Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: May 05, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ሠራተኞች እና ተማሪዎች

ማክሰኞ፣ ሜይ 12/2020 የትምህርት ቦርድ ስለ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የውጤት እና ሪፖርት አሰጣጥ እቅድ-ውይይት በማድረግ እርምጃ ይወስዳል። እቅዱ- ስለ አጠቃላይ የሴሚስተር ውጤት፣ ስለ አማካይ ውጤት (GPA) ስሌት፣ እና አጠቃላይ ውጤት እንዴት በትራንስክሪፕቶች ላይ ሪፖርት እንደሚደረግ ያካትታል። ስብሰባው የሚጀመረው በ 11 a.m. ሲሆን በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ድረ-ገጽ MCPS website እና በ MCPS-TV ቴሌቪዥን በቀጥታ ይተላለፋል። እባክዎ ይህንን ጠቃሚ ውይይት ከፍተው ያዳምጡ። ቦርዱ የማጠቃለያ እርምጃ-ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ለማህበረሰቡ ወቅታዊ መረጃ እንሰጣለን።

ባለፉት በርካታ ሣምንታት፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለሁለተኛው ሴሚስተር በርካታ የውጤት አሰጣጥ እና ሪፖርት የማድረግ አማራጮችን ቃኝቷል። ሠራተኞች ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያዳበሩትን በርካታ ጽንሰሃሳቦችን እና አስተያየቶችን ሠራተኞች፣ ወላጆች እና ተማሪዎቻ አማካይነት በጥንቃቄ ተመልክተው የሰጡትን ግብረመልስ ጭምር ለቦርድ ያቀርባሉ።

ቦርዱ የተለያዩ ጽንሰሃሳቦችን ጭምር ይወያያል፦

  • በሁሉም ዘንድ እንደሚሠራበት ለሁሉም ተማሪዎች የሴሚስተሩ የመጨረሻ ውጤት "Pass/Incomplete"
  • ተማሪዎች በ3ኛ የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ከሚያገኙት ውጤት በፊደል የሚሰጥ የመጨረሻ ውጤት አንድ አይነት ይሆናል
  • ተማሪዎች ከ3ኛ የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ አንድ ፊደል ከፍ ያለ የመጨረሻ የፊደል ውጤት ያገኛሉ
  • ተማሪዎች የመጨረሻ ውጤት በፊደል ወይም "Pass/Incomplete" የማግኘት ምርጫ አላቸው

ቦርዱ ሜይ 12 ስለሚወያይባቸው ጉዳዮች የበለጠ ለማወቅ እባክዎ ይህንን አጭር ቪድኦ ይመልከቱ። በተጨማሪ ይህንን አውታረመረብ መጎብኘት ይችላሉ Continuity of Learning ድረ-ገጽ/webpage

 

Scot Murphy Image