Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: Oct. 07, 2019

mcps logo

ስለ አትሌቲክስ እና ተጨማሪ ከሪኩለም እንቅስቃሴዎች ቁጥጥር የውጭ ግምገማ

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

የተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ

በደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Damascus High School) በወንዶች ወጣቶች ቁምሣጥን ክፍል ውስጥ ኦክቶበር 31/2018 በተደረገው ወሲባዊ ጥቃት ሳቢያ በአትሌቲክስ እና ከቀለም ትምህርት ውጪ በሆኑ ፕሮግራሞች ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎችን ሠላም እና ደህንነት በይበልጥ ለማሻሻል የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አፋጣኝ እርምጃዎችን ወስዷል። የዚህ አይነተኛ ጥረት አንዱ አካል በመሆኑ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ “Wilmer Cutler Pickering Hale and Dorr (WilmerHale)” የተሰኘ የህግ ተቋምን በማሳተፍ በዲስትሪክቱ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከመደበኛ የትምህርት ሠዓት በኋላ የሚያካሄዷቸውን እንቅስቃሴዎች እንዲያጣራ/after-school investigation ተደርጓል። ይህ ግምገማ የተካሄደው በ MCPS ከተደረገው የውስጥ ምርመራ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ስቴት ዓቃቤ ሕግ ኦክቶበር 31 ከተከሰተው ተከታታይ የወንጀል ማጣራት ሂደት በተጨማሪ ነው።

WilmerHale በቀረበው ሪፖርት የግምገማ ግብ ላይ እንደተገለጸው፦ “MCPS የትምህርት ቤትን ባህል ለማሻሻ መውሰድ የሚችላቸውን እርምጃዎች ለይቶ ለማወቅ፣ ያሉትን ፖሊሲዎች ጭምር፣ ቅደምተከተሎችን፣ እና ክትትል/ቁጥጥር እና ሪፖርት ከማድረግ ትግበራዎች ጋር የተገናኙ ድርጊቶችን ጭምር፣ ለወደፊት በደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Damascus High School) የተፈጠረውን አይነት ክስተቶች ለመከላከል እንዲረዳ እና በዲስትሪክቱ የሚገኙት ጠቅላላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአትሌቲክስ እና በሌሎች ተጨማሪ ትምህርቶች ላይ ለሚሳተፉ ተማሪዎች ጤናማ፣ አበረታች፣ እና አመቺ የሆነ ድባብ መኖሩን ለማረጋገጥ ነው።” ግምገማው ያተኮረባቸው ነገሮች፦ ሠነዶችን ማጣራት፣ የፖሊሲ ዝርዝር ጥናት/ትንታኔ፣ እና ከሠራተኞች፣ ከተማሪዎች፣ እና የአካባቢ እና አገር አቀፍ ኤክስፐርቶችን በርካታ ቃለመጠይቆች በማድረግ የተንጸባረቁ ሃሳቦችን እና ግኝቶችን፣ የ WilmerHale አስተያየቶችን ጭምር ይዟል። ነገር ግን በሞንትጎመሪ ካውንቲ ስቴት ዓቃቤ ህግ ጽ/ቤት አማካይነት እየተካሄደ ላለው የምርመራ ሂደት ጥንቃቄ ለማድረግ ሲባል፣ በ DHS በተፈጠረው ክስተት ተጠቂ የሆኑትን፣ ማናቸውንም በድርጊቱ ተጠርጣሪ የሆኑትን፣ ወይም ማናቸውንም የእነርሱ ቤተሰቦች፣ በግምገማው አልተጨመሩም፣ እና WilmerHale ከዚህ በፊት ሪፖርት ያልተደረጉ ታሪካዊ ይዘት ያላቸው ክስተቶችን ዛቻ፣ ማስፈራራት፣ ማሸማቀቅ፣ ጾታዊ ጥቃት የመሣሠሉትን አጠቃላይ የሆነ ግምገማ አላደረገም።

ይህ በውጭ አካል የተደረገ ግምገማ ሦስት ቁልፍ ነገሮችን ተመልክቷል፦ የቅንነት መልካም ባህልን ማዳበር፣ ማበረታታት፣ ማነቃቃት፣ ጠንካራ የቁጥጥር ተግባሮችን በሥራ ላይ ማዋል፣ እና ክስተቶችን በአፋጣኝ ሪፖርት ማድረግን እና ምላሽ መሰጠቱን ማረጋገጥ።

የግምገማው መደምደሚያ፣ “የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በአጠቃላይ በጎነት ያለው መልካም ባህልን በአትሌቲክስ ዙርያ እና በሌሎች ኤክስትራከሪኩለሞች ላይ አዳብሯል።” እና MCPS ስለ ሪፖርት አስፈላጊ የሆኑ ግዴታዎች እና ቅደምተከተል መርሆች ዲስትሪክት አቀፍ ደንቦች አሉት። ሆኖም ግን የ WilmerHale ሪፖርት ትምህርት ቤት ስፖንሰር በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ላይ/after-school activities ስለሚሳተፉ ተማሪዎች ሠላም እና ደህንነት ቁጥጥር መገምገም እና መሻሻል የሚገባቸውን ለይቶ አቅርቧል። MCPS በግምገማው ላይ በተገለጹት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ በቅርብ ወራት በርካታ እርምጃዎችን ወስዷል። እነዚህም እርምጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦

  • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሠልጣኞች እና የአክቲቪቲዎች/activities ስፖንሰሮች የበለጠ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከትምህርት ሠዓት በኋላ/after-school የተሻሻለ ቁጥጥር የማድረግ/ሱፐርቪዥን ፕላን የመፍጠር አሠራርን ማሻሻል
  • ማሸማቀቅ፣ ማስፈራራት/ዛቻ፣ ትንኮሳ እና ጥቃት የመሣሰሉትን ለመከላከል እርስበርስ ተግባብተው አዎንታዊ ተፅእኖ መፍጠር እንዲችሉ በተማሪ-የሚመራ ስልጠና ለማዳበር ከ MCPS መሪዎች ጋር የሚሠራ የተማሪ-አትሌት መሪዎች ካውንስል እንዲጀመር ማድረግ

በተጨማሪም፣ በቀጣዩ ዓመት፣ MCPS ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን እርምጃዎች የመውሰድ እቅድ አለው

  • ከትምህርት ሠዓት በኋላ/after-school የደህንነትና ሠላም ቁጥጥርን በሚመለከት ምርጥ የአፈጻጸም ተሞክሮዎችን በማድረግ በአገር አቀፍ መሪ ለመሆን ከ National Center for Sports Spectator Safety and Security ጋር ትብብር መፍጠር
  • የዋና ጽህፈት ቤትን እና በትምህርት ቤት የተመሠረተ የአትሌቲክስ እና ከትምህርት ሠዓት በኋላ የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች/after-school የሱፕርቪዥን መዋቅር አጠቃሎ የያዘ ለመተባበር፣ ለቁጥጥር፣ እና ለደህንነት ጥበቃ አመቺ የሆነ መዋቅር ማሻሻል
  • ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከትምህርት ሠዓት በኋላ የሚካሄዱ ፕሮግራሞች/after-school programming የደህንነት እና የሱፐርቪዝን ሥራ ለመደገፍ የሚሆን የሪሶርስ ማሟያ በጀት  መዘርጋት
  • በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቻችን በሙሉ በአትሌቲክስ እና በካሪኩለም ተጨማሪ አክቲቪቲዎች ላይ/athletic and extracurricular activities ለሚሳተፉ ተማሪዎች የስነምግባር ትምህርት ፕሮግራሞችን ድጋፍ መስጠት
  • በህዝብ ፋሲሊቲዎች ላይ የማህበረሰብ አጠቃቀምን በሚመለከት ከ Innteragency Coordinating Board (ICB) ጋር ያለውን የመግባቢያ ሠነድ/ Memorandum of Understanding ሠላምና ደህንነት ጥበቃን በሚመለከት ተገቢ ሽፋን የሚሰጥ መሆኑን ለማረጋገጥ ክለሣ ማድረግ። ይህ የአስቸኳይ ጊዜ/ለድንገተኛ ሁኔታ ፈጣን ምላሽ የመስጠት እቅድ እና ለ ICB የሥራ ባልደረቦች የተሟላ ስልጠና መስጠትን ያካትታል
  • ስለ ማሸማቀቅ፣ መፈታተን፣ ማስቸገር፣ ማስጨነቅ፣ መተንኮስ ማጥቃት (በፆታ፣ በዘር፣ ወ.ዘ.ተ) የ MCPS  ሪፖርት አቀራረብ  ቅደምተከተል ክለሳ በማድረግ ይበልጥ ግልፅ የሆነ ግንዛቤ ማስጨበጥ
  • ስለ አትሌቲክስ እና ከትምህርት ሠዓት በኋላ የሚካሄዱ ፕሮግራሞች/after-school programming አቋም ለትምህርት ቦርድ ዓመታዊ የሆነ አስፈላጊ መረጃዎችን ገለፃ መስጠት

ይህ የተሻሻለ የሱፐርቪዥን ስትራቴጂ የተማሪዎቻችንን ሠላምና ደህንነት የመጠበቅ አቅማችንን ያጠናክረዋል ብለን እናምናለን። ግባችን በትምህርት ቤት ማሸማቀቅን፣ ማስጨነቅን፣ ትንኮሳን በፆታ፣ በዘር፣ ወ.ዘ.ተ ጥቃትን ለመከላከል የሚያስችል የቁጥጥር መዋቅር በመዘርጋት ጤናማ/መልካም የትምህርት ቤት ድባብ መፍጠር ነው።

በውጭ ገምጋሚዎች የተነገሩትን ጠቃሚ ጉዳዮች የማህበረሰቡ አባላት እንዲቃኙት እናበረታታለን። በ WilmerHale ሪፖርት ላይ የቀረቡትን የግምገማ ግኝቶች እና አስተያየቶች በሙሉ MCPS ተግባራዊ እያደረገ ስለሆነ እናንተም ተሳትፎ እንድታደርጉ እንጋብዛለን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለሁሉም ተማሪዎች ሠላማዊ እና ምቹ የሆነ የትምህርት አካባቢ ለመስጠት ቁርጠኛ ነው። ምርጥ ተሞክሮዎችን እየወሰድን በዚህ ወሳኝነት ባለው ሥራ ግንባር ቀደም ለመሆን እና ከተማሪዎች ጋር፣ ከሠራተኞች ጋር፣ ከማህበረሰብ አባላት እና ከህግ አስከባሪ ሸሪኮቻችን ጋር ይህ ዋና ተግባራችን ስኬታማ እንዲሆን በትብብር እንሠራለን።

ከአክብሮት ጋር

Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of Schools
ዶ/ር ጃክ አር ስሚዝ
የትምህርት ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