ይህ ኢሜይል በሚገባ አይታይም ወይ? በእርስዎ መዳሰሻ/browser ይመልከቱትቀን፦ ኦገስት 23/2019


English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

የተማሪን ደህንነት ስለማረጋገጥ - ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ዋና የደህንነት ኃላፊ ኤድዋርድ ኤ. ክላርክ (MCPS Chief Safety Officer Edward A. Clarke) የተሰጠ መልእክት

ስለደህንነት ቪድዎ

በእንግሊዝኛ የምስል መግለጫ ፅሑፍ ቪድዎ

ማውጫ

አዲስ የትምህርት ዓመት እየተቃረበ ሲመጣ፣ ስለደህንነት ጠቃሚ የሆነውን ርእስ እንደገና ማንሣት አስፈላጊ ነው። በትምህርት ሥርዓታችን ውስጥ ዋናው ዓላማችን ተማሪዎቻችንን በሙሉ ስለ ወደፊት እድገት እና ጥንካሬ ማዘጋጀት ሲሆን፣ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቻችን ደህንነት እና ምቾት ካልተሰማቸው ከታለመለት ግብ መድረስ እንደማይቻል እንገነዘባለን።

ስለዚህ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች ደህንነቱ የተሟላ ለትምህርታቸው ደጋፊ የሚሆን የትምህርት አካባቢ ለመስጠት ቁርጠኛ ነው። ይህንን የምናደርገው ስርዓት አቀፍ የሠላም እና የደህንነት ስልት በመዘርጋት በርካታ ስልቶችን፣ በተባበረ/የተቀናበረ እና ስትራቴጂ የተሞላበት አኳኋን በማስፈን ነው። የእኛ ሥራ የተገነባበት መሠረት፤ የስቴት እና የአካባቢ ህጎች እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ፖሊሲዎች፣ የተማሪዎች ድምፅ፣ ሠራተኞች፣ ወላጆች እና የማህበረሰብ አባላት ድምፅ ላይ የተገነባ ነው።

ከማውጫው ላይ ወይም ወደታችን በመሸብለል የተማሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በየቀኑ MCPS የሚሠራቸውን መንገዶች በጥቂቱ መመልከት ይችላሉ።



ስለ ደህንነት ግንባታ

  • በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የድንገተኛ-የአስቸኳይ ጊዜ እቅዶች ተሻሽለዋል የበለጠ ይገንዘቡ
  • በትምህርት ቤት አስቸኳይ-ድንገተኛ ሁኔታ በሚከሰትበት ጊዜ እርዳታ ለማድረግ የሚችሉ በተጠንቀቅ የሚገኝ ቡድን በሥፍራው አለ።
  • ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የፖሊስ ዲፓርትመንት፣ የእሳት አደጋ የመታደግ አገልግሎት፣ እና ትምህርት ቤት ላይ ድንገተኛ/አስቸኳይ ሁኔታ ባጋጠመ ጊዜ ድጋፍ የሚሰጡ ሌላ የካውንቲ ኤጀንሲዎች ጋር በትብብር እንሠራለን MOU ያንብቡ
  • በሁሉም ትምህርት ቤቶች እና የትምህርት ተቋማት የሚገኙበት ቦታዎች ላይ የትምህርት ቤት ደህንነት ግምገማዎች ይካሄዳሉ
  • ስለእሳት እና ድንገተኛ-አስቸኳይ ከባድ የአየር ሁኔታዎች የደህንነት ጥበቃ ልምምዶች ይሰጣሉ
  • የአደጋ ጥቃት ፈፃሚን ለመከላከል የሚያስችል የተሻሻለ/ የዳበረ የዝግጁነት ስልጠና የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ
  • በእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የት/ቤት ደህንነት ጥበቃ ኦፊሰር የበለጠ ያንብቡ
  • በጠቅላላ በካውንቲው የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶችን፣ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶችን፣ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችን የሚረዱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ለዓላማቸው የቆሙ የMCPS ሰኩሪቲ/የጥበቃ ሠራተኞች
  • በት/ቤቶች ላይ መቆጣጠሪያ ያላቸው የመግቢያ በር ሲስተም
  • ለትምህርት ቤቶች የደህንነት ጥበቃ ጥይት መከላከያ ሰደርያ/ቨስቲቡለስ/vestibules ማሠራጨት
  • የብሔራዊ እና የስቴት የጾታዊ ጥቃት ፈጻሚዎች የመረጃ ቋት-ዳታቤዝ ቢኖርም ወደ ት/ቤት የሚመጡ ሁሉንም ጎብኚዎች ለማጣራት በትምህርት ቤቶች የጎብኚ ማኔጅመንት ስርዓት
  • ስለ ት/ቤት ሠላም እና ደህንነት ሁለገብ ሪፖርት የ2018 ሪፖርት እና የሥራ እቅድ ያንብቡ
  • በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እና በሚድል ስኩል በሙሉ የደህንነት ካሜራዎች፣ በኤለመንተሪ ት/ቤቶችም ካሜራዎች እየተጨመሩ ናቸው
  • ለትምህርት ቤቶች የሪሶርስ ኦፊሰሮች እና የሰኩሪቲ ሠራተኞች አስፈላጊ የሆነ ስልጠና መስጠት
  • ሠላም እና ደህንነትን ለመገንባት የሁሉንም የሥራ ባልደረቦች ንቃት እና ትኩረት መስጠት

እንደገና ወደ ከፍታ


ከትምህርት ቤት ሠዓት-በኋላ ክትትል/ቁጥጥር

  • የስፖርት እና ከትምህርት ቤት-ሠአት በኋላ የሚኖር እንቅስቃሴን በንቃት የመከታተል እና የመቆጣጠር ፕላኖች
  • ሴፕቴምበት 2019፣ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የስቴት ዓቃቤ ህግ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ከትምህርት-ሠዓት በኋላ ስለሚደረጉት የደህንነት ቁጥጥር ሁኔታ የውጫዊ አካል ግምገማ ይፋ ይደረጋል


እንደገና ወደ ከፍታ


የተማሪ ጤንነት እና ደህንነት

ደህንነት
  • በሁሉም ትምህርት ቤቶች "Be Well 365" አጠቃላይ የማህበራዊ-ስሜት ክህሎት ግንባታ ይበልጥ ግንዛቤ ያግኙ
  • የሚተን/ወደጋዝነት የሚለወጡ ነገሮችን ስለማጨስ አደገኛነት የሚያስረዱ መረጃዎች አገናኝ/Link
  • ትምህርት ቤት የሚገኙ የጤንነት-ደህና ቁመና ማእከሎች
  • በሁሉም ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤት ማህበረሰብ የጤና ነርሶች ወይም የትምህርት ቤት የጤና ክፍል ቴክኒሻኖች ይበልጥ ግንዛቤ ያግኙ
  • ለሁሉም የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተማሪዎች ራስን ስለማጥፋት የመከላከል ስልጠና
  • ስለ አእምሮ ጤንነት ቀውስ ስጋት፣ ጥቃት፣ ማስፈራራት እና ረብሻ ወይም ሌሎችም ነገሮችን ስጋት ሪፖርት ለማድረግ ተደራሽ ሚስጥራዊ መስመር ይበልጥ ግንዛቤ ያግኙ
  • BtheOne ስለ አእምሮ ጤንነት ቅስቀሳ-ዘመቻ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ጋር በመተባበር፣ Every Mind and Family Services, Inc. ስለ ቅስቀሳው ይማሩ
  • የማስፈራራት ስነምግባር ምርመራን በሚመለከት የሠራተኞች ስልጠና
  • በሁሉም ደረጃዎች ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች ሁለገብ የጤና ሥርዓተ ትምህርት/ከሪኩለም
  • የአእምሮ ጤንነት ሪሶርሶች እና ለቀውስ ሁኔታ ለተማሪዎች የሚደረጉ ድጋፎች የበለጠ ይወቁ
  • ራስን መግደል ስለመከላከል እና ጣልቃ ገብነት ለሁሉም ሠራተኞች ግዴታ የሆነ ስልጠና
  • ራስን የመግደል ስጋትን ሪፖርት ማድረጊያ የተሻሻለ/የተቀናጀ አሠራር-ሂደት የበለጠ ያንብቡ
  • ለትምህርት ተነሳሽነት አገናኝ የበለጠ ያንብቡ
  • ከሱሰኝነት ለተላቀቁ ተማሪዎች የማገገሚያ አካደሚክ ፕሮግራም የበለጠ ይወቁ
  • ለሞንትጎመሪ ካውንቲ የአደንዛዥ እፅ መጥፎ አጠቃቀም ግምገማ እና ህክምና መጠቀሚያዎች/Resources መጠቀሚያዎችን ይመልከቱ
  • ለተማሪዎች ፍትሃዊ የተሃድሶ ፕሮግራሞች የበለጠ ይወቁ
  • ለትምህርት ባለሙያዎች አስፈላጊነት ያለው/Mandatory የብቃት ባህልን ስለማዳበር ስልጠና መስጠት

እንደገና ወደ ከፍታ


የአውቶቡስ ላይ ደህንነት

ድጋሚ ወደ ከፍታ


ስለደህንነት ህጎች፣ ፖሊሲዎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች

  • "Maryland Safe to Learn Act of 2018" ላይ የሚገኘውን ምንባብ ደንቡን አንብቡ
  • በሥራ ላይ የዋለ የትምህርት ቦርድ ፖሊሲ/Board of Education Policy COA፦ ስለ ተማሪ ደህንነት እና የትምህርት ቤት ሠላም/Student Well-being and School Safety ይበልጥ ግንዛቤ ይውሰዱ
  • ስለ አስጊ ስነምግባር ምርመራ ፕሮቶኮል የተዘጋጀውን ደንብ"Regulation COA-RA" ማዳበር ደንቡን ያንብቡ
  • ተግባሪዊ ስለማድረግ Policy ACA: አድሎ የሌለበት/Nondiscrimination፣ ፍትኃዊ/Equity፣ እና የዳበረ ባህልን/Cultural Proficiency(ፖሊሲውን ያንብቡ)

ዳግም ወደ ከፍታ


የእግረኛ ተጓዥ ደህንነት

  • የእግረኛ ደህንነት ሪሶርሰስ (የበለጠ ይወቁ)
  • ስለእግረኞች ደህንነት የማህበረሰብ አገልግሎት ማስታወቂያ-ወደ ት/ቤት መጓዝ ማለት ውድድር አይደለም “Getting to School is Not a Race” (ይመልከቱ
  • ስለ እግረኞች እና ብስክሌተኞች ደህንነት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የመንግስት አስተዳደር ጋር ትብብር ማድረግ ቪድዎ ይመልከቱ)
  • ስለ እግረኞች ደህንነት የሚሰጥ ትምህርት በጤና ትምህርት ላይ ተካቷል

ዳግም ወደ ከፍታ


በጉስቁልና እና በቸልተኝነት የተተወ(ች) ልጅ

  • ለሁሉም ሠራተኞች፣ ኮንትራክተሮች፣ እና አንዳንድ በጎ ፈቃደኞች ዘርፈ-ብዙ የበፊት ታሪካቸውን ማጣራት ይበልጥ ለማወቅ
  • ለሠራተኞች፣ ለኮንትራክተሮች እና ለበጎ ፈቃደኞች ስለ ልጆች መጎሣቆል እና ቸልተኝነትን መከላከል፣ ማጤን እና ሪፖርት ስለማድረግ ግዴታዊ የሆነ ስልጠና ይሰጣል ስልጠና ይውሰዱ
  • ከእድሜ-እና ከእድገት ጋር ተገቢ የሆነ የግል ሰውነትን ደህንነት ስለመጠበቅ ለሁሉም ተማሪዎች ትምህርት ይሰጣል ትምህርቶቹን ይመልከቱ
  • ማጎሳቆል እና የጥቃት ተግባርን ሪፖርት ስለማድረግ የተቀናጀ ሂደት (ስለ ህፃን/ልጅ ማጎሳቆል የእኛን የ MCPS የሪፖርት አደራረግ ፖሊሲ ይመልከቱ)
  • ለሁሉም ሠራተኞች የስነምግባር ደንብ የበለጠ ያንብቡ
  • በጉስቁልና እና በቸልተኝነት የተተወ(ች) ልጅ የባለድርሻ አካላት በተከታታይ የሚያሻሽል ቡድን መፍጠር (ይበልጥ ያንብቡ)
  • በጉስቁልና ላይ ስለሚገኝ/ስለምትገኝ እና በቸልተኝነት የተተወ(ች) ልጅ በአውታረ-መረብ ሪፖርት ማድረግ ቅጹን ይመልከቱ

ዳግም ወደ ከፍታ


የማስጨነቅ/ማንገላታት እና የማስፈራራት መከላከል

መነዝነዝ/ማስጨነቅ
  • ስለ መነዝነዝ/መጨቅጨቅ ክስተቶች ሪፖርት ስለማድረግ ሂደት (መነዝነዝ-መጨቅጨቅን ሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ/Bullying Reporting Form)
  • ስለ ማስጨነቅ/ማንገላታት፣ ማስገደድ፣ እና ማስፈራራት መከላከል እና ሪፖርት ስለማድረግ ለሁሉም ሠራተኞች ስልጠና መስጠት
  • አደገኛነቱን ለይተው እንዲያውቁ እና አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖራቸው ለሁሉም የአትሌቲክስ-ተማሪዎች ስልጠና መስጠት (ይበልጥ ግንዛቤ ይውሰዱ)
  • በሁሉም የአትሌቲክስ ሁነቶች ወቅት የአድሎአዊነት ባህርይን ለመከላከል እና ሪፖርት ማድረግን ለማበረታታት ከስፖርተኝነት የሚጠበቁ ስነምግባሮችን ትኩረት መጨመር
  • ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሠራተኞች ከህግ አስከባሪዎች ጋር በመተባበር ስለወሮበላነት-እንዲነቁ/Gang-awareness ስልጠና መስጠት
  • ስለ ተማሪ የጾታ ማንነት ጉዳዮች የተሻሻሉ መመሪያዎች (የበለጠ ያንብቡ)
  • ለተማሪዎች የካውንስሊንግ/የምክር ድጋፍ
  • የኃይማኖት ልዩነቶችን ስለ ማክበር መመሪያ(መመሪያዎቹን ያንብቡ)
  • አክብሮትን ይምረጡ የልጆች ጤናማ የፍቅር ግንኙነት ዓመታዊ ኮንፈረንስ የበለጠ ይማሩ

ዳግም ወደ ከፍታ


የአካባቢ ደህንነት

ዳግም ወደ ከፍታ


በኤሌክትሮኒክስ አማካይነት የሚደረግ ጥቃትን መከላከል

ዲጅታል

ዳግም ወደ ከፍታ


ከእርስዎ ጋር ታላቅ እና ሠላማዊ የትምህርት ዓመት እንዲሆንልን እንመኛለን!

ከአክብሮት ጋር

Edward A. Clarke
Chief Safety Officer