Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: March 27, 2020

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


ርእሰ ጉዳይ፦ ልዩ የግል ትምህርት ፕሮግራሞች "Individualized Education Programs" ወይም ሰክሽን 504 ፕላን "Section 504 Plans" ተማሪዎች ወላጆች/ሞግዚቶች።

የተወደዳችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ቤተሰቦች፣

ሁሉም ተማሪዎች የተቀናበረ የትምህርት ቤት ልምድ እንዲኖራቸው ለማስጀመር MCPS የመጀመሪያውን ምእራፍ ቀጣይ (በርቀት/ከቤት የመማር ሲስተም) ትምህርት ማርች 30/2020 እንደሚጀመር ሱፐርኢንተንደንት ጃክ ስሚዝ/Superintendent Jack Smith ማርች 22/2020፣ ባስተላለፉት መልእክት ገልጸዋል። ሰኞ፣ ማርች 30 መምህራኖቻችን እና የ 10 ወር ድጋፍ ሰጪ የሥራ ባልደረቦች ወደ ሥራ የሚመለሱበት የመጀመሪያ ቀን ይሆናል። ከተማሪዎቻቸው ጋር እንደገና ለመገናኘት በናፍቆት እና በጉጉት ላይ ናቸው።

በግል ትምህርት ፕሮግራሞች ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ቤተሰቦች/Individualized Education Programs (IEPs) እና የ1973 የመልሶ ማቋቋም ደንብ/Section 504 of the Rehabilitation Act of 1973 መሠረት የመቀበያ (Section 504) በርካታ ጥያቄዎች እንዳላቸው እናውቃለን። ባለፉት ጥቂት ሣምንታት በሙሉ፣ ትምህርት እንዲቀጥል በጥንቃቄ የታሰበበት እርምጃ ለመወሰን የስፔሻል ኢጁኬሽን ጽ/ቤት፣ ችግር/አለመግባባት ማስወገጃ እና የቅሬታ ሰሚ ክፍል፣ እና የጀነራል ካውንስል ጽ/ቤት ከአካባቢ እና ከስቴት የትምህርት ኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር እየሠሩ ቆይተዋል። የማስተማር ዘይቤው በአካል ከሚደረገው ወደ ኦንላይን የተሸጋገረ በመሆኑ ተማሪዎች እና አስተማሪዎች ራሳቸውን ለማለማመድ-ለማስተካከል ጊዜ ይፈልጋሉ።

በዚህ መሠረት፣ ከማርች 16 እስከ ማርች 27/2020 ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ምክንያት ተላልፈው የነበሩ የ IEP እና Section 504 ስብሰባዎች በሙሉ እንደገና መርሃግብር-ቀጠሮ ይያዝላቸዋል። ከማርች 30 እስከ ኤፕሪል 3 የተያዙት የ IEP እና Section 504 ስብሰባዎች በሙሉ እንዲተላለፉ የተደረገ ሰልሆነ እንደገና መርሃግብር-ቀጠሮ ይያዛል።

ከሰኞ፣ ማርች 30 ጀምሮ ተማሪዎች እና ወላጆች ከኦንላይን መሣሪያዎች/online tools ጋር ለመለማመድ ቱቶሪያል ትምህርቶችን የመውሰድ እድል ይኖራቸዋል። ሠራተኞች የተማሪን ትምህርት ሂደት ለመርዳት እና የእነርሱን "myMCPS classrooms" ለማመቻቸት አዲሱን እና ቀደም ሲል የሚያውቁትን የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች ጭምር በተለያዩ የሙያ ማበልጸግ ርእሶች ላይ ይሳተፋሉ። በእነዚህ ቨርቹዋል መሣሪያዎች/virtual tools አማካይነት ስንክልና ያላቸው ተማሪዎችን ጨምሮ ጠቅላላ ተማሪዎች የመማር ተደራሽነት እንደሚኖራቸው ለማረጋገጥ ያለመታከት እየሠራን ነው።
የኤለመንተሪ ት/ቤት ሠራተኞች ከሰኞ እስከ ረቡእ (ማርች 30 - ኤፕሪል 1) ድረስ በፕሮፌሽናል ትምህርት ላይ ይሳተፋሉ። ረቡእ፣ ኤፕሪል 1 ከተማሪዎች ጋር መገናኘት ይጀምራሉ እና ሐሙስ፣ ኤፕሪል 2 ከተማሪዎች ጋር ትምህርት ይጀምራሉ።

የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሠራተኞች ሰኞ እና ማክሰኞ (ማርች 30-31) ፕሮፌሽናል ትምህርት ላይ ይሳተፋሉ። ከረቡዕ ኤፕሪል 1 ጀምሮ ከተማሪዎች ጋር ዳግም ይገናኛሉ እና ሦስተኛውን የማርክ ክፍለጊዜ ማገባደድ ይጀምራሉ።

በ IEPs ወይም Section 504 Plans ለታቀፉ ተማሪዎች፣ በእነርሱ ግላዊ ሁኔታ የተዘጋጀ ማስተማር በተቻለ ለማሳደግ ወይም የእነርሱን Section 504 accommodations የተቻለውን ያክል ሁሉ በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንሠራለን። ረቡእ፣ ኤፕሪል 1 ጀምሮ፣ ስለ ግላዊ ድጋፎች ለመወያየት ከእናንተ ጋር ተመልሰን እንገናኛለን። ከሚቀጥለው ሣምንት ጀምሮ ስለሚኖሩት ሂደቶች ከዚህ በታች መረጃዎች ይገኛሉ። ከፌደራል፣ ከስቴት እና ከአካባቢ የትምህርት እና የጤና ዲፓርትመንቶች ተጨማሪ መረጃ-ኢንፎርሜሽን እና መመሪያ ሲደርሰን፣ እናሳውቃችኋለን።


የ Virtual IEP እና Section 504 ስብሰባዎች       

  • የትምህርት ቀጣይነትን ስለመተግበር የ virtual IEP እና Section 504 ስብሰባዎችን መርሃግብር ለማዘጋጀት ሠራተኞቻችን ከከባድ ሁኔታ ቡድን አባላት/critical team members ጋር ይሠራሉ።
  • ስብሰባዎች የሚካሄዱት በ conference call ወይም Google Meet ወይም Google Hangouts በመጠቀም ነው።
  • ስለ እርስዎ ልጅ የግል ትምህርት ፕላን ስለሚቀጥልበት ሁኔታ ለመወያየት ማርች 30 በሚውልበት ሣምንት ኬዝ ማኔጀሮች ያነጋግሩዎታል።
  • ከስብሰባዎቹ በፊት እና በኋላ ዶኩሜንቶች ለእርስዎ ይላካሉ። ኮምፒውተር ከሌለዎት እና ዶኩሜንቶችን በህትመት የሚፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎ የእርስዎን ኬዝ ማኔጀር በሚያገኙ ጊዜ ይንገሩ።
  • virtual meeting-ስብሰባ ላይ እንዴት መሣተፍ እንደሚችሉ እና በስብሰባው ወቅት ውይይት ስለሚደረግባቸው ዶኩመንቶች ጭምር መግለጫ ይሰጥዎታል።

ለተማሪዎች አካደሚያዊ ድጋፍ
ኬዝ ማኔጅመንት

  • ለእርስዎ ልጅ የ IEP goals ወይም 504 Plan accommodations ለመተግበር የሚያስፈልግ የትምህርት ፕላን ግላዊ ድጋፎችን እና ልጅዎ ትምህርት የሚቀጥልበትን/የምትቀጥልበትን ሁኔታ ለመወያየት በሚቀጥለው ሣምንት ኬዝ ማናጀር ያነጋግርዎታል-ታነጋግርዎታለች።
  • በዚህ የመጀመሪያው ግንኙነት፣ በተከታታይ መደረግ ሰላለበት check-ins፣ የሪሶርስ አሰጣጥ፣ ከወላጅ ጋር ስለሚደርግ ግንኙነት የሚጠበቁ ዝርዝሮች ይዘጋጃሉ።

የመዳረሻ ገፅታዎች

  • ለተማሪዎች የሚሰጣቸው የትምህርት-ይዘት ሊያከናውኑ በሚችሉበት ደረጃ እየተዘጋጀ ነው/Content for students is being developed with accessibility standards። ስንክልና ያላቸው ተማሪዎች በ IEPs ወይም Section 504 እቅዶች ላይ በተዘረዘረው መሠረት በ MCPS-provided Chromebooks አማካይነት የሚያግዝ ቴክኖሎጂ/assistive technology፣ በ Google Read & Write ለሒሳብ እና ሌሎችም በ Google Suite ላይ የሚገኙ/embedded features አማካይነት አጋዥ ቴክኖሎጂ ይጠቀማሉ።
  • በዚህ ወቅት ተጨማሪ አጋዥ ቴክኖሎጂዎች ማግኘት አስፈላጊ ከሆነ፣ የ IEP እና Section 504 ቡድኖች ከቤተሰቦች ጋር ይሠራሉ።

የስፔሻል ኢጁኬሽን አስተማሪ/የረዳት አስተማሪ ድጋፎች

የስፔሻል ኢጁኬሽን አስተማሪዎች ከአጠቃላይ ትምህርት አስተማሪዎች ጋር በጋራ ፕላን ያዘጋጃሉ እንዲሁም አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ በጋራ ያስተምራሉ። ለእርስዎ ልጅ ፓራ ኢጁኬተር ምን አይነት ድጋፎችን መስጠት እንደሚችል/እንደምትችል ለመወሰን ስፔሻል ኢጁኬሽን አስተማሪዎች ከፓራ ኢጁኬተሮች ጋር ይተባበራሉ።

ወደ አማራጭ የትምህርት ውጤች እየሰሩ ላሉ ተማሪዎች አካደሚያዊ ድጋፍ መስጠት የተሻሻለ/modified መርሃግብር እና ቁሳቁሶችን ያካትታል። የጨረሱበትን ሠርተፊኬት ለማግኘት ለሚሠሩ ተማሪዎች የአማራጭ ትምህርት ማእቀፍን ለመርዳት የልዩ ትምህርት ጽ/ቤት = Office of Special Education የተማሪዎችን ፍላጎት በሚያሟላ ሁኔታ የተዘጋጀ ከሪኩለም ማቴሪያሎችን መርሃግብር አዘጋጅቷል። ስለዚህ የተሻሻለ/modified መርሃግብር የእርስዎ ልጅ ኬዝማኔጀር አጭር መግለጫ ይሰጥዎታል/ተሰጥዎታለች። School Community-based፣ Autism and Learning for Independence የመሣሰሉ ፕሮግራሞችን ለማጠናከር፣ ድጋሚ ለማስተማር እና የተሻሻሉ ትምህርቶችን በመስጠት የስፔሻን ኢጁኬሽን አስተማሪዎች ተማሪዎችን የሚረዱበት የጊዜ ማእቀፍ ተበጅቷል።

ጣልቃ ገብነት/Interventions
በዚህ የተገደበ ባይሆንም፣ i-Ready Math፣ Systems 44 እና Math 180 የመሣሰሉ በኮምፒውተር ድጋፍ የሚሰጡ አካደሚያዊ ጣልቃ ገብነቶች ይኖራሉ።

Section 504 Accommodations
ትምህርቱ እየቀጠለ ሲሄድ፣ ይህንን የተሻሻለ ከሪኩለም እንደአስፈላጊነቱ ጥግ ለማድረስ አስተማሪዎች በእርስዎ ልጅ Section 504 Plan ላይ ያሉትን አኮሞዴሽኖች ተግባራዊ ይደረጋሉ።

ግምገማ እና ዳሰሳዎች

  • የእርስዎ ተማሪ በዚህ ወቅት ብቁ በመሆን ጀማሪ ደረጃ ላይ ከሆነ(ች)፣ ወይም ለዳግመኛ ግምገማ የታሰበ(ች) ከሆነ፣ ግምገማዎቹን ለማጠናቀቅ ከኦርጅናል የጊዜ ማእቀፍ ጋር ማስተካከል ያስፈልግ ይሆናል።
  • በርቀት አንድ አይነት ተመሣሣይ መደበኛ ግምገማ/virtually እንዴት እንደሚደረግ እና/ወይም የወላጅ እና የተማሪ ቃለመጠይቅ የመሣሰሉ ለግምገማ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን-ኢንፎርሜሽን የሚሰበሰብበትን ሁኔታ ለማስረዳት ገምጋሚዎቹ ያነጋግሩዎታል።
  • በአካል መገኘት የሚያስፈልጉ ግምገማዎች ትምህርት ቤቶች እንደገና በሚከፈቱበት ጊዜ ለማድረግ ይተላለፋሉ።
  • ስለ ግምገማው የግል ጥያቄዎች ካሉዎት እባክዎ ከኬዝ ማኔጀርዎ ጋር አብረው ይነጋገሩ።

 
ተዛማጅ አገልግሎት መስጠት

  • ተዛማጅ አገልግሎት ስለመስጠት፦ ከሙያ ሥራ ጋር የተያያዘ አሰልጣኝ-ሐኪሞች/occupational therapists፣ የሰውነት ሃኪሞች/physical therapists፣ የትምህርት ቤት ካውንስለሮች/school counselors፣ የትምህርት ቤት ሳይኮሎጂስቶች/school psychologists፣ ሶሻል ዎርከሮች/social workers እና የንግግር ቋንቋ አስጠኚዎች/speech language pathologists የመሣሰሉትን ሊያካትት ይችላል።
  • በዚህ ወቅት ከእርስዎ ልጅ የ IEP አገልግሎቶች ጋር የሚገናኙ አገልግሎቶች ላይ ተመርኩዞ፣ ተዛማጅ ተግባራዊ አገልግሎት ሰጪዎች በመጪዎቹ ሣምንቶች ስለ ተዛማጅ ተግባራዊ አገልግሎት ለመወያየት አገልግሎት ሰጪዎች ያገኙዎታል።
  • አንዳንድ በእጅ የሚሠሩ አገልግሎቶችን አሁን ቀጣይ ትምህርት እየተካሄደ ባለበት ወቅት ለመስጠት ጤናማ ላይሆን ይችላል።
  • በ IEPs ተዛማጅ አገልግሎት የሚሰጣቸው ተማሪዎች ወላጆች/ሞግዚቶች ከሚከተሉት አንዱን ወይም ሁለት መጠበቅ አለባቸው፦ በተማሪው(ዋ) ሁኔታ ተመስርቶ የተሻሻለ ቀጥተኛ አገልግሎቶች/individually modified direct services to students፣ ለ IEP ቡድን የማማከር አገልግሎቶች/ consultative services to the IEP team፣ የቤተሰብ ማሠልጠኛ ሞዴል ስትራቴጂዎች/strategies for a family coaching model፣ እና/ወይም በቴሌፎን ጥየቃዎች/tele-visits።
  • በእርስዎ ልጅ Section 504 Plan ላይ አሁን ባሉት ምክር ጋር የተገናኙ አገልግሎቶችን በመመርኮዝ፣ ተፈጻሚነት ያለው ተዛማጅ አገልግሎት ሰጪ(ዎች) ስለ እርስዎ ልጅ Section 504 Plan መሠረት ስለሚሰጡት ተዛማጅ የምክር አገልግሎት(ቶች) ለመወያየት በመጪዎቹ ሳምንቶች ያገኙዎታል።
  • ተዛማጅ አገልግሎት ሰጪዎች የተማሪዎችን እና የቤተሰቦችን ጥያቄዎቻቸውን ለመመለስና ለመርዳት በስልክ፣ በቴክስት ወይም በኢ-ሜይል ይገኛሉ።

የመሸጋገሪያ ተግባሮች/Transition Activities

  • በ 14 ዓመት እድሜ ለሚጀምሩ (ወይም 13 ዓመት እድሜ ላይ ጀምረው በ IEP ዓመት 14 ዓመት ለሚሞላቸው) የ IEPs ተማሪዎች የሽግግር አገልግሎቶች በየአመቱ ይጠናቀቃሉ።
  • ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ በእርስዎ ልጅ የ IEP የሽግግር አክቲቪቲዎችን ግላዊ ድጋፎች በሚመለከት ለመወያየት በመጪዎቹ ሳምንቶች የሽግግር ድጋፍ ሰጪ አስተማሪዎች ያነጋግሩዎታል።
  • ለሚድል ስኩል ተማሪዎች፣ ስለ እርስዎ ልጅ ወቅታዊ IEP፣ ስለ ግላዊ የሽግግር ወቅት ድጋፍ አክቲቪቲዎች ለመወያየት በመጪዎቹ ሣምንቶች የስፔሻል ኢጁኬሽን ሪሶርስ አስተማሪዎች ያነጋግሩዎታል።
  • ሥራ የመቀጠር ሙያ ጋር የተገናኘ ወይም community-based instruction ትምህርትን በሚመለከት የሽግግር አክቲቪቲዎች በገቨርነት ላሪ ሆጋን/Governor Larry Hogan አማካይነት በተጣሉት ማእቀቦች መሠረት እንዴት ምላሽ እንደሚሰጥ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሠራተኞች ማብራሪያ ይሰጣሉ-ያስረዳሉ።

ለተማሪዎቻችን፣ ለሠራተኞቻችን እና ለትምህርት ቤት ማህበረሰቦች ጤንነትና ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ስላደረጋችሁት ግንዛቤ እና በቀጣይነት ስለምታሳዩት ቁርጠኝነት እናመሰግናለን።

ከቤተሰቦች ጋር መደበኛ ወቅታዊ መረጃ በ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የኮሮና ተዋሲ የቀጣይ ትምህርት ድረ-ገጽ/MCPS Coronavirus Continuity of Learning webpage አማካይነት ይተላለፋል። በተጨማሪ፣ በዩ. ኤስ. የትምህርት ዲፓርትመንት/U.S. Department of Education እናበሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት/Maryland State Department of Education አማካይነት በስፔሻል ኢጁኬሽን የትምህርት ቤት ቡድኖችን የሚረዳ የተለየ መመሪያ አዘጋጅተዋል።