Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: June 4, 2020


mcps logo

English |  español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የውጤት አሰጣጥ አማራጮች ስልት

የተከበራችሁ ወላጆችና አሳዳጊዎች፣

ለ4ኛው የማርክ ውጤት መስጫ ክፍለጊዜ (MP4)፣ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው ክሬዲት ለሚሰጥባቸው ኮርሶች በፊደል ከሚሰጥ ማርክ ይልቅ "አልፏል-አልፋለች ወይም አላጠናቀቀም-አላጠናቀቀችም/Pass (P) or Incomplete (I)" የሚለውን ያገኛሉ። ተማሪዎች በወላጆቻቸው/በሞግዚቶቻቸው ድጋፍ፣ የመጨረሻውን “ሴሚስተር 2” ውጤት (ለምሳሌ፦ A, B, C, D, E) ወይም Pass/Incomplete (P/I) ከሁለት በአንዱ አይነት እንዲሆን ለመምረጥ ይችላሉ። የ Grading Options Tool-የውጤት አሰጣጥ አማራጮች ስልት የተቀየሰው ተማሪዎች የራሳቸውን አማራጭ እንዲያቀርቡ እና በእያንዳንዱ ኮርስ ላይ እነርሱን ይበልጥ የሚጠቅም አማራጭ ለመስጠት ነው። የማርክ-ውጤት አሰጣጥ አማራጭ ያለው ለ “ሴሚስተር 2” ኮርሶች ብቻ ሲሆን፣ ሙሉ አመት ለሚወሰዱ ኮርሶች ወይም ክሬዲት ለማይሰጥባቸው ኮርሶች አይሆንም-አይደለም።

የማርክ ውጤት አሠጣጥ ምርጫህ(ሽ)ን አቅርብ(ቢ) (Instructions for Students)
ለ “ሴሚስተር 2” አንተ(ቺ) የመረጥካቸውን-የመረጥሻቸውን የማርክ ውጤት አሠጣጥ ለማየት፣

  1. ይህንን ድረ-ገጽ ጎብኝ(ኚ)፦ https://bit.ly/mcpsmd-grade-display-preference
  2. ሎግኢን ለማድረግ፦ የአንተ(ች)ን MCPS Google የተጠቃሚ ስም ለምሳሌ፦ (ex., student_id@mcpsmd.net) and your password to log in መጠቀም ያስፈልጋል።
  3. ምርጫዎችህ(ሽ)ን አሳይ። ለእያንዳንዱ ኮርስ የበለጠ የሚጠቅመውን ለመምረጥ "Grade Calculator" ተጠቀም(ሚ)። ከጨረስክ(ሽ) በኋላ Submit የሚለውን ተጫን(ኚ)
  4. አማራጮችህ(ሽ)ን ካቀረብክ(ሽ) በኋላ፣ ሪኮርድ እንዲደረግልህ(ሽ) ለ MCPS Google account የኢሜይል ማረጋገጫ ይላካል።

አስፈላጊ መረጃዎች

  • Timeline/የጊዜ ገደብ ጁን 4/2020 እና ጁን 12/2020፣ መካከል ተማሪዎች የ “ሴሚስተር 2” የማርክ ውጤቶች በሪፖርት ካርዳቸው ላይ እንዴት እንዲታይ እንደሚፈልጉ ምርጫዎቻቸውን ለማቅረብ ይችላሉ።
  • Daily Limits/እለታዊ ገደቦች → ተማሪዎች በመሃል በርካታ ጊዜ ምርጫዎቻቸውን ለማስተካከል ይችላሉ፣ ነገር ግን በቀን ሦስት ጊዜ ማድረግ/እና ማቅረብ ብቻ ይቻላል።
  • Course List/የኮርስ ዝርዝር → መገልገያው (The tool) ለተማሪዎች የሚያሳየው ክሬዲት የሚሰጥባቸውን ኮርሶች ብቻ ነው።
  • Default Choice → በምርጫ ካልተገለጸ የ "The default report card" ላይ በፊደል የሚመዘገበው የማርክ ውጤት አጠቃላይ GPA ን የሚያሻሽል እስከሆነ ድረስ በካርድ ላይ የሚቀመጠው በፊደል “Letter” ይሆናል። ካልሆነም “P” ይመዘገባል።

ስለ ማርክ አሰጣጥ ስልት ጥያቄ ካለ ወይም እርዳታ ካስፈለገ፣ እባክዎ help guide የሚለውን ይመልከቱ።

ከሰላምታ ጋር

Montgomery County Public Schools


Important Online Resources: