Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: May 12, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በፊደል የሚሰጥ ወይም አልፏል-አልፋለች/Letter Grade or “Pass” የሚል የውጤት አሰጣጥ አማራጭ እንዲኖራቸው የትምህርት ቦርድ ክለሳ የተደረገበትን የውጤት አሠጣጥ ፖሊሲ አፀድቋል።

የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞ፡-

ከኮቪድ ቫይረስ - COVID-19 ጋር በተገናኘ ያልትለመዱ/ያልተጠበቁ ሁኔታዎችን እና በ MCPS ወደ ርቀት ትምህርት የተደረገ ሽግግርን መሠረት በማድረግ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ - Montgomery County Board of Education ዛሬ ሜይ 12  አሁን ያለውን የውጤት አሰጣጥ ፖሊሲ ለማስወገድ እና በጊዜያዊ የውጤት አሰጣጥ ሲስተም ለመተካት ወስኗል።
ኤለመንተሪ፣ መካከለኛ (ሚድል ስኩል) እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች።

በሺዎች የሚቆጠሩ የ MCPS ተማሪዎች፣ ሠራተኞች፣ ወላጆች እና የማህበረሰብ አባላት የግብረመልስ ግብአት በመስጠት ኢ-ሜይሎችን ልከዋል፣ እና ስለ ውጤት አሰጣጥ አማራጭ ሃሳቦችንም ሰጥተዋል። እነዚህን ግብረመልሶች መሠረት በማድረግ፣ ለሁሉም ተማሪዎች ሚዛናዊ እና ፍትሃዊ የሆነ ሲስተም ተግባራዊ እንዲሆን ቦርዱ ኢላማ አድርጓል።

ለ 2019-2020 የትምህርት ዓመት (ጁን 15 የሚያበቃው)፦

ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

  • ለአራተኛ የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ - 4th Marking Period (MP4)፣ የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተሰጠው መስፈርት ተመርኩዘው "Pass/Incomplete" የሚለውን የውጤት አሰጣጥ ሲስተም መጠቀም ይቀጥላሉ። አራተኛውን የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ - 4th Marking Period ማለፊያ ውጤት ካገኙ፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የእያንዳንዱን ሴሚስተር ኮርሶች ውጤት በሦስተኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ - 3rd Marking Period (MP3) ካገኙት የአንድ ፊደል ውጤት ይበልጥ ያገኛሉ። ውጤቱ(ቷ) በፊደል እንዲሆን የተማሪው(ዋ) ምርጫ ከሆነ፣ የመጨረሻው ሴሚስተር ውጤት በትራንስክሪፕት ላይ ሪፖርት የሚደረግ ሲሆን በአጠቃላይ ድምር ተባዝቶ አማካይ ውጤቱ "cumulative grade point average (GPA)" ይቀመጣል። ይህ የውጤት አሰጣጥ አማራጭ አሁን ካለው የውጤት አሰጣጥ ሲስተም .ተሞክሮዎች ጋር የሚጣጣም ይሆናል እና ተማሪዎች የ MP3 ውጤታቸውን እንዲያሻሽሉ እድል ይሰጣል።
  • በፊደል ውጤት ፋንታ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሴሚስተሩን ማጠቃለያ “Pass” የሚለውን ውጤት ለመምረጥ ይችላሉ (መስፈርቶቹን በሙሉ የሚያሟሉ ከሆነ)፣ እና በእያንዳንዱ ኮርስ - course-by-course basis ይህንን አማራጭ መውሰድ ይችላሉ። በአንድ ኮርስ ላይ “Pass” ከመረጡ፣ ውጤቱ ለተማሪው(ዋ) "cumulative GPA" በአካፋይ ወይም ብዜት አይተነተንም።
  • የ 2019-2020 ትምህርት ዓመት ትራንስክሪፕት ላይ የሁለተኛው ሴሚስተር ሲመዘገብ “COVID-19” የሚል ምልክት ይጻፍበታል።
  • በ4ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ኮርስ የማለፍ መስፈርት - meet the criteria  ያላሟሉ ተማሪዎች አላሟላም/አላሟላችም የሚል ይሰጣቸዋል።

ሚድል ስኩል

  • የሙሉ ዓመት ኮርሶችን ለሚወስዱ የሚድል ስኩል ተማሪዎች፣ የእያንዳንዱ ኮርስ የማጠቃለያ ውጤት በማርክ መስጫ ክፍለ ጊዜ 1፣ 2፣ እና 3 አማካይ ውጤት ላይ ተመስርቶ ለአራተኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ - MP4 “Pass” ይሆናል፣ ይኼውም ከ MP3 ውጤት በአንድ ፊደል ከፍ ያለ ሲሆን ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጋር ተመሣሣይ ነው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ኮርሶችን ለሚወስዱ የሚድል ስኩል ተማሪዎች የውጤት አሰጣጡ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፀደቀውን የውጤት አሰጣጥ ፖሊሲ የሚከተል ይሆናል።

ኤለመንተሪ ት/ቤት

  • ለ4ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ በፊደል ማርክ-ውጤት አይሰጥም። ትኩረት የሚሰጠው በትምህርት ላይ የተማሪዎችን ተሳትፎ በማዳበር እና በተቻለ መጠን ከበርካታ ተማሪዎች ጋር በማገናዘብ ይሆናል። ከ 2ኛ ክፍል እስከ 5ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች፣ በፊደል የሚሰጠው የማጠቃለያ ውጤት በ MP1፣ MP2 እና MP3 አማካይ ውጤት ላይ የተመሠረተ ይሆናል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሠራተኞች ይህ አዲሱ ፖሊሲ በፍትኃዊነት እና በሚዛናዊነት ተግባራዊ መደረጉን እንዲሁም ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው የውሳኔው ግንዛቤ እንዳላቸው በማረጋገጥ የሲስተሙን አፈጻጸም ሒደት ያከናውናሉ።

በስብሰባው ወቅት በተደረገው ውይይት ላይ፣ ፍጹም የሆነ-ምንም አይነት ግድፈት የማይገኝበት ሲስተም እንደሌለ የቦርድ አባላት እውቅና ሰጥተዋል፣ ነገር ግን ለተማሪዎች አማራጭ እንዲኖራቸው እና የተማሪዎችን የትምህርት-አቋም በአዎንታዊነት የሚያንጸባርቅ ተማሪዎችን የሚረዳ አይነት የውጤት አሰጣጥ ሲስተም ሥራ ላይ መዋል እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተዋል።

amharic
*ከዚህ በላይ የተመለከተው ስላይድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሴሚስተር ኮርሶችን ብቻ የሚመለከት መሆኑን እባክዎ ይገንዘቡ

ቦርድ ያካሄደውን ውይይት ይመልከቱ
የትምህርት ቀጣይነት ድረ-ገጽ (Continuity of Learning webpage)

ከአክብሮት ጋር

Montgomery County Public Schools