪያ ቀን ሴፕቴምበር 14 ነው። የተፈቀዳለቸው እንክብካቤ ሰጪዎች በጥቂት ቡድን ማድረግን እና በቡድኖቹ መካከል ርቀት መጠበቅን እንዲሁም የስቴት እና የካውንቲ የፈቃድ አሰጣጥ እና የህዝብ የጤና መስፈርቶችን መጠበቅ አለባቸው

ኦገስት 31 ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በወሩ መገባደጃ ላይ ቤተሰቦች ከዲስትሪክቱ እና ከየትምህርት ቤቶቻቸው በተከታታይ መልእክቶችን እንደሚያገኙ መጠበቅ አለባቸው። ከዚህ በታች ያሉት በቅርብ ጊዜ ያደረግነው ውይይት ተጨማሪ መግለጫዎች ሲሆኑ፤ የእኛን የማገገሚያ እቅድ ለሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት (MSDE) ስለማቅረብ፣ ስለ Give BACKpacks የማሰባሰብ ዘመቻ፣ ስለ ተሻሻለው የተማሪ መብቶች እና ግዴታዎች እና ስለ ስነምግባር መመሪያ መምሪያ፣ ቀጣዮቹን webinars በሚመለከት ስለ ጾታዊ ጥቃት፣ የስምምነት እና ጤናማ ግንኙነቶች፣ እና የስንየር ፎተግራፎችን የሚያካትት ነው።

ስለትብብርዎ እናመሰግናለን።
አብረን እየሥራን፣ ለልጆቻችን ይህ ስኬታማ የትምህርት ዓመት እንደሚሆን እናረጋግጣለን።

ከአክብሮት ጋር፣

Jack R. Smith, Ph.D. 
Superintendent of Schools


በረቂቅ የ MCPS የማገገሚያ እቅድ ላይ የተደረጉ ቨርቹወል ውይይቶች

MCPS በረቂቅ እቅዶቻችን ላይ ሁለት ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን —አንዱ በ ኦገስት 12 ከወላጆች እና ከማህበረሰብ ጋር ሲሆን እና ሌላኛው በ ኦገስት 13 ከተማሪዎች ጋር የተደረገ ውይይት ነው። በወቅቱ የቀጥታ ስርጭቱን ለመከታተል ያልቻሉ ከሆነ፣ ስለ እቅድ ዝግጅታችን ጥረት ይበልጥ ለማወቅ እንዲችሉ ፕሮግራሞቹን እንዲመለከቱ አበረታታዎታለሁ።


የማገገሚያ እቅድ ለስቴት ስለማቅረብ

የ MSDE ን የማገገሚያ እቅድ መስፈርት ለማሳካት፣ የእኛን የፎል 2020 የማገገሚያ እቅድ መምሪያ በ ድረ-ገጽ ላይ ለጥፈናል። ዶኩመንቱ-ሠነዱ የሚያንፀባርቀው ኦገስት 6/2020 ለትምህርት ቦርድ ስብሰባ የቀረበውን መረጃ ነው። ስለ እንደገና መክፈት የ MSDE ልዩ መስፈርቶች በቀረበው ሠነድ ላይ በአባሪነት ተጨምሯል። MSDE የትምህርት ሲስተም እቅዶቹን ከገመገሙ በኋላ እንደሚያፀድቁ ገልጸውልናል።

ማስታወሻ፦ የቀረበው ሠነድ ከኦገስት 6 ስብሰባ በኋላ በፕላኑ ላይ ያደረግናቸውን ማሻሻያዎች-ክለሳዎችን (ከላይ የተዘረዘሩትን) አያንጸባርቅም።


ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የትምህርት መርጃ አቅርቦቶችን መስጠት

በርካታ ተማሪዎች ከመቼውም ጊዜ የበለጠ አሁን፣ የትምህርት ቤት አቅርቦቶችን ለማግኘት እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

ተማሪዎች ከርቀት ትምህርት ሁኔታ ጋር በመለማመድ ላይ ስለሆኑ ሁሉም ተማሪዎች በትምህርታቸው የመዳበር እድል እንዲኖራቸው አስፈላጊ የትምህርት መገልገያዎችን እና ሪሶርሶችን መስጠት ወሳኝነት አለው።

በዚህ ዓመት ለተማሪዎቻችን የሚያስፈልጋቸውን ለማሟላት ዓመታዊ Give BACKpacks የማሰባሰብ ዘመቻ እጅግ አስፈላጊ ነው። በ $10 ዶላር አንድ ተማሪ ቨርቹወል ለመማር የሚያስፈልጉትን አቅርቦቶች፣ ወረቀት፣ የስእል መሥሪያ (crayons)፣ እርሳሶች/እስክሪብቶዎች፣ ነጭ ሠሌዳዎችን፣ የደረቅ ላጲስ ማርከሮችን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለመስጠት ይችላሉ።

በርካታ ተማሪዎች እቤታቸው ሆነው ለመማር የሚያስፈልጓቸው ቁሳቁሶች አይኖሯቸውም፤ የእርስዎ ልግስና ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ በስኬታማነት እንዲያተኩሩ የሚያስፈልጋቸውን አቅርቦቶች ለመስጠት ይረዳል።

ስለ "MCPS Give Backpacks" በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች  ያንብቡ።

የተማሪ መብቶችና ሃላፊነቶች-ግዴታዎች

ሠላማዊ፣ ምርታማ እና አስተማማኝ የሆነ የትምህርት አካባቢን ለማረጋገጥ፣ ተማሪዎች፣ ወላጆች እና ሠራተኞች ስለ ትምህርት ቤት ህጎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች እንዲያውቁ እና ከተማሪ ስለሚጠበቅ ስነምግባር፣ እና እነዚህን ህጎች መጣስ ስለሚያከትለው ውጤት እንዲገነዘቡ ለመርዳት MCPS ሁለት ዶኩመንቶችን አዘጋጅቷል።

የአንድ ተማሪ መበቶችና ሀላፊነቶች-ግዴታዎች መመርያ ተማሪዎች በ MCPS የሚደሰቱባቸው መብቶችና ሀላፊነቶች-ግዴታዎች አጭር መግላጫና በተማሪዎች ላይ ተፅእኖ ያላቸው ህጎችና ሀላፊነቶች መግለጫ ነው።

የተማሪ ስነምግባር መመሪያ-Student Code of Conduct ስለ ዲስፕሊን ሒደቶች እና ፕሮቶኮሎችን እንዲሁም ተማሪዎች የተለያዩ ፖሊሲዎችን፣ ደንቦችን እና ህጎችን መመሪያዎችን በሚጥሱበት ጊዜ የተለያዩ የዲስፕሊን እርምጃዎች እንደሚወሰዱ አጠቃላይ ግንዛቤ ይሰጣል። መመሪያው በተጨማሪ ስለ MCPS የዲስፕሊን ፍልስፍና የሚገልጽ ከመሆኑም በላይ የተለያዩ አይነት የዲስፕሊን እርምጃዎችን ያብራራል።

እነዚህን ሁለቱን መመሪያዎች እና ሌሎችም ያሉንን የሃይማኖት ብዝሃነትን ስለማክበር መመሪያ-Guidelines for Respecting Religious Diversity እና ስለ ተማሪ ጾታ መለያ መመሪያ-Guidelines for Student Gender Identity፣በ MCPS ድረ-ገጽ ላይ መመልከት ይችላሉ።


ስለ ጾታዊ ጥቃት Choose Respect Montgomery - በመረጃ መረብ ቀጥታ የቪድኦ ስርጭት (Webinars) ያካሄዳል።

"Choose Respect Montgomery" ማለት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የቤት ውስጥ ግጭትን የመከላከል አስተባባሪ ካውንስል፣ ጾታዊ ጥቃትን ስለመከላከል፣ በስምምነት የሚደረጉ ጤናማ ግንኙነቶች፣ እና አገራዊ እና የአካባቢ ውይይቶች እና በቅርብ ጊዜ የተደረጉ የማህበራዊ ሚድያ ላይ የተለጠፉ ጉዳዮች በሚመለከት ሪሶርሶችን እና ትምህርት ለመስጠት ሁለት በመረጃ መረብ የሚላክ ቀጥታ የቪድኦ ስርጭት (Webinars) ይካሄዳል።

ሁለት ቨርቹወል webinars የሚደረጉ ሲሆን—አንድ ለወላጆች እና አንድ ለወጣቶች—በሜሪላንድ የፀረ ጾታዊ ጥቃት ተከላካይ ጥምረት አማካይነት ይካሄዳል።

