Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: June 25, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


MCPS በሠመር ወቅት በሙሉ የቁርስ እና የምሣ ምግቦችን ይሰጣል።

ውድ ወላጆች እና አሳዳጊዎች፡-

ከጁላይ 6/2020 ጀምሮ፣ MCPS ለሁሉም የሞንትጎመሪ ልጆች እና ለሁሉም የ MCPS ተማሪዎች (እድሜ ሳይለይ) በካውንቲው እስከ 100 ጣቢያዎች ላይ የቁርስ እና የምሣ ምግቦችን ይሰጣል። የምግብ ማከፋፈል የሚካሄደው ከ 10 a.m. – 12 p.m. በትምህርት ቤት ጣቢያዎች ሲሆን ከ 9 a.m. – 10 a.m. በአውቶቡስ የሚከፋፈልባቸው ቦታዎች ላይ ነው።

አጠቃላይ የጣቢያዎችን ዝርዝር ይመልከቱ፦


በዚህ ወቅት፣ ለእራት የሚሆን ምግብ ለመስጠት MCPS ከፌደራል መንግሥት እንዳይከፈል ይሁንታን-waiver አላገኘንም። እንዳይከፈል ይሁንታው-waiver ከፀደቀ፣ ዲስትሪክቱ በሚያካሄደው የምግብ እደላ ላይ እራት ይጨመራል።

የትምህርት ጊዜ ሰሌዳ
የምግብ ሥርጭት የሚካሄደው በሣምንት አራት ቀን ይሆናል፦ ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ ረቡዕ፣ እና ዓርብ። በየሣምንቱ ረቡዕ ቀን፣ MCPS ለሁለት ቀኖች የሚሆን ምግብ ያከፋፍላል። በየሣምንቱ ሐሙስ ቀን፣ የምግብ ማከፋፈያ ጣቢያዎች በሙሉ ዝግ ይሆናሉ። ይህ አይነቱ መርኃግብር የተማሪዎችን እና የሠራተኞችን ጤንነት እና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚረዳ ከመሆኑም በላይ፣ የ COVID-19 (ኮሮናቫይረስ-coronavirus) ወረርሽኝን የመሠራጨት እድል ይቀንሳል።

የማህበረሰብ አጋሮች እና የካውንቲ ሪሶርሶች
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከ መና የምግብ ማዕከል (Manna Food Center) እና በየሣምንቱ ማለቂያ ለቤተሰቦች ምግብ የሚሰጥ-"Women Who Care Ministries" ጋር በሠመር ወቅት ግንኙነቱን ይቀጥላል። ስለ ማከፋፈያ ጊዜዎች እና ጣቢያዎች በ MCPS Meals Service web page-የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የምግብ አገልግሎት ድረ-ገጽ ላይ ይፋ ይደረጋል። እንዲሁም፣ ቤተሰቦች ስለተጨማሪ ሪሶርሶች የሞንትጎመሪ ካውንቲን COVID-19 Food Resources Page-ስለኮቪድ- 19 የምግብ ሪሶርስ ገጽ እንዲጎበኙ እናበረታታለን።

ከሰላምታ ጋር
Montgomery County Public Schools