ለወላጆች የሚደረገው webinar ማክሰኞ፣ ኦገስት 18 ከ 6–7 p.m. በ Zoom አማካይነት ይካሄዳል። ስለ ጾታዊ ጥቃት፣ በስምምነት ስለሚደረጉ ጤናማ ግንኙነቶች፣ እነዚህን ጉዳዮች በሚመለከት ከልጆች ጋር እንዴት መነጋገር እንደሚቻል፣ እና ሠላም ስለ ሰፈነበት ማህበረሰብ እንዴት ማቀንቀን እንደሚቻል መሠረታዊ ግንዛቤ ይሰጣል።

እዚህ ይመዝገቡ

ለተማሪዎች የሚደረገው webinar እሮብ፣ ኦገስት 19 ከ 6–7 p.m. በ Zoom አማካይነት ይካሄዳል። ትንንሽ ልጆች ስለ ጾታዊ ጥቃት፣ የስምምነት ጤናማ ግንኙነቶች፣ ሠላማዊና ጤናማ አካባቢዎችን ለመፍጠር የራሳቸውን ተጽእኖ መፍጠር እና የሚያሰጉ ሁኔታዎችን ለመካከል ስለሚደረጉ ጣልቃገብነቶች፣ እና ጓደኞቻቸውን እንዴት ለመርዳት እንደሚችሉ መሠረታዊ ግንዛቤዎችን ይማራሉ።

እዚህ ይመዝገቡ።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ Choose Respect Montgomery website የሚለውን ድረ-ገጽ ይጎብኙ።

የመከባበርን ባህል መፍጠር


ስለ SAT ፈተናዎች

አሁን ባለው ወቅታዊ መመሪያ ላይ በመመሥረት እና ከአጎራባች ዲስትሪክቶች ጋር በመተባበር፣ ኦገስት 29 በ MCPS ህንፃዎች ውስጥ መካሄድ የነበረባቸው የ SAT ፈተናዎች ተሠርዝዋል። ወደፊት በመቀጠል፣ ሁኔታዎች የሚፈቅዱ ከሆነ፣ የፎል 2020 ፈተናዎችን የመውሰድ እድሎችን ለመስጠት ከኮሌጅ ቦርድ እና ከአካባቢ የጤና ሃላፊዎች ጋር በቅርበት እየሠራን እንገኛለን። እነዚህም የሚያካትቱት፦ በሴፕቴምበር/ኦክቶበር በትምህርት ቀን ስለሚሰጡ ፈተናዎች፣ በቅዳሜ ቀን የ SAT ፈተናዎች፣ ሴፕቴምበር 26፣ ኦክቶበር 3፣ ኖቬምበር 7፣ እና ዲሴምበር 5 የፎል ACT ምዘናዎችን ይመለከታል። እባክዎ የእነዚህ ፈተናዎችና ምዘናዎች አሠጣጥ ከኮቪድ-19 ጋር በተገናኘ በአካባቢ የጤና ኃላፊዎች ውሳኔ እና የትምህርት ቤቶች የሥራ እንቅስቃሴ፣እና በሠራተኞች መገኘት ላይ የሚሞረኮዝ መሆኑን ግንዛቤ ይውሰዱ። በእነዚህ እቅዶች ላይ መሥራታችንን እየቀጠልን የምዝገባ ገደብ ከማብቃቱ በፊት ለማህበረሰቡ መረጃዎችን እናስተላልፋለን።

በሠመር እና በፎል ወቅት ሙሉ የፈተና መልመጃዎችን ለመሥራት እና በግላዊ ሁኔታ ላይ የተመረኮዘ የትምህርት መርጃዎችን በሚመለከት ተማሪዎችን ለመርዳት College Board and Khan Academy በኦንላይን ሪሶርሶችን በነፃ መስጠት ይቀጥላሉ።


የስንየሮች ፎቶ

በተለምዶ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በየግላቸው ፎቶ አንሽዎች እየመጡ የሲንየር ፎተግራፍ የመነሣት እድል ያመቻቹላቸው ነበር። ከጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት በተሰጠ የወቅቱ መመሪያ መሠረት፣ የእኛ ሁሉተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሴፕቴምበር አጋማሽ ላይ እነዚህን በአካል የመገኘት in-person እድሎች መስጠት ይጀምራሉ። ይህም ትምህርት ቤቶቻችን የህዝብ ጤና ጥበቃ መመሪያ ፕሮቶኮሎችን በቋሚነት ለመጠበቅ እና እያንዳንዱን ሲንየር በተሣካ የጊዜ ሠሌዳ ለማስገባት እየዞሩ ፎተግራፍ ከሚያነሱት ጋር በመተባበር ለመሥራት የበለጠ ጊዜ ይሰጣቸዋል።